አስቶንቪላ ቪላ ማርከስ ራሽፎርድን በውሰት ውል አስፈረመ
**************
አስቶንቪላ የማንቸስተር ዩናይትድ አጥቂ የነበረውን ማርከስ ራሽፎርድን በውሰት ውል ማስፈረሙ ተገለጸ።
በውሉ መሰረት የ27 አመቱ ተጫዋች እስከ የውድድር ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በሚኖረው ቆይታ 75 በመቶው የተጨዋቹ ደሞዝ በአስቶን ቪላ ይሸፈናል ተብሏል፡፡
በውሉ ላይ አስቶን ቪላ በሰኔ ወር በ40 ሚሊየን ፓውንድ ተጫዋቹን የግሉ የሚያደርግበት የግዢ አማራጭ እንዳለውም ተገልጿል።
ራሽፎርድ በኢንስታግራም ገፁ ላይ “ይህ የብድር ውል እንዲፈፀም በማድረጋቸው ማንቸስተር ዩናይትድን እና አስቶን ቪላን ማመስገን እፈልጋለሁ” ሲል ሀሳብን ጠቅሷል።
ተጨዋቹ በማንችስተር ዩናይትድ የ20 አመታት ቆይታው በ426 ጨዋታዎች 138 ግቦች እና አምስት ዋንጫዎች አሳክቷል።
በሴራን ታደሰ