የአፋር እና ሶማሊ ወንድማማች ህዝቦች የኢፍጣር መርሐ ግብር በጅግጅጋ
*********************************
ዛሬ ምሽት የአፋር እና ሶማሊ ወንድማማች ህዝቦች ታላቅ የጋራ የኢፍጣር መርሐ ግብር በጅግጅጋ ይካሄዳል።
ለዚህም በአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳደር አወል አርባ የተመራ ልዑክ ጅግጅጋ ገራድ ዊልዋል አየር ማረፊያ ሲደርስ የሶማሊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፋ ሙሁመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በሶማሊና አፋር ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ላይ አልፎ አልፎ የሚከሰቱ ግጭቶችን ለማስቆምና ዘላቂ ሰላም ለማስፈን በሁለቱ ክልል አመራሮች መካከል በቅርቡ ስምምነት መደረጉ ይታወሳል።
አሁን ላይ በሰላም ሚኒስትር፣ በሁለቱ ክልል አመራሮችና በባለድርሻ አካላት ጥረት በክልሎቹ አዋሳኝ አካባቢዎች ላይ የሚከሰቱ ግጭቶችን ማስቆም እንደተቻለ የሰላም ሚኒስቴር በቅርቡ ያወጣው መረጃ ያመለክታል።
በቀጣይም ሰላምን ለማፅናትና የግጭት ምክንያቶችን በመለየት ዘላቂ መፍትሄ ለማስቀመጥ በትኩረት መስራት እንደሚያስፈልግ የተጠቆመ ሲሆን በሁለቱ ክልል አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ተደጋጋሚ ውይይቶች ሲካሄዱም ቆይቷል።
በዛሬው ዕለትም የሁለቱ ክልል አመራሮችና ልዑካቸው የጋራ የአፍጥር ፕሮግራም የሚካሄድ ሲሆን ይህም የሁለቱን ህዝቦች የህዝብ ለህዝብ ትስስር ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚያግዝ ነው የተጠቆመው።
የሰላም ሚንስትሩ አቶ መሀመድ እድሪስ፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፕሬዝዳንት ሼኽ ሃጂ ኢብራሂም ቱፋ እንዲሁም የፌደራል የስራ ሀላፊዎች በጋራ የአፍጥር ፕሮግራሙ ላይ ለመሳተፍ ጅግጅጋ ገብተዋል።
በቴዎድሮስ ታደሰ