የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር ጋር ተወያዩ
********************
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አቭራሃም ንጉሴ (ዶ/ር) ጋር ተወያይተዋል፡፡
ውይይቱ የሀገራቱን ዲፕሎማሲያዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብር ማስፋት በሚቻልበት አግባብ ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ሀገራቱ በተለይ በንግድ፣ ኢንቨስትመንት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር ዘርፎች ያላቸውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ማሳደግ በሚያስችሉ ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
ሁለቱ ወገኖች ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር ቁርጠኝነታቸውን የገለፁ ሲሆን በተለይም የእስራኤልን የኢንቨስትመንት አቅምና የተራቀቀ ቴክኖሎጂ የኢትዮጵያን አዲስ የኢኮኖሚ ማሻሻያ እና የልማት ዕቅዶች እንዲደግፍ ተስማምተዋል፡፡
ሁለቱ ሀገራት በታሪክ በባህል እና በዲፕሎማሲ ዘርፎች የቆየ ግንኙነት እንዳላቸውም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡