Ethiopian Public Health Institute | የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


EPHI one of the oldest and known public health institutes in Africa. It is open 24/7 for public health emergency management through Emergency Operation Center.
For any information and help call 8335 or send us a message through ephieoc@gmail.com

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


የወባ በሽታን አስመልክቶ በአገር አቀፍ ደረጃ ሳምንታዊው የውይይት ስብሰባ ተካሄደ
በአገር አቀፍ ደረጃ የወባ በሽታ ወቅታዊ ሁኔታን በተመለከተ ዛሬ ጥር 19/2017 ዓ.ም  በኢንስቲትዩቱ የስልጠና ማዕከል በበይነ መረብ ሳምንታዊ የውይይት ስብሰባ ተካሄደ፡፡
በአገር አቀፍ ደረጃ ወቅታዊ የወባ ወረርሽኝ በተመለከተ የኢንስቲትዩቱ የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ማስተባበሪያ ማዕከል፣ የክልል ጤና ቢሮዎች፣ ክላስተሮች የወባ ወረርሽኝን አስመልክቶ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን፣ የታዩ ለውጦችን ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን የወባ ወረርሽኝ ከመከላከልና ከመቆጣጠር አኳያ በአገር አቀፍ ደረጃ በሁሉም ክልሎችና ክላስተር ወረዳዎች ወረርሽኙ እየቀነሰ ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች የመከላከል ስራው ላይ የመቀነስ ሁኔታዎች እንደሚታዩ ተገልጿል።  
ለተማሪዎች የጤና ትምህርት የተሰጠ መሆኑን፣ በተለያዩ በማህበራዊ ሚዲያዎች፣ በቴሌቪዥን፣ በሬዲዮ ለማሕበረሰቡ የወባ የመከላከያ መንገዶች እና የጤና ትምህርቶችን አስመልክቶ የግንዛቤ ስራዎች መሰራታቸውን፣ እስከ አሁን የተሰሩ ስራዎች ውጤታማነትን በተመለከተ ግምገማ መደረጉን እና በቀጣይም የመከላከልና የመቆጣጠር ተግባራት በተሻለ መንገድ ማጠናከር እጅግ አስፈላጊ መሆኑን፣ ስለሆነም አካባቢን ከማጽዳት አንጻር ሕብረተሰቡን በማስተባበር በዘመቻ መልክ የተለያዩ ስራዎችን ለመስራት መታቀዱን ክልሎች በሪፖርታቸው ገልጸዋል፡፡  
ዶ/ር መልካሙ አብቴ የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና  ዳይሬክተር የውይይቱን ማጠቃለያ ሃሳብ በሰጡበት ወቅት እንደገለጹት የወባን ወረርሽኝየመከላከሉና የመቆጣጠሩ ስራ ውጤታማ መሻሻል ማሳየቱን፣ በሁሉም አካባቢ የተጠናከረ የመከላከል ተግባራት ሲከናወኑ መቆየታቸውን ጠቅሰው፤ ከክልል እስከ ወረዳ በተዋረድ የሚገኙ አመራር አካላት ሁሉ ከዚህ በፊት ሲደረግ የነበረውን የመከላከልና የመቆጣጠር ድጋፍ በማጠናከር መከናወን የሚገባቸው ተግባራት መስራት እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ያሳሰቡ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ኃላፊነቱን ከመወጣት አንጻር አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑን ተናግረዋል፡፡




የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አመራሮችና ሠራተኞች በዛሬው ዕለት በተካሄደው ወርሃዊ የጤና ማስ ስፖርት ላይ ተሳተፉ።
የዚህን ወር ማስ ስፖርት የጤና ሚኒስቴር ከአለርት ሆስፒታል እና ከአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነበር።




CALL for ABSTRACTS
------------------------------------
National Malaria
Consultative Meeting on
Overcoming Malaria Chalenges


Building National Health Security Enhances global Health Security
----------------------------
Ethiopia conducted the 2024 International Health Regulation (IHR) State Party Self-assessment Annual Report (SPAR) on a workshop conducted from January 21-24,2025 in Hawassa. The workshop brought together a diverse group of participants from government sectors, UN agencies, and different partners. The objective of the meeting was to produce the 2024 mandatory state parties annual report for Ethiopia based on the One Health approach, which will be submitted to the World Health Organization (WHO). 
Dr. Messay Hailu, the Ethiopian Public Health Institute’s (EPHI) Director General at the opening of the workshop said that the SPAR process is vital in tracking the country's progress and identifying areas that require further attention and improvement. The Director General further stressed that the tool, which will be used by the participants, has been instrumental in monitoring the implementation of the capacities required under the international health regulation. Dr. Messay further mentioned the datas collected have been made available through the Global Health Observatory (GHO), providing valuable insights into the health profiles of countries and regions.
Speaking on his behalf, Dr. Feyessa Regassa, International Health Regulations and One Health Office Head, stated that since the One Health approach acknowledges the interdependence of environmental, animal, and human health, it is essential to attain the best possible health outcomes and tackle the intricate health issues that affect everyone and cut across national boundaries. Dr. Feyessa went on to say that the workshop's wide collection of attendees reflected the spirit of cooperation that motivates everyone's efforts to ensure both national and international health security.
In addition to expressing their support and commitment to the overall activities, partner organizations from WHO, FAO, CDC, USAID, UKHS, and RTSL Heads & representatives reaffirmed their dedication to maintaining and accelerating the momentum and tackling new issues through cooperation and communication.
www.ephi.gov.et/news




ወባን ለማስወገድ አዳዲስ ስልቶች እና ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም በሚቻልበት መንገድ ላይ ከአጋር ድርጅቶች ጋር ውይይት ተካሄደ
https://www.facebook.com/share/p/1AjfWhm75F/




ለኢንስቲትዩቱ ሰራተኞች በሙሉ
የኢንስቲትዩቱ ሰራተኞች ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ማለትም የስኳር፣ የደም ግፊት እና የኮሊስትሮል መጠንን እንዲያውቁ ለማድረግ ወይም ያስችላው ዘንድ አርብ ከጥር 16 ቀን ጀምሮ በኢንስቲትዩቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ነፃ ምርመራ ሊደረግ በመሆኑ ከላይ ከተጠቀሰው ቀን ጀምሮ ፍላጎት ያላችሁ የኢንስቲትዩቱ ሰራተኞች ምርመራ ለማድረግ የተጋበዛችሁ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ የምርመራው ተሳታፊ በመሆን ጤንነትዎን ይጠብቁ፡፡
የኢንስቲትዩቱ የስርዓተ ጤና ምርምር ዳይሬክቶሬት


የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ፣ የጤና ሚኒስትር ዴኤታዎች እና የተጠሪ ተቋማት የስራ ኃላፊዎች የኢቢሲ (EBC) ሚዲያ ኮምፕልክስን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡
https://www.facebook.com/share/p/1D5V6oGUuY/




የጤና ላቦራቶሪ አገልግሎትን ጥራት በማስጠበቅ እና ባዮሴፍቲ እና ባዮሴኪዩሪቲ ስርዓቶችን ለተገበሩ የጤና ላቦራቶሪዎች የእውቅና እና የምስክር ወረቀት ተሰጠ።
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከUK Health Security Agency (UKHSA) ጋር በመተባበር ከተለያዩ ክልሎች ለተውጣጡ 10 የጤና ላቦራቶሪዎችን የላብራቶሪ ጥራት ስርአት ማሻሻያ ፕሮግራም (Strengthening Laboratory Management Towards Accreditation/SLIPTA/) እንዲሁም 16  ተጨማሪ  በባዮ-ሴፍቲ እና ባዮ-ሴኪዩሪቲ ሰርተፍኬት ፕሮግራምን ለተገበሩ ላቦራቶሪዎች  የእውቅና እና የምስክር ወረቀት የመስጠት ፕሮግራም በአዲስ አበባ ጥር 8/2017 ዓ.ም ተካሄደ። በፕሮግራሙም ላይ የUKHSA ሃላፊዎች እና ተወካዮች፣ የክልል የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና የክልል ላቦራቶሪዎች ሃላፊዎች፣ ከተመረጡ የጤና ተቋማት የመጡ የሆስፒታል ስራስኪያጆች እና የላቦራቶሪ ሃላፊዎች፣ የላቦራቶሪ ባለሙያዎች  እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በዝግጅቱ ላይ ተሳትፈዋል።
በዝግጅቱ ላይ ተገኘተው የእንኳን ደህና መጣችሁና የመክፈቻ መልዕክት ያስተላለፉት የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሳሮ አብደላ እንደገለጹት የላቦራቶሪ ጥራት የማሻሻልና የአክሪዲትሽን ስራዎች ላይ የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የትኩረት አቅጣጫ (ፍላግ-ሽፕ) በመሆኑ በዚህ ዘርፍ እየተሰሩ ካሉ ስራዎች አንዱ ከUKHSA ጋር በመተባበር ባለፉት ዓመታት ከተለያዩ ክልሎች ለተመረጡ ላቦራቶሪዎች አስፈገላጊውን ድጋፍ እና ክትትል ኢንስቲትዩቱ ሲያደረግ እንደነበር እና በዚህም አበረታች ውጤቶችንም እንደተገኙና ይህንንም ኢንስቲትዩቱ አጠናክሮ  እንደሚቀጥል የገለጹ ሲሆን፤ በተጨማሪም የባዮሴፍቲ እና የባዮሴኪዩሪቲ መርሃ ግብሮች በተለያዩ የጤና ላቦራቶሪዎች እየተተገበረ ሲሆን በአተገባበሩ ሂደት ውስጥ ብዙ ተግዳሮቶች ቢያጋጥሟቸውም የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ 16 ላቦራቶሪዎች በዚህ መርሃ ግብር እውቅና እንደሚሰጥ ገልጽው አያይዘውም በአገር አቀፍ ደረጃ የላቦራቶሪ አገልግሎትን ለማሻሻል የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስራዎች በመሰራታቸው ተጨባጭ ለውጦች እና አበረታች ማሻሻያዎች መመዝገባቸውን ገልጽዋል።
UKHSA ከኢንስቲትዩቱ ጋር በመተባበር በላቦራቶሪው ዘርፍ ያከናወናቸውን እና እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን በተመለከተ ዶ/ር ሳጂል ሊቃት በኢትዮጵያ የUKHSA ፕሮጀክት ኃላፊ ንግግር  ያደረጉ ሲሆን በተለይም UKHSA በዓለም አቀፍ የጤና ደንብ (International Health Regulation) ላይ  ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራ፤ የላቦራቶሪ ምርመራ አገልግሎቶችን ጥራት ለማሻሻል ለ10 ላቦራቶሪዎች የባዮሴፍቲ እና የባዮሴኪዩሪቲ መርሃ ግብሮችን ተግባራዊ ለማድረግ  ለተመረጡ 16  ላቦራቶሪዎች የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችንና ሌሎች ሙያዊ ድጋፍ ሲያደርግ እንደነበረ የገለጹ ሲሆን በቀጣይም መሰል ድጋፎችን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ቃል ገብተዋል::
በላፉት ሁለት ዓመታት የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከUKHSA ጋር በመተባበር ሲያከናውናቸው ለነበሩ ስራዎች እና ስለተገኘው ውጤትም አቶ ዳንኤል መለሰ የኢንስቲትዩቱ የላቦራቶሪ አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን ዝርዝር የተሰሩ ስራዎች እና የተገኙ ውጤቶች በተመለከተ በኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና በUKHSA ባለሙያዎች በጽሁፍ አቅርበው ቀጣይ የስራ አቅጣጫዎች ተሰጥቶባቸዋል፡፡
www.ephi.gov.et/news

13 last posts shown.