የጤና ላቦራቶሪ አገልግሎትን ጥራት በማስጠበቅ እና ባዮሴፍቲ እና ባዮሴኪዩሪቲ ስርዓቶችን ለተገበሩ የጤና ላቦራቶሪዎች የእውቅና እና የምስክር ወረቀት ተሰጠ።
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከUK Health Security Agency (UKHSA) ጋር በመተባበር ከተለያዩ ክልሎች ለተውጣጡ 10 የጤና ላቦራቶሪዎችን የላብራቶሪ ጥራት ስርአት ማሻሻያ ፕሮግራም (Strengthening Laboratory Management Towards Accreditation/SLIPTA/) እንዲሁም 16 ተጨማሪ በባዮ-ሴፍቲ እና ባዮ-ሴኪዩሪቲ ሰርተፍኬት ፕሮግራምን ለተገበሩ ላቦራቶሪዎች የእውቅና እና የምስክር ወረቀት የመስጠት ፕሮግራም በአዲስ አበባ ጥር 8/2017 ዓ.ም ተካሄደ። በፕሮግራሙም ላይ የUKHSA ሃላፊዎች እና ተወካዮች፣ የክልል የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና የክልል ላቦራቶሪዎች ሃላፊዎች፣ ከተመረጡ የጤና ተቋማት የመጡ የሆስፒታል ስራስኪያጆች እና የላቦራቶሪ ሃላፊዎች፣ የላቦራቶሪ ባለሙያዎች እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በዝግጅቱ ላይ ተሳትፈዋል።
በዝግጅቱ ላይ ተገኘተው የእንኳን ደህና መጣችሁና የመክፈቻ መልዕክት ያስተላለፉት የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሳሮ አብደላ እንደገለጹት የላቦራቶሪ ጥራት የማሻሻልና የአክሪዲትሽን ስራዎች ላይ የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የትኩረት አቅጣጫ (ፍላግ-ሽፕ) በመሆኑ በዚህ ዘርፍ እየተሰሩ ካሉ ስራዎች አንዱ ከUKHSA ጋር በመተባበር ባለፉት ዓመታት ከተለያዩ ክልሎች ለተመረጡ ላቦራቶሪዎች አስፈገላጊውን ድጋፍ እና ክትትል ኢንስቲትዩቱ ሲያደረግ እንደነበር እና በዚህም አበረታች ውጤቶችንም እንደተገኙና ይህንንም ኢንስቲትዩቱ አጠናክሮ እንደሚቀጥል የገለጹ ሲሆን፤ በተጨማሪም የባዮሴፍቲ እና የባዮሴኪዩሪቲ መርሃ ግብሮች በተለያዩ የጤና ላቦራቶሪዎች እየተተገበረ ሲሆን በአተገባበሩ ሂደት ውስጥ ብዙ ተግዳሮቶች ቢያጋጥሟቸውም የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ 16 ላቦራቶሪዎች በዚህ መርሃ ግብር እውቅና እንደሚሰጥ ገልጽው አያይዘውም በአገር አቀፍ ደረጃ የላቦራቶሪ አገልግሎትን ለማሻሻል የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስራዎች በመሰራታቸው ተጨባጭ ለውጦች እና አበረታች ማሻሻያዎች መመዝገባቸውን ገልጽዋል።
UKHSA ከኢንስቲትዩቱ ጋር በመተባበር በላቦራቶሪው ዘርፍ ያከናወናቸውን እና እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን በተመለከተ ዶ/ር ሳጂል ሊቃት በኢትዮጵያ የUKHSA ፕሮጀክት ኃላፊ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በተለይም UKHSA በዓለም አቀፍ የጤና ደንብ (International Health Regulation) ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራ፤ የላቦራቶሪ ምርመራ አገልግሎቶችን ጥራት ለማሻሻል ለ10 ላቦራቶሪዎች የባዮሴፍቲ እና የባዮሴኪዩሪቲ መርሃ ግብሮችን ተግባራዊ ለማድረግ ለተመረጡ 16 ላቦራቶሪዎች የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችንና ሌሎች ሙያዊ ድጋፍ ሲያደርግ እንደነበረ የገለጹ ሲሆን በቀጣይም መሰል ድጋፎችን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ቃል ገብተዋል::
በላፉት ሁለት ዓመታት የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከUKHSA ጋር በመተባበር ሲያከናውናቸው ለነበሩ ስራዎች እና ስለተገኘው ውጤትም አቶ ዳንኤል መለሰ የኢንስቲትዩቱ የላቦራቶሪ አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን ዝርዝር የተሰሩ ስራዎች እና የተገኙ ውጤቶች በተመለከተ በኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና በUKHSA ባለሙያዎች በጽሁፍ አቅርበው ቀጣይ የስራ አቅጣጫዎች ተሰጥቶባቸዋል፡፡
www.ephi.gov.et/news