📍ተከታይህ ከህሊና ድህነት አያድንህም፤ ሃብት ንብረትህ አስተሳሰብህን አይቀርፅም፤ ወዳጆችህ ውስጣዊ ሰላም አይሰጡህም። በእውነት ካልተመራህ፣ በስረዓት ማሰብ ካልቻልክ፣ ጥያቄህን ካልመረጥክ፣ ተግባርህን ካልቆጠብክ ጉዞህን እንጂ መውደቂያህን አታስተውልም፤ ጭብጨባውን እንጂ ስህተትህን አትረዳም፤ ድጋፍህ እንጂ ጥፋትህ አይገባህም።
አዕምሮህን ክፍት ማድረግህ ሚዛናዊ ማንነት እንዲኖርህ ያደርግሃል። መስማት የሚፈልግ ሰው ሁሉ ይሰማህ ይሆናል፤ የሚወድህም ይከተልህ ይሆናል፤ የሚያምንብህም እንዲሁ ሊያሽቃብጥልህ ይችላል። እውነታ በሌለበት ግን ማንም ሰው እስከመጨረሻው አብሮህ እንደማይቆይ እወቅ። ጥልቁ ማንነትህ እንጂ የያዝከው ጊዜያዊ ንብረትና ዝና ነፃ አያወጣህም።
🔷ስትታወቅና ከፊት ስትሆን በእውቀት እና በጥበብ ካልተጓዝክ ብዙ ነገር ታበላሻለህ፡፡ በሰዎች ሙገሳና አድናቆት በሞቅታ መስመር ትስታለህ፡፡ ዛሬ ላይ ሶሻል ሚዲያ ላይ ብዙ ተከታይ ለማግኘት ካሰብክ ካንተ ሚጠበቀው ለገንዘብ ተገዝተህ ወጣ ያለ አቋም መያዝ፣ ሌላ ፆታን ማራከስ፣ ሌላውን ብሄር በመጥፎ ማውገዝ ነው። ያኔ ማን ይሆን እሱ! እያለ ሁሉም ካለበት ቦታ እየሮጠ ይመጣልሃል።
♦️ወዲህ ግን ቁምነገር የሚጽፉ ተከታያቸው ጥቂት ብቻ የሆኑ ጠንካራ የማህበረሰብ አንቂዎች አሉ። ግና ሰው ስለራሱ ነውርና እንከን ለመስማት የሸሸበት የረሳበት ዘመን ላይ ነው ያለነው። ከዕውቀት ከጥበብ ይልቅ ስላቅና ፣ ዘለፋን ያስበለጠበት ዘመን ላይ እንገኛለን። እስቲ ይሄን ሥልጣኔ ያለንበትን ነገር በጥሞና ተመልከቱ። የዘመንኛው ቁሳዊ ሥልጣኔ ግኝቶችን ልብ እንበል። ዓለም ላለባት ችግር መፍትሔ ከመሻት ይልቅ፤ ግኝቶቹ ራሳቸው ከምንም የከፋ ችግር እየሆኑ እንዲያውም የቀደሙትን ችግሮች እስከማስረሳት ደርሰዋል። ግኝቶቹ ከሚያስከትሉት ጠንቅ ይልቅ በግኝቶቹ የሚገኘው ኃይል ገንዘብና ዝና ይበልጥ ትኩረት ተሰጥቶታል ።
🔑እናም ወዳጄ ቁምነገሩን ስንቅ አርግ
ዋናው ጉዳይ የሰው ክትትል ወይም ጭብጨባ አይደለም፤ ከፈጠረህ አምላክ አንፃር ትክክል ከሆንክ የፍጡራን ክትትል አያሳስብህ። ፊት መሆን በሚችል ስብዕና ከፊት ቁም፣ ጊዜህን አፍ በመካፈት አትብላው፣ አለምን የገዙ ፣ በአስተሳሰብ ሊቅነታቸው አርአያነታቸውን የምንከተላቸው ፈላስፎች ፣ ተመራማሪዎች፣ የህይወት መንገድ እያመቻቹልን እነሆ በዚህ ተጓዙ፣ ያኛው የብዝኋኑ መንገድ አሜኬላና እንቅፋት አለው። የዓለም ምስጢራት የሚገለጡት በስውር መስመር ነው እያሉ አመላክተውናል።
ለሰው ልጅ በተሰጠው ወንበር ላይ ቁጭ ብለን ሰው የመሆናችንን፣ ሰው የመባላችንን ልዩ ገፀ-በረከት የሚያጎናፅፉን ሀብቶቻችን እንከተል።
💡ህሊና ይፈርዳል፣ የእራሱን ብይንም ይሰጣል። ስለተጨበጨበልህ እውነት ተናግረሃል ማለት አይደለም፤ ተቃውሞ ስለበዛብህም ውሸት ተናግረሃል ማለት አይደለም። ለሁሉም ሰው የተሰጠው ህሊና የመንገድህ መሪ፣ የንግግርህ ቆንጣጭ፣ የተግባርህ አራሚ ነው። ለመፍረድ አትቸኩል፤ ለንግግር አትጣደፍ፤ እውነታውን በጥላቻህ አትሸፍን፤ በእውቅናህ ሰላምን አትግፋ፤ በተሰሚነትህ ክፍተትን አታስፋ። ውሸት የአብሮነት ምክንያት ሆኖ አያውቅም፤ ተንኮል ፍቅርን አንግሶ አያውቅም፤ ጥላቻም የሰላምን በር ከፍቶ አያውቅም።
♦️ሁሉን ያገኘህው በፈጣሪህ ሞገስ እንጂ አንተ አምጥተህው አይደለምና ለበጎ ተጠቀመው። እውነትን በፍቅር ያዝ፣ ለሰላም ግድ ይኑርህ፣ ለመከባበርም ቅድሚያ ስጥ። ትዕቢትን፣ ጉራን፣ ጀብደኝነትን፣ ጥቅመኝነትን ከውስጥህ አስወግደው የመልካምነትን ስብዕና ገንባ፣ ጥሩ መሪ ፣ ጥሩ ተከታይም ሁን።
ደርበብ ያለች ቅዳሚትን ተመኘን 😉
@Ethiohumanity
@EthioHumanity
✍ @EthioHumanitybot