📍ቡዳን እንዴት ማወቅ እንችላለን?
✍አሌክስ አብርሃም
♦️ሰሞኑን ስለቡዳ አብዝታችሁ ስታወሩ ነበር። ሁላችሁም ቡዳ ስለሚባል የሆነ ቦታ የሆነ ሰው ውስጥ ተደብቆ ሰወችን ስለሚበላ መንፈስ ነው "አለ የለም" ስትባባሉ የነበረው። መኖር አለ። እኔ የምላችሁ ግን... እናንተ ራሳችሁ ውስጥ የቡዳ መንፈስ እንደሌለ በምን እርግጠኛ ሆናችሁ? ለምን ምርመራውን ከራሳችሁ አትጀምሩም? ለማንኛውም የቡዳ መንፈስ እንዳለባችሁና እንደሌለባችሁ ለማወቅ የሚረዱ 5 ነጥቦችን ልንገራችሁ፤ ከዛ ((ቡዳ ፖዘቲቭ)) ወይም ((ቡዳ ኔጌቲቭ)) መሆናችሁን ራሳችሁ ወስኑ።
1ኛ:- ከምትወዱት ሰው ይልቅ የምትጠሉት ሰው ቁጥር ከበለጠ፣ ጥላቻችሁ በግል የማታውቁትን ሰው ከሆነ፣ ምንም ተበድላችሁ ሳይሆን ያ የጠላችሁት ሰው ቆንጆ፣ ሐብታም ወይም ታዋቂ፣ ወይም የተሳካለት ስለሆነ ብቻ ፀጉር የሚያስነጫችሁ ከሆነ ቡዳ ፖዘቲቭ ናችሁ።
2ኛ:- ሁልጊዜ ሰወችን የምትፈልጉት ለችግራችሁ ብቻ ከሆነና እናንተን ሲፈልጓችሁ የምትሸሹ፣ ችግር ውስጥ ሲገቡ እንደአቅማችሁ የማትረዷቸው ከሆነ ቡዳ ከነልጁ ውስጣችሁ ፈርሿል።
3ኛ:- የሶሻል ሚዲያ አጠቃቀማችሁን ፈትሹ፤ በተደጋጋሚ የምትገኙት ምናይነት ወሬ ላይ ነው? ተጋደሉ፣ ተፋቱ፣ ሚስቱ ከዳችው ባሏ ካዳት፣ ተጣሉ፣ ተለያዮ ተሰዳደቡ ዝምታቸውን ሰበሩ ወዘተ ላይ ከሆነ ቡዳ ውስጣችሁ ተቀምጦ አይናችሁን እንደመስኮት እየተጠቀመ ነው።
4ኛ:- ሀሜተኛ፣ አሽሙረኞች፣ የሰወችን ስም በሐሰት የምታጠፉ፣ አቃጣሪወች፣ ተንኮለኛና አድመኞች፣ ቀናተኞች፣ ትዕቢተኞች፣ ሰውን በመዝለፍ ለማሸማቀቅ የምትሞክሩ (((ፌክ አካውንት ያላችሁ))) የሰው ላይክ የምትቆጥሩ ከሆናችሁ፣ ሌሎች ሲደነቁ "እኔምኮ..." ብላችሁ የድሮ ዝናችሁን በሰው ክፍለጊዜ የምትዘንቁ ከሆ...ነ ቡዳ ጢባጢቤ እየተጫወተባችሁ፤ እንደፈረስም እየጋለባችሁ ነው።
5ኛ:- አካውንታችሁን ሎክ አድርጋችሁ ሌሎችን የምታዮ 😀 ይሄ ቀለል ያለው ነው ፤ አንዳንዴም ኮንፊደንስ ማጣት፣ ወይም ፀጉር ቤት እስከምትሄዱ ኤክሳችሁ ተጎሳቁላችሁ እንዳያያችሁ ከመፈለግ ሊሆን ይችላል። የሆነ ሁኖ የራሳችሁን ቆልፋችሁ ሌሎች መቆለፋቸው ካበሳጫችሁ ግን... 😀😀
💎መፍትሄ፦ ጨክናችሁ ከጥላቻ ውጡ። የሌሎች ውድቀት አያጓጓችሁ። ፍቅር ቡዳን አይነጋጃውን ነው የሚያጠፋው።
ውብ ዛሬ❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
✍ @EthioHumanityBot