#MekelleUniversity
በቅርቡ በትምህርት ሚኒስቴር ፀድቆ የተላከው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ወጥ-የሆነ የምግብ ሜኑ በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተግባራዊ መደረግ መጀመሩን ተከትሎ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ተቃውሞ አሰምተዋል፡፡
መቐለ ዩኒቨርሲቲ ከቅዳሜ ታህሳስ 12/2017 ዓ.ም ጀምሮ አንድ ዳቦ ለቁርስ እያቀረበ እንደሚገኝ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግረዋል። ከዚህ በፊት ዩኒቨርሲቲው መጠናቸው አነስተኛ የሆነ ሁለት ዳቦ ለቁርስ ያቀርብ እንደነበር ተማሪዎች አስታውሰዋል፡፡
"ዕለታዊ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የምግብ ተመን ወጪ አንድ መቶ ብር በሆነ ማግስት፥ አንድ ዳቦ ለቁርስ ማቅረብ ማሻሻል አይደለም" ሲሉ ተማሪዎቹ ቅሬታቸውን አቅርበዋል፡፡
ከታህሳስ 1/2017 ዓ.ም ጀምሮ የአንድ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ዕለታዊ የምግብ ወጪ ተመን ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) እንዲሆን መንግሥት መወሰኑ ይታወቃል። በዚህም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የምግብ ሜኑ በሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወጥነት እንዲኖረው ለማድረግ ተመሳሳይ የምግብ ሜኑ በትምህርት ሚኒስቴር ተዘጋጅቶ ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ተልኳል፡፡
መቐለ ዩኒቨርሲቲ ከተቋሙ የተማሪዎች ህብረት ጋር በመነጋገር የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች የምግብ ሜኑን አዘጋጅቶ ወደ ትግበራ መግባቱን ገልጿል። (አዱሱ የዩኒቨርሲቲው ሜኑ ከላይ ተያይዟል)
በማሻሻያውና በቀረበው የዳቦ መጠን ላይ ደስተኛ ያልሆኑ የዋናው ግቢ እና የዓዲ ሓቂ ግቢ ተማሪዎች ድርጊቱን በመቃወማቸው ለድብደባ እና ለእስር መዳረጋቸውን ገልፀዋል።
የክልሉ ፓሊስ ኮሚሽን ወደ ካምፓሶቹ የፀጥታ አካላት መላኩ ተነግሯል። በፓሊስ እና በተማሪዎቹ መካከል በተፈጠረ ግጭት ተማሪዎች የድብደባ ጥቃት እንደደረሰባቸው ተነግሯል። በዋናው ግቢ የተማሪዎች መመገቢያ አዳራሽ ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን፤ ይህንንም ተከትሎ የታሰሩ ተማሪዎች መኖራቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በሁለቱ ካምፓሶች የተፈጠረው ግርግር በአሁኑ ሰዓት ሙሉ በሙሉ መቆሙ ታውቋል።
ዩኒቨርሲቲው ባወጣው መግለጫ "በምግብ ሜኑው ላይ የሚስተካከሉ ነገሮች ካሉ ብሔራዊ ሜኑ በይዘት እና በጀት ደረጃ እስካልተለየ ድረስ ጥያቄዎች በተማሪዎች ህብረት በኩል ቀርበው ማስተካከል እንደሚቻል" ገልጿል፡፡ ተማሪዎች ቅሬታቸውን በሰላማዊ መንገድ መግለፅ እንዳለባቸውም ጠቁሟል፡፡
ከሚመለከተው የማኔጅመንት አካላት ጋር ውይይት መጀመሩን የገለፀው የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሀብረት፤ "ያለአግባብ የታሰሩ ተማሪዎች እንዲፈቱና ያለ በቂ መረጃ በተማሪዎች ላይ እርምጃ እንዳይወሰድ" ጠይቋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው ያዘጋጀው አዲሱ የምግብ ሜኑ ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ እስከሚሆን ድረስ ነባሩ ሜኑ እንዲቀጥልም ህብረቱ ጥሪ አድርጓል፡፡
መቐለ ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረው ጉዳይ ላይ ይፋዊ መግለጫ እንደሚሰጥ ይጠበቃል፡፡