ውሸትን ፍለጋ
══✘══
✍ ዮፍታሔ ካሳ
'
ለማይጠረቃ ሥጋ፣
ምሽቱ እንዳይነጋ፣
ሰርክ ድካም፣ ውሸትን ፍለጋ።
ውሸት! ውሸት!
የህላዌ ካስማ፣ የኑሮ መሠረት፣
የመዛለቅ ዋርካ፣ ያብሮነት መቀነት።
ኦ ውሸት .....!
የፍቅራችን የሳር አክሊል፣
የቃላችን የቅብ ተክሊል።
የሰላማችን የጭድ ፋና፣
ያልጠና ነፍስ ጉተና።
ኦ ውሸት .....!
የመከባበራችን የሸንበቆ ዋልታ፣
ይድረስሽ ከንቱ ውዳሴ ከጽልመትሽ ቦታ።
ኦ ውሸት !
═══════
📔 በአራጣ የተያዘ ጭን
🗓 2010 ዓ.ም.
📖 📖 📖 📖 📖
https://t.me/Ethiobooks
══✘══
✍ ዮፍታሔ ካሳ
'
ለማይጠረቃ ሥጋ፣
ምሽቱ እንዳይነጋ፣
ሰርክ ድካም፣ ውሸትን ፍለጋ።
ውሸት! ውሸት!
የህላዌ ካስማ፣ የኑሮ መሠረት፣
የመዛለቅ ዋርካ፣ ያብሮነት መቀነት።
ኦ ውሸት .....!
የፍቅራችን የሳር አክሊል፣
የቃላችን የቅብ ተክሊል።
የሰላማችን የጭድ ፋና፣
ያልጠና ነፍስ ጉተና።
ኦ ውሸት .....!
የመከባበራችን የሸንበቆ ዋልታ፣
ይድረስሽ ከንቱ ውዳሴ ከጽልመትሽ ቦታ።
ኦ ውሸት !
═══════
📔 በአራጣ የተያዘ ጭን
🗓 2010 ዓ.ም.
📖 📖 📖 📖 📖
https://t.me/Ethiobooks