አቤቱ፥ የሚያስጨንቁኝ ምንኛ በዙ! በኔ ላይ የሚቆሙት ብዙ ናቸው። ብዙ ሰዎች ነፍሴን። አምላክሽ አያድንሽም አልዋት።አንተ ግን አቤቱ፥ መጠጊያዬ ነህ፥ ክብሬንና ራሴንም ከፍ ከፍ የምታደርገው አንተ ነህ። በቃሌ ወደ እግዚአብሔር እጮሃለሁ ከተቀደሰ ተራራውም ይሰማኛል።እኔ ተኛሁ አንቀላፋሁም እግዚአብሔርም ደግፎኛልና ነቃሁ። ከሚከብቡኝ ከአእላፍ ሕዝብ አልፈራም። ተነሥ፥ አቤቱ፤ አምላኬ ሆይ፥ አድነኝ፤ አንተ የጠላቶቼን መንጋጋ መትተሃልና፥ የክፉዎችንም ጥርስ ሰብረሃልና።ማዳን የእግዚአብሔር ነው፥ በረከትህም በሕዝብህ ላይ ነው።መዝሙረ ዳዊት ምዕ. 3 ቁ1-8
🥀እንዴት ዋላችሁ 🤲☦🧎♀
🥀እንዴት ዋላችሁ 🤲☦🧎♀