አርሴማን ጥሩልኝ🥺
ክፍል ፲፪
በቃ ዝም ብሎ ስቅስቅ እያሉ ማልቀስ መንገዱ ረዘመብኝ ግን በቃ አንዳንድ ጊዜ የእማማ እና የልጇ ንግግር ተስፋ እየሰጠኝ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ መለየትን ሳስብ እየጨነቀኝ ሆስፒታል ደረስኩኝ ግን አሁን ሞተው ባገኛቸውስ… ብቻ ብዙ መጥፎ ሀሳቦች ጭንቅላቴን ሞልተውት ወደ ክፍላቸው ገባሁና እማማ የነገሩኝን አንድም ሳላስቀር አንድ በአንድ ነገርኳቸው ልጄ ወይኔ አባዬ የእውነትህን ነው ብሎ በደስታ ሳቀ ባለቤቴም እንባዋ እንደ ክረምት ጅረት በጉንጮቿ ፈሰሱ እና ምን ይሻላል ስላቸው ልጃችን ምንም ተስፋ የላትም አለቀላት የተባለችውን ልጅ ከደረሰችላት ለእኛ ትንሽም ቢሆን ተስፋ የተሰጠንን የተበጠሰውን የህይወት መንገዳችንን አትቀጥልም አትፈውሰንም ብሎ ማውራት አርሴማን አባዬ በግመል ቀዳዳ ግመል ያልፋል ብሎ ከመናገር አይተናነስም ደግሞም ልጅቷ ልክ ነች ከሞትንም እዛው አርሴማ ደጅ ታቦቱ በወጣበት ዕለት አፈር ልልበስ አለ እናትም አዎ ልጄ ትክክል ነው የእውነት ከሰው ሃገር ሄጄ በሬሳ ሳጥን ከምመጣ እዚሁ በእናቴ ደጅ ነፍሴ ከስጋዬ ትለይ አለችኝ ግራ ገባኝ ምን ልሁን እና ምን ይሻላል ስላቸው ልጄ ሁለት አልጋ መግፋት ስለሌለብህ እኔን ወደ እማዬ አልጋ ውሰደኝና አሁኑኑ ከዚህ አውጣን አለኝ እኔ ደስ አላለኝም እና በቃ አይሆንም ለህክምና ከሀገር መውጣት አለባችሁ አልኩኝ ባለቤቴ በፍፁም አይሆንም የኔ አዳም በህይወቴ በትዳር ዘመናችን ያስቀየምኩህ አይመስለኝም አስቀይሜህ ከሆነም ይቅር በለኝ አለችኝ እንባዋ እየፈሰሰ አንቺ እኮ እንኳን እኔን ይቅርና ነፍሳት የማታስቀይሚ ልዩ ስጦታዬ ነሽ ጥሩ የእውነት ከልብህ ከሆነ ዛሬ አሁኑኑ ከዚህ ሆስፒታል አስወጥተህ ለቡ አርሴማ ውሰደኝ አለችኝ የምገባበት ጠፋኝ ምናባቴ ላድርግ ምን አድርጌ ራሴን ላጥፋ ምጥ ሆነብኝ…
ይቀጥላል
✍ብርሃኑ ባውቄ