ጾም የሥጋ ረሀብ አይደለም፤ የነፍስ ምግብ እንጂ። አንዳንድ ሰዎች እንደሚያስቡት ጾም የሥጋ ሥቃይ ሰማዕትነት ወይም መስቀል አይደለም፤ ሥጋ ከነፍስ ጋር የሚተባበርበት ደረጃ ላይ ለመድረስ ከፍ ከፍ የሚልበት እንጂ። ስንጾም የመጾማችን ዕቅድ ሥጋችንን ለማንገላታት አይደለም፤ ጠባዩን ለመግራት እንጂ። ይህ በመሆኑም አንድ የሚጾም ሰው መንፈሳዊ እንጂ ሥጋዊ ሰው አይሆንም ማለት ነው።
ጾም መናኝ ነፍስ ስለሆነ በምናኔ ውስጥ ያለ ባልንጀራ ሥጋውን ይዞ ይጓዛል እንጂ፤ ብቻውን አይጓዝም። ጾም ማለት የተራበ ሥጋ ማለት አይደለም የመነነ ሥጋ እንጂ። ጾም የሥጋ ረሀብ አይደለም የሥጋ ልዕልና እና ንጽህና እንጂ ለመብላት የሚናፍቅ የሚራብ ሰውነት ያለበት ሁኔታ ማለትም አይደለም፤ መብላት ዋጋውን የሚያጣበትና ሰውነት ለመብላት ካለው ፍላጎት ራሱን የሚያላቅቅበት ሁኔታ እንጂ።
አቡነ ሺኖዳ