ኢትዮ ኘላስ + Ethio Plus


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


በኢትዮጵያ እና ከኢትዮጵያ ባሻገር ያሉ መረጃዎች እና ሃሳብ የሚቀርብበት ቻናል ነው።
አለምአቀፋዊ እይታ እና ግንዛቤን በመረጃ እናሳድግ!
#Diplomacy #International #Politics #Science #Culture #Sport #Art

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


እስራኤል 118 ፍልስጤማውያን እስረኞችን ትለቃለች
-------------

የሃገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር ዛሬ እንዳስታወቀው ቅዳሜ እለት 118 ፍልስጤማውያን እስረኞችን እስራኤል እንደምትለቅ ዛሬ አስታውቋል።

በአንፃሩ ሃማስ ሶስት የእስራኤል ታጋቾችን እንደሚፈታ ታውቋል።

ከሚፈቱት እስረኞች መካከል እድሜ ልክ እስር ተፈርዶባቸው የነበሩ ፍልስጤማውያን እንደሚገኙ ተገልጿል።


የጀነራል አልቡርሃን ሰራዊት የካርቱምን አብዛኛውን አካባቢ ደግም ተቆጣጠረ
------
በጄነራል አብዱልፈታ አልቡርሃን የሚመራው የሱዳን ሰራዊት ባለፉት ከንድ አመት ውስጥ ከፍተኛ የተባለ ድል በተፋላሚው የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሃይል ላይ በዚህ ሳምንት ውስጥ ተቀናጅቷል።

የሱዳን ሰራዊት በሳምንቱ ውስጥ በሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሃይል ቁጥጥር ውስጥ የነበረውን የዋና ከተማ ካርቱምን አብዛኛውን ክፍል መቆጣጠሩ ተገልጿል።

የአበዱልፈታ አልቡርሃን ሰራዊት ከሳምንታት በፊት ቁልፍ የሆነውን የጀዚራ ግዛት ከተቆጣጠረ ወዲህ ወደፊት ግስጋሴውን ቀጥሎ የበላይነትን እየተቀናጀ ነው።

የካርቱም ነዋሪዎች ለቢቢሲ እንደገለፁት በአሁኑ ወቅት የካርቱም አብዛኛው ክፍሎች ዳግም በሱዳን ሰራዊት እጅ የገቡ ሲሆን የጀነራል ሃምዳን ደጋሎ ወታደሮች አፈግፍገው በከተማዋ ዳርቻ ላይ እንደሚገኙ ገልፀዋል።

ባለፈው ማክሰኞ ሰራዊታቸው እያገኘ ያለውን ድል አስመልክቶ ጀነራል አብዱልፈታ አልቡርሃን በሰጡት መግለጫ ካርቱም በቅርቡ ሙሉ ለሙሉ ከአማፂያን ትፀዳለች ብለዋል።


ከተሞከሩባቸው የግድያ ሙከራዎች በኋላ ወደ ሃይማኖት መቅረባቸውን ትረምፕ ተናገሩ
--------

ዛሬ በዓመታዊው ‘ብሔራዊ የፀሎትና የቁርስ ሥነ ሥርዐት’ ላይ የተገኙት የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ፣ ከተፈጸመባቸው ሁለት የግድያ ሙከራዎች በኋላ ከሃይማኖት ጋራ ያላቸው ግንኙነት እንደተቀየረ አስታውቀዋል።

አሜሪካዊያን “ፈጣሪን መልሠው በሕይወታቸው ውስጥ ያኑሩ” ሲሉ ጥሪ አድርገዋል ትረምፕ።

በካፒቶል የሚካሄደውና የሰባ ዓመታት ዕድሜ ያስቆጠረው ዓመታዊ የፀሎትና የቁርስ ሥነ ሥርዐት የሁለቱም ፓርቲዎች የምክር ቤት ዓባላት የሚሳተፉበት ሃይማኖታዊ ሥነ ስርዓት ነው።


የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽ በግማሽ ዓመቱ ከእቅድ በላይ 2.6 ቢሊየን ብር ገቢ ማገኘቱን አስታወቀ
----------------


ኮርፖሬሽኑ በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የተቋሙን ስኬት ቀጣይነት ያረጋገጡ ስኬታማ ሥራዎች መሰራታቸውን ባካሄደው የአፈጻጸም ግምገማ አረጋግጧል፡፡

በግማሽ ዓመቱ 2 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ገቢ ለማግኘት የታቀደ ቢሆንም ከ2 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተገኝቷል፡፡

ገቢውም ከኮሪደር ልማት ጋር ተያይዞ ኮርፖሬሽኑ ከፍተኛ ገቢ የሚያገኝባቸው ቤቶች በመልሶ ማልማት አካል በመሆናቸው የተቋሙ ገቢ ያሽቆለቁላል የሚለውን ስጋት የቀረፈ የገቢ እድገት ነው፡፡

ኮርፖሬሽኑ በመልሶ ማልማት ያጣውን ገቢ ለማካካስ በፍጥነት ተጨማሪ ሱቆችን በመስራት እና ሌሎች የገቢ ማስገኛ አማራጮችን በማከናወን በግማሽ ዓመቱ ከፍተኛ የገቢ እድገትና ተጨማሪ ከ 1 በሊየን ብር በላይ አሴት እንዲፈጠር ያስቻለ ውጤታማ ሥራ መሰራቱም ተጠቁሟል፡፡

በገቢ እድገትና ጤናማ የፋይናንስ ሥርዓት ከመፍጠር አኳያ የተሰራው ሥራ የኮርፖሬሽኑን የለውጥ ጉዞ አስተማማኝ እንዲሆን እያደረገ መሆኑን ነው የተገመገመው፡፡

ኮርፖሬሽኑ በራሱ አቅም ግዙፍ የቤት ግንባታ ፕሮጀክቶችን ለመገንባት የሚያስችል አቅም መፍጠር መቻሉም በጥንካሬ ተግምግሟል፡፡

ተቋሙ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ንጹህ የኦዲት አስተያያት ማግኘት መቻሉም በግምገማው ተነሰቷል፡፡ ይህም ዘመናዊ የፋይናንስ ሥርዓት ዝርጋታው የደረሰበትን ደረጃ የሚያሳይ ነው፡፡

ወጪ ቆጣቢ አካሄድን ተግባራዊ በማደረግ ረገድና የገቢ አማራጮችን ከማስፋት አንጻርም ውጤታማ ስራዎች መሰራታቸው ነው በግምገማው የተመለካተው፡፡

በግማሽ ዓመቱ የምስራቅ አጠቃላይ፣ ኮከበ ጽብሃና ግዙፍ የግብዓት ማምረቻ ማዕከል ተመርቆ ለአገልግሎት መብቃት መቻሉ የኮርፖሬሽኑ በላቀ አፈጻጸም ላይ እንዳለ የሚያሳይ መሆኑን ተገምግሟል።

በዚህ ስኬትን ለማጽትና ለማስቀጠል በተሰሩ አንኳር ሥራዎች ላይ ትኩረት ያደረገውን ግምገማ የመሩት የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር ረሻድ ከማል ተጨማሪ የአፈጻጸም አቅጣጫም ሰጥተዋል፡፡

አገራዊ ፋይዳው የላቀ ትእምርት ባለው የኮሪደር ልማት፣ ኮርፖሬሽኑ እያደረገ ያለውን ተሳትፎ በተጠናከረ ሁኔታ ለማስቀጠል የሚያስችል አቅጣጫም ተቀምጧል፡፡

የኮሪደር ልማቱ ይዞት የመጣውን እድል በአግባቡ በመጠቀም በሚቻልበት ሁኔታ ውይይትና የአፈጻጸም አቅጣጫ ተሰጥቷል፡፡

ኮርፖሬሽኑ ገንብቶ ለማስረከብ ውል የገባበቸውን ግዙፍ አገራዊ ፕሮጀክቶችን ግንባታቸውን በጊዜ ገንብቶ ለማጠናቀቅ በልዩ ሁኔታ ክትትልና ድጋፍ እንደሚያደርግ ተገልጿል፡፡

የበርካታ ተቋማትን የአብረን እንስራ ጥያቄ ለመመለስ የሚያስችል ያልተቋረጠ የአቅም ግንባታ ሥራ መሰራት እንደለበት በግምገማው አጽንኦት ተሰጥቶበታል፡፡


የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽ በግማሽ ዓመቱ ከእቅድ በላይ 2.6 ቢሊየን ብር ገቢ ማገኘቱን አስታወቀ
----------------


ተዋጊውን ኤም 23 የሚደግፍ ትዕይንተ ህዝብ በጎማ ከተማ ተካሄደ
---------
ከኮንጎ መንግስት ጋር እያደረገ ባለው ውጊያ የምስራቅ ኮንጎ ኪቩ ግዛት ዋና ከተማ የሆነውን ጎማ ለተቆጣጠረው ኤም 23 ተዋጊ ሃይል ያለውን ድጋፍ የከተማው ህዝብ አደባባይ በመውጣት ዛሬ ገልጿል።

ተዋጊ ቡድኑ ጎማን ከተቆጣጠረ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በተካሄደው ሰልፍ በሺዎች የሚቆጠር ህዝብ በውጣት ደጋፉን ሲገልፅ ውሏል።

በስፍራው በመገኘት ለህዝቡ ንግግር ያደረጉት የተዋጊው ቡድን መሪ ኮርኒየል ናጋ ዋና ከተማዋን ነፃ እስክትወጣ ውጊውን እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

በኮንጎ እየተካሄደ በሚገኘው ውጊያ በጎማ ብቻ እስካሁን ከ3 ሺህ በላይ ሰዎች ህይታቸውን አጥተዋል።


ለአለምአቀፍ መረጃዎች ቻናላችንን ተመራጭ ያድርጉ 👇👇

https://t.me/Ethioplus_s


ፍልስጥኤማዉያን ጋዛን እንዲለቁ የሚያስችል ዕቅድ እንዲነድፍ ታዘዘ
-----------
ትዕዛዙ የተላለፈው በእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ ነው።

የሚንስትሩ ትዕዛዝ የተሰማው የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የጋዛ ሰርጥን ለመቆጣጠር እንደሚፈልጉ ካስታወቁ በኋላ ዓለማቀፍ ተቃዉሞ እየተሰማ ባለበት ወቅት ነው።

የመከላከያ ሚንስትሩ እስራኤል ካትዝ፣ ትራምፕ ከ2 ሚሊዮን በላይ ፍልስጥኤማዉያን የሚኖሩባትን ጋዛን ለመቆጣጠር ማቀዳቸውን አድንቀዋል።

"የፕሬዚደንቱን በድፍረት የተሞላ ዕቅድ በደስታ እንቀበላለን ፤ በየትኛውም ዓለም እንደሚሆነው የጋዛ ነዋሪዎች ከመኖሪያቸዉ በነጻነት መውጣት እና መሰደድ ሊፈቀድላቸው ይገባል » ብለዋል።

ሚንስትሩ ፍልስጥኤማዉያኑ በየብስ ፣ በባህር አለያም በአየር እንደምርጫቸው ከጋዛ መውጣት እንዲችሉ አማራጮች ማዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል።

የአረብ እና የአውሮጳ ህብረት አባል ሃገራትን ጨምሮ በርካታ ሃገራት የፍልስጥኤማዉያኑን ከሃገራቸው እንዲሰደዱ በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የቀረበውን ሃሳብ ተቃዉመዋል።

የፍልስጥኤም አስተዳደር ፕሬዚዳንት መሐሙድ አባስ በበኩላቸው የአሜሪካውን ፕሬዚዳንት ዕቅድ በይፋ ውድቅ ባደረጉበት መግለጫቸው ።

" ህጋዊ የፍልስጥኤማዉያን መብቶች ለድርድር አይቀርቡም" … ሃሳቡም " ከባድ የመብት ጥሰት ነው " ብለውታል።

የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬሽ በበኩላቸው“የፍልስጤም ሕዝብ በገዛ ምድራቸው እንደሰው የመኖር የማይገሰስ መብቶች» እንዳላቸው አጽንዖት ሰጥተዋል።


ሁለቱ ባለ አርባዎች

በ40 አመት እድሜያቸው ዛሬም ብቃት ላይ የሚገኙት ሁለቱ ገናናዎች።

ክርስቲያኖ ሮናደልዶ እና ሊብሮን ጀምስ ❤


በአል ናስር እና በሎስአንጀለስ ሌከርስ ዛሬም ስራቸው ላይ ናቸው !

ዛሬም በድል መንገድ ላይ እየተጓዙ ነው!!


በሶማሊያ በሚገኘው የአይሲስ ክንፍ ላይ የሚካሄደው ዘመቻ ተጠናክሮ ቀጥሏል
------------

ለአንድ ወር ያህል የፑንትላንድ የፀጥታ ኅይሎች በእስላማዊ መንግሥት ተዋጊዎች መደበቂያ ምሽጎች ላይ እርምጃቸውን አጠናክረው የቀጠሉ ሲሆን፣ በቅርቡ ቱርማሳሌ በተሰኘው ቁልፍ ሥፍራ የተደረገው ከባድ ግጭት ተጠቃሽ ነው።

በሁለቱም ወገኖች ላይ ጉዳት ቢደርስም፣ የፑንትላንድ ኅይሎች በርካታ ሥፍራዎችን በመቆጣጠር የበላይነት አግኝተዋል ተብሏል።

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ባለፈው ቅዳሜ በሶማሊያ በሚገኙ አንድ ከፍተኛ የእስላማዊ መንግሥት ጥቃት አቀናባሪና በሌሎቹም የቡድኑ ዓባላት ላይ ወታደራዊ የአየር ጥቃት እንዲፈፀም አዘዋል።

የአየር ጥቃቶቹ በጎሊስ ተራራማ ቦታዎች ላይ መደረጋቸውንና በሲቪሎች ላይ ጉዳት እንዳልደረሰም የአሜሪካው የመከላከያ ምኒስትር ፒት ሄግሴት አስታውቀዋል።

የሮይተርስ ዜና ወኪል ዝርዝር ጉዳዮችን በተመለከተ ከገለልተኛ ወገኖች ማረጋገጥ እንዳልቻለ አስታውቋል።

ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉና በሶማሊያ ፕሬዝደንታዊ ጽ/ቤት የሚገኙ አንድ ባለሥልጣን የአየር ጥቃቶቹ መፈፀማቸውን አረጋግጠው፣ የሶማሊያ መንግሥት እርምጃውን በመልካም እንደሚቀበለው አስታውቀዋል።

አሜሪካ ለበርካታ ዓመታት በሪፐብሊካኑም ሆነ በዲሞክራቶቹ የአስተዳደር ዘመኖች ሶማሊያ ውስጥ የአየር ጥቃት ስትፈፅም ቆይታለች፡፡


ትራምኘ የመጀመሪያውን መሪ በኋይት ሃውስ ዛሬ ተቀበሉ
--------

ትረምፕ በጋዛው የተኩስ አቁም ስምምነት ሂደት ዙሪያ ለመነጋገር ዛሬ ኔታንያሁን በዋይት ሀውስ ተቀብለው ያነጋግራሉ

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁን ዛሬ ማክሰኞ በዋይት ሀውስ ተቀብለው ያነጋግራሉ።

የሁለቱ መሪዎች ንግግር የመጣው ጋዛ ውስጥ የቀሩት ታጋቾች በሙሉ መለቀቅን፣ የውጊያው ሙሉ በሙሉ በቋሚነት መቆምን እና የእስራኤልን ኃይሎች ከጋዛ ተጠቃሎ መውጣት ጨምሮ በእስራኤል እና በሃማስ መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም ከወሳኝ ምዕራፍ በደረሰበት ወቅት ነው።

እስራኤል እና ሃማስ በደረሱት ስምምነት መሰረት የውላቸውን ሁለተኛው ዙር አፈጻጸም ተግባራዊ ለማድረግ ከአራት ሳምንታት ያነሰ ጊዜ ነው የቀረው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ “ሰላሙ ስለመያዙ የምሰጠው ዋስትና የለም” ሲሉ ትረምፕ ሰኞ ዕለት ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።


የጤና ሚኒስትር በሲዲሲ እና ዩኤስኤአይዲ የበጀት ድጋፍ የተቀጠሩ ሠራተኞችን ዉል ማቋረጡን አስታወቀ
----------

ከ 5 ቀን በፊት ለሁሉም መንግስታዊ የጤና ቢሮ በተፃፈው ደብዳቤ እንደተገለፀዉ በጤና ሚኒስቴር ድጋፍ ከዩኤስኤአይዲ እና ሲዲሲ ጋር በተደረገው ውል በኮንትራት የተቀጠሩ ሠራተኞች ዉል መቋረጡን እና ይህን ዉሳኔ እንዲያስፈፅሙ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

ሚኒስትሩ ለዚህ እርምጃ የደረሰዉ ከአሜሪካ መንግሥት በ "ሲዲሲ" ወይም "ዩኤስኤአይዲ" አማካይነት በተገኘ የበጀት ድጋፍየ የሚከናወን ማንኛውም ስራም ሆነ ክፍያ ከየካቲት 17 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እንዲቋረጥ ማሳሰቢያ ስለደረሰዉ እንደሆነ ካፒታል ጋዜጣ ዘግቧል።


ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በሀገር ዉስጥ ገንዘብ ለመገበያየት መስማማታቸው ተሰማ
----

ሩሲያ ኢትዮጵያን ጨምሮ ናይጄሪያን እና ቱኒዚያን በሰሜን እስያዊቷ ሀገር ውስጥ በገንዘብ ለመገበያየት ከተፈቀደላቸው አገሮች ዝርዝር ውስጥ አካታለች።

ሀገራቱ ከሩሲያ ጋር በሚፈጽሙት ግብይት የሚያጋጥማቸውን የውጭ ምንዛሪ እጥረት ለመቅረፍ እና የተሻለ የንግድ ግንኙነት ለመፍጠር እንደሚያግዝ ተገልጿል ።

የዩክሬኑን ጦርነት ተከትሎ ከተለያዩ ሀገራት ጋር ከዶላር ውጭ የሆነ ግብይት ለመፈጸም ስምምነቶችን እያደረገች የምትገኝው ሞስኮ ተጨማሪ ሶስት የአፍሪካ ሀገራትን የተቀበለችው ከሰሞኑ ነዉ።

ስፑትኒክ እንደዘገበዉ የሩሲያ መንግስት እንደገለጸው ይህ መመሪያ የሩሲያ ኢኮኖሚ በመገበያያ ገንዘብ የሚከፈለዉን ፍላጎት ለማሟላት እንዲረዳ እንዲሁም የወዳጅ እና ገለልተኛ መንግስታትን የብሔራዊ ገንዘቦችን በቀጥታ ለመለዋወጥ የሚያስችለውን ስርዓት ውጤታማነት እንደሚያረጋግጥ አስረድተዋል ።

ከሁለት አመት በፊት በዚህ ዝርዝር ውስጥ የነበሩ አገሮች ቁጥር 30 የነበረ ሲሆን አሁን ግን ከሩሲያ ጋር በሀገር ውስጥ ገንዘብ ለመገበያየት ስምምነት ላይ የደረሱ ሀገራት ቁጥር 40 ደርሷል ይላል ካፒታል ጋዜጣ ያዘጣው መረጃ ፡፡


ትረምፕ የካናዳን እና የሜክሲኮን መሪዎችን ሊነጋገሩ ነው
-----------

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ ከሁለቱ ጎረቤቶቻቸው ካናዳ እና ሜክሲኮ፣ እንዲሁም ከቻይና በሚገቡ ምርቶች ላይ አዲስ ቀረጥ ከጣሉ እና በምላሹ ሁለቱ አገሮች በዩናይትድ ስቴትስ ላይ የአጻፋ ቀረጥ መጣላቸውን ይፋ ካደረጉ በኋላ ከመሪዎቹ ጋር ለመነጋገር ማቀዳቸውን አመለከቱ።

ትረምፕ በመጀመሪያው የሥልጣን ዘመናቸው ከካናዳ እና ሜክሲኮ ጋር ተደራድረው ‘ነጻ-የንግግድ ስምምነት’ ተግባራዊ ቢያደርጉም፤ ከነገ ማክሰኞ አንስቶ ተፈጻሚ የሚሆን አዲስ የሃያ አምስት በመቶ ቀረጥ ሲጥሉባቸው፤ በቻይና ላይ ደግሞ ቀደም ሲል ከተደነገገው በተጨማሪ የአሥር በመቶ ቀረጥ ጥለዋል።

ትረምፕ ሕገ-ወጥ ፍልሰትን ለማስቆም እና ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ለብዙዎች ህልፈት ምክኒያት የሆነው ‘ፌንቲኔል’ የተባለ አደገኛ መድሃኒት ወደ አሜሪካ እንዳይገባ ለመከላከል በቂ ጥረት አላደረጉም’ ሲሉ ሦስቱን ሃገራት ከሰዋል።


የፓናማ መንግስት የቻይናን ተፅዕኖ ካልቀነስ አሜሪካ እርምጃ እንደምትወስድ ማርኮ ሩቢዮ አስጠነቀቁ
------------
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ከፓናማ ኘሬዝደንት ዦዜ ማኑዌል ሙሊኖ ጋር ፊት ለፊት ተገናኝተዋል።

ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ለኘሬዝደንቱ ቀጭን ማስጠንቀቂያን እንዲህ ሲሉ ሰጥተዋል።

" ሃገርዎት በፓናማ አካባቢ እያደገ የመጣውን የቻይና ተፅዕኖ የግድ መግታት አለባት። ያ የማይሆን ከሆነ የትራምኘ አስተዳደር አስፈላጊ የተባለውን ሁሉ እርምጃ ይወስዳል"

ኘሬዝደንት ትራምኘ ከአለማችን ዋንኛ የባህር መተላለፊያ መስመሮች አንዱ በሆነው የፓናማ ካናል የአሜሪካ የንግድ መርከቦች በአግባቡ እየተስተናገዱ አይደለም ፣ ከፍተኛ ታሪፍ እየተጠየቁ ነው ከማለት ጀምረው ወሳኙ ስፍራ የአሜሪካ ነው እስከማለት መድረሳቸው ይታወቃል።

ዛሬ ደግሞ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸው በከል የፓናማ መንግስት ከቻይና ይልቅ እኛን ለመጥቀም ካልፈቀደ ሃይልን ጨምሮ አስፈላጊ እርምጃን መንግስታቸው ለመውሰድ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል ።

ማርኮ ሩቢዮ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከሆኑ በኋላ የመጀመሪያ ጉብኝታቸውን ዛሬ በፓናማ የጀመሩ ሲሆን በቀጣይ ቀናት ወደ ኤል ሳልቫዶር ፣ ኒካራጓ ፣ ጓቲማላ እና ዶሚኒካ ሪፐብሊክ ያመራሉ።


ሶስት የአውሮፓ ታላላቅ ክለቦች ከርዋንዳ ጋር ያላቸውን የማስታወቂያ ውል እንዲያቋርጡ ኮንጎ ጠየቀች
----------

አርሰናል ፣ ባየር ሙኒክ እና ፓሪሰን ዠርሜን ከሩዋንዳ ጋር ያላቸውን የማስታወቂያ የስፓንሰርሺኘ ውል እንዲያቋርጡ ተጠየቀ።

ጥያቄውን ያቀረበው የኮንጎ መንግስት ነው።

ሩዋንዳ ምስራቃዊ ኮንጎን የተቆጣጠረውን ኤም 23 ትደግፋለች የሚል ክስ የሚያቀርበው የኮንጎ መንገስት ፥ ሶስቱ ክለቦች ርዋንዳን ጎብኙ " Visit Rwanda " በሚል የገቡትን የማስታወቂያ ውል እንዲያቋርጡ ጠይቋል።

የኮንጎ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቴርሴ ኪያዋምባ ዋግነር ለሶስቱ ክለቦች በፃፉት ደብዳቤ ኮንጎ እያቀረበች ያለው የሞራል ጥያቄ ነው በማለት ገልፀዋል።

ሚኒስትሩ በደብዳቤያቸው ርዋንዳ በእርስ በርስ ጦርነት እና የዘር ግጭት የተበላሸ ገፅታዋን ለመገንባት ቪሲት ርዋንዳ በሚል ከሶስቱ ክለቦች ጋር የገባችውን ስፓንሰርሺኘ የምትከፍለው በህገወጥ መንገድ በተገኘ ገንዘብ ነው ብለዋል።

ርዋንዳ የምታስታጥቀው ኤም 23 ታጣቂ ቡድን ከተቆጣጠራቸው የምስራቅ ኮንጎ አካባቢዎች የሚገኙ ውድ ማዕድናትን ወደ ሃገሯ በመውሰድ ወደ ተለያዩ ሃገራት እየላከች ከፍተኛ ገንዘብ እያገኘች መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ሰላማዊ ዜጎችን እየፈናቀለ እና ሺዎችን እየቀጠፈ ከሚገኘው የኮንጎ ግጭት በሚሰበሰብ ገንዘብ ሶስቱ ክለቦች ርዋንዳን ማስተዋወቃቸው የሞራል ጥያቄን ያስነሳል ብለዋል።


ካናዳ የአፀፋ እርምጃ በአሜሪካ ላይ እንደምትወስድ አስታወቀች
---------
ከካናዳ ወደ አሜሪካ የሚገቡ ምርቶች ላይ የ25% አዲስ የቀረጥ ታሪፍ እንዲጣል ዶናልድ ትራምኘ ውሳኔ ማሳለፋቸውን ተከትሎ የካናዳ መንግስት ቁጣውን እያሰማ ነው።

ወዳጅ በሚሏት አሜሪካ መካዳት እንደተፈፀመባቸው የካናዳ ባለስልጣናት እየገለፁ ይገኛል።

የትራምኘ ውሳኔ የሃገራቱን ግንኙነት እንደሚያሻክር ሲገለፅ የነበረ ሲሆን ዛሬ የጀስቲን ቱሩዶ መንግስት ካናዳ በተመሳሳይ ከአሜሪካ የሚገቡ ምርቶች ላይ 25% ታሪፍ እንደምትጥል አስታውቀዋል።

ይህም 155 ቢሊየን ዶላር በሚገመቱ ምርቶች ላይ ተፈፃሚ እንደሚሆን ተገልጿል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ቱሩዶ በውሳኔው ዙሪያ ዛሬ ካቢኔያቸውን የሚሰበስቡ ሲሆን ሌሎች ተጨማሪ ውሴኔዎችን ያሳልፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ተመሳሳይ የ25% ታሪፍ ወደ አሜሪካ በምትልካቸው ምርቶች ላይ የተጣለባት ሜክሲኮም የኋይት ሃውስን ውሳኔ ፍፁም ተገቢ ያልሆነ እና አጋርነትን ያላገናዘበ ስትል ተቃውማዋለች።

ትራምኘ ግልፅ የንግድ ጦርነት አውጀውብናል ብለዋል ሜክሲኳውያኑ።


ትራምኘ ሶማሊያ ውስጥ ይገኛሉ በተባሉ የአይሲስ አመራሮች ላይ የአየር ጥቃት እንዲፈፀም ትዕዛዝ ሰጡ
------
ኘሬዝደንት ዶናልድ ትራምኘ የአሜሪካ አየር ሃይል በሶማሊያ በሚገኙ የአይሲስ ሽብር ቡድን አባላት ላይ የአየር ጥቃት እንዲፈፀም ዛሬ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል።

ኘሬዝደንቱ በኤክስ ገፃቸው ላይ እንዳስታወቁት በሶማሊያ በመሸጉ የአይሲስ ሽብር ቡድን ከፍተኛ አመራርን ኢላማ ያደረገ የአየር ጥቃት ትዕዛዝ ሰጥቻለሁ ብለዋል።

ኘሬዝደንት ትራምኘ የጥቃቱ ኢላማ የትኛው አመራር እንደሆነ በስም አልጠቀሱም።

ኘሬዝደንቱ የሽብር ቡድኑ መሪዎች በሶማሊያ ዋሻዎች ውስጥ ተሸሽገው እንደሚገኙ የተጠቀሱ ሲሆን ፥ ከአጋሮቻችን ጋር በመሆን እናጠፋቸዋለን ብለዋል።


የፈረንሳይ ጦር ሰራዊት ከቻድ ሙሉ ለሙሉ ወጣ
---------
የፈረንሳይ ኃይሎች ከምዕራብ አፍሪካዊቷ ቻድ ሙሉ ለሙሉ ለቀው ወጥተው መጨረሳቸውን የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ማሃማት ኢድርስ በደስታ ተቀብለውታል።

ይህም ፈረንሳይ ጂሃዲስት ታጣቂዎች በስፋት ከሚንቀሳቀሱበት የአፍሪካ ሳህል ቀጠና የመውጣቷ ሂደት የመጨረሻው ምዕራፍ ነው ተብሏል።

ከአንድ ቀን በፊት በዋና ከተማው ን'ጃሚና በዝግ በተካሄደ ወታደራዊ ስነስርዓት ዴቢ ለቻድ ኃይሎች እና ዲፕሎማቶች ንግግር ያደረጉ ሲሆን፣ ፈረንሳይ በመካከለኛው አፍሪካውቷ ሀገር የነበራትን የመጨረሻ የጦር ሰፈር አስረክባለች።

ቻድም ከቀድሞ ቅኝ ገዢዋ ጋር የነበራትን ወታደራዊ ትብብር ሙሉ ለሙሉ አቋርጣለች።


ኪንሻሳን እስኪቆጣጠሩ ሰራዊታቸው ግስጋሴውን እንደመያቆም የኤም 23 ዋና አዛዥ አስታውቁ
----------

ያልተጠበቁ ክስተቶችን እያስተናገደ በሚገኘው የኮንጎ ውጊያ ኤም 23 በዚህ ሳምንት ወሳኝ የሆነውን የሰሜን ኪቩ ግዛት ዋና ከተማ ጎማን ሙሉ ለሙሉ በእጁ ማስገባቱ ይታወቃል።

ዛሬ ደግሞ ማጥቃቱን በመቀጠል በምስራቃዊ ኮንጎ የደቡብ ኪቩ ግዛት ዋና ከተማ ቡካቩን ለመቆጣጠር ጫፍ ላይ መድረሳቸው ተገልጿል።

ሁለቱ ግዛቶች ኤም 23 ከተመሰረተ ጀምሮ መሰረት አድርጎ የሚንቀሳቀስባቸው ሲሆን ከፍተኛ የማዕድን ሃብት ክምችት ያለባቸው ናቸው።

ድሉን ተከትሎ የኤም 23 ታጣቂ ሃይል መሪ ኮኒየል ናጋ በሰጡት መግለጫ " ሰራዊታችን ወደ ዋና ከተማ ኪንሻሳ መገስገሱን ይቀጥላል፥ ካንሻሳን ሳንቆጣጠር ወደፊት የምናደርገው ግስጋሴ አይቆምም " ብለዋል።

የሃገሪቱን መንግስት ማስወገድ የትግላቸው የመጨረሻ እና ዋንኛ ግብ እንደሆነም መሪው አስታውቀዋል።

በብዙ አካባቢዎች የኮንጎ መንግስት ሰራዊት አባላት የውጊያ አቅማቸው ተዳክሞ በቀላሉ ቁልፍ ስፍራዎችን ለተፋላሚ ቡድኑ እያስረከቡ መሆኑ እየታየ ነው።

ኤ 23 ራሱን ጭቆናን ለማስወገድ የሚዋጋ የኘፃነት ሃይል አድርጎ ይገልፃል። ሆኖም ግን ብዙዎች በምስራቅ ኮንጎ የሚገኘውን የማዕድን ሃብት ለመቆጣጠር እና የኮንጎን መንግሰት ለማስወገድ በርዋንዳ የሚደገፍ ቡድን እንደሆነ ይገልፁታል።

ርዋንዳ ይህን ውንጀላ በፅኑ ትቃወማለች።


ሰነድ አልባ ስደተኞች ወደ ጓንታናሞ ቤይ እንደሚልኩ ትራምኘ ትዕዛዝ አስተላለፉ
----------

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ሰነድ አልባ ስደተኞችን ኪዩባ በሚገኘው ጓንታናሞ ቤይ እንዲያዙ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል።

ለዚህም አስተዳደራቸው እስር ቤቱን ዝግጁ እንዲያደርግ የሚያስችል ሰነድ እንደፈረሙም ታውቋል።

በኪዩባ የሚገኘው የአሜሪካ እስር ቤት፣ ጓንታናሞ ቤይ፤ ወታደራዊ እስረኞችን፣ የታሊባንና የመስከረም 11 የሽብር ጥቃት ተጠርጣሪዎችን በመያዙ ይታወቃል።

የመከላከያ እና የሃገር ውስጥ ደህንነት መሥሪያ ቤቶች እስር ቤቱ 30 ሺሕ ስደተኞችን ለማስተናገድ እንዲችል ዝግጅት እንዲያደርጉም ትረምፕ አዘዋል።

20 last posts shown.