ኢትዮ ኘላስ + Ethio Plus


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


በኢትዮጵያ እና ከኢትዮጵያ ባሻገር ያሉ መረጃዎች እና ሃሳብ የሚቀርብበት ቻናል ነው።
አለምአቀፋዊ እይታ እና ግንዛቤን በመረጃ እናሳድግ!
#Diplomacy #International #Politics #Science #Culture #Sport #Art

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


የፈረንሳይ ጦር ሰራዊት ከቻድ ሙሉ ለሙሉ ወጣ
---------
የፈረንሳይ ኃይሎች ከምዕራብ አፍሪካዊቷ ቻድ ሙሉ ለሙሉ ለቀው ወጥተው መጨረሳቸውን የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ማሃማት ኢድርስ በደስታ ተቀብለውታል።

ይህም ፈረንሳይ ጂሃዲስት ታጣቂዎች በስፋት ከሚንቀሳቀሱበት የአፍሪካ ሳህል ቀጠና የመውጣቷ ሂደት የመጨረሻው ምዕራፍ ነው ተብሏል።

ከአንድ ቀን በፊት በዋና ከተማው ን'ጃሚና በዝግ በተካሄደ ወታደራዊ ስነስርዓት ዴቢ ለቻድ ኃይሎች እና ዲፕሎማቶች ንግግር ያደረጉ ሲሆን፣ ፈረንሳይ በመካከለኛው አፍሪካውቷ ሀገር የነበራትን የመጨረሻ የጦር ሰፈር አስረክባለች።

ቻድም ከቀድሞ ቅኝ ገዢዋ ጋር የነበራትን ወታደራዊ ትብብር ሙሉ ለሙሉ አቋርጣለች።


ኪንሻሳን እስኪቆጣጠሩ ሰራዊታቸው ግስጋሴውን እንደመያቆም የኤም 23 ዋና አዛዥ አስታውቁ
----------

ያልተጠበቁ ክስተቶችን እያስተናገደ በሚገኘው የኮንጎ ውጊያ ኤም 23 በዚህ ሳምንት ወሳኝ የሆነውን የሰሜን ኪቩ ግዛት ዋና ከተማ ጎማን ሙሉ ለሙሉ በእጁ ማስገባቱ ይታወቃል።

ዛሬ ደግሞ ማጥቃቱን በመቀጠል በምስራቃዊ ኮንጎ የደቡብ ኪቩ ግዛት ዋና ከተማ ቡካቩን ለመቆጣጠር ጫፍ ላይ መድረሳቸው ተገልጿል።

ሁለቱ ግዛቶች ኤም 23 ከተመሰረተ ጀምሮ መሰረት አድርጎ የሚንቀሳቀስባቸው ሲሆን ከፍተኛ የማዕድን ሃብት ክምችት ያለባቸው ናቸው።

ድሉን ተከትሎ የኤም 23 ታጣቂ ሃይል መሪ ኮኒየል ናጋ በሰጡት መግለጫ " ሰራዊታችን ወደ ዋና ከተማ ኪንሻሳ መገስገሱን ይቀጥላል፥ ካንሻሳን ሳንቆጣጠር ወደፊት የምናደርገው ግስጋሴ አይቆምም " ብለዋል።

የሃገሪቱን መንግስት ማስወገድ የትግላቸው የመጨረሻ እና ዋንኛ ግብ እንደሆነም መሪው አስታውቀዋል።

በብዙ አካባቢዎች የኮንጎ መንግስት ሰራዊት አባላት የውጊያ አቅማቸው ተዳክሞ በቀላሉ ቁልፍ ስፍራዎችን ለተፋላሚ ቡድኑ እያስረከቡ መሆኑ እየታየ ነው።

ኤ 23 ራሱን ጭቆናን ለማስወገድ የሚዋጋ የኘፃነት ሃይል አድርጎ ይገልፃል። ሆኖም ግን ብዙዎች በምስራቅ ኮንጎ የሚገኘውን የማዕድን ሃብት ለመቆጣጠር እና የኮንጎን መንግሰት ለማስወገድ በርዋንዳ የሚደገፍ ቡድን እንደሆነ ይገልፁታል።

ርዋንዳ ይህን ውንጀላ በፅኑ ትቃወማለች።


ሰነድ አልባ ስደተኞች ወደ ጓንታናሞ ቤይ እንደሚልኩ ትራምኘ ትዕዛዝ አስተላለፉ
----------

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ሰነድ አልባ ስደተኞችን ኪዩባ በሚገኘው ጓንታናሞ ቤይ እንዲያዙ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል።

ለዚህም አስተዳደራቸው እስር ቤቱን ዝግጁ እንዲያደርግ የሚያስችል ሰነድ እንደፈረሙም ታውቋል።

በኪዩባ የሚገኘው የአሜሪካ እስር ቤት፣ ጓንታናሞ ቤይ፤ ወታደራዊ እስረኞችን፣ የታሊባንና የመስከረም 11 የሽብር ጥቃት ተጠርጣሪዎችን በመያዙ ይታወቃል።

የመከላከያ እና የሃገር ውስጥ ደህንነት መሥሪያ ቤቶች እስር ቤቱ 30 ሺሕ ስደተኞችን ለማስተናገድ እንዲችል ዝግጅት እንዲያደርጉም ትረምፕ አዘዋል።


ሶስተኛ ተከታታይ ድል

ማንችስተር ዩናይትድ በምሽቱ የዩሮፓ ሊግ ጨዋታ ስቴዋ ቡካሬስትን ከሜዳው ውጭ 2ለ0 አሸንፏል


ቅዱስ ቁርዐን ያቃጠለው ግለሰብ ተገደለ
--------------

በስዊድን ቁርዓን በማቃጠሉ ከፍተኛ ተቃውሞ ያስነሳው ግለሰብ በጥይት ተመትቶ ተገደለ።

የ38 ዓመቱ ሳልዋን ሞሚካ ረቡዕ ማምሻውን በስቶክሆልም በሚገኝ አንድ አፓርታማ ውስጥ መገደሉ ተዘግቧል።

ሳልዋን የእስልምና እምነት ቅዱስ መጽሃፍ የሆነውን ቁርዓንን በስቶክሆልም በሚገኝ መስጊድ ውጭ ከሁለት ዓመት በፊት ማቃጠሉን ተከትሎ ከፍተኛ ቁጣና ተቃውሞ ተፈጥሮ ነበር።

የስቶክሆልም ፖሊስ ባወጣው መግለጫ በ40ዎቹ ዕድሜ የሚገኝ አንድ ግለሰብ ሌሊት በተተኮሰበት ጥይት መገደሉን ተከትሎ አምስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቋል።


ሶማሌላንድ እና አረብ ኤምሬት ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማሙ
----------

ከሁለት ወር በፊት የተካሄደውን የሶማሌላንድ ምርጫ በማሸነፍ የሃገሪቱ መሪ የሆኑት ኘሬዝደንት አብዱረህማን አይሮ የሶስት ቀናት ጉብኝት በአረብኤምሬት አድርገው ዛሬ ወደ ሃርጌሳ ተመልሰዋል።

ኘሬዝደንት አብዱረህማን የመጀመሪያቸው በሆነው የውጭ ሃገር ጉብኝት ከአረብኤምሬት ኘሬዝደንት መሃመድ ቢንዛይድ ጋር በአቡዳቢ ተገናኝተው መክረዋል።

ጉብኝቱን አስመልክቶ የሶማሌላንድ ውጭ ጉዳይ ባወጣው መግለጫ ሁለቱ ሃገራት ግንኙነታቸው በግበርና ፣ በመሰረተ ልማት ፣ በሃይል እና ማዕድን ዘርፍ ለማጠናከር የሚያስችል ስምምነቶችን አድርገዋል።

ጉብኝቱ ስትራቴጂካዊ ግንኙነታቸውን ወደ ከፍተኛ ደረጃ ለማድረስ የሚያሰችል እና አረብ ኤምሬትስ በሶማሌላንድ የምታደርገውን ኢንቬስትመንት ለማሳደግ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ እንደሆነም በመግለጫው ተጠቅሷል።

አረብ ኤምሬትስ ከራስ ገዟ ሶማሌላንድ ጋር ጠንካራ ግንኙነት ካላቸው ሃገራት ቀዳሚዋ ስትሆን በበርካታ ዘርፎች መዋዕለ ነዋይዋን እያፈሰሰች እንደሚገኝ ይታወቃል።


https://t.me/Ethioplus_s


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
በዋሽንግተን አየር ማረፊያ አቅራቢያ ትላንት ምሽት ሄሊኮኘተር የመንገደኞች አውሮኘላንን ሲጋጩ የተቀረፀ ተንቀሳቃሽ ምስል ☝️☝️

በግጭቱ አውሮኘላኑ ተቃጥሎ ወንዝም ውስጥ የወደቀ ሲሆን ያሳፈራቸው 60 መንገደኞች ህይወት ማለፉ እየተነገረ ነው።


የ60 ሰዎች ህይወት ማለፉ ታውቋል
--------------

በአሜሪካ በደረሰ የአውሮፕላን መከስከስ አደጋ ከ60 በላይ ሰዎች መሞታቸው ተነግሯል።

በዋሽንግተን ዲሲ አደጋው ሊደርስ የቻለው የመንገደኞች አዉሮፕላን ለማረፍ በሚሞክርበት ጊዜ ሔሊኮፕተር ጋር ተላትሞ አውሮፕላኑ ወንዝ ውስጥ በመከስከሱ ነው።

በአደጋው ከሞቱት ውስጥ የሩስያ አትሌቶች እንደሚገኙባቸው ታውቋል።

የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች እስከ አሁን የ28 ሰዎችን አስከሬን ማግኘታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።


ፀረ ኢትዮጵያው ሴናተር የ11 ዓመት እስራት ተፈረደባቸው
-----------
በኢትዮጵያ ላይ ጫና እንዲደረግ የግብፅን ጥቅም ለማስጠበቅ ጉቦ የተቀበሉት የቀድሞው የኒው ጀርዚ ሴናተር ቦብ ሜኔንዴዝ የ11 ዓመት እስራት ተፈርዶባቸዋል።

ቦብ ሜንዴዝ የግብፅን ጥቅም ለማስጠበቅ የተለያዩ ጥሬ ገንዘቦችን እና የዓይነት ጉቦ መቀባላቸው በመረጋገጡ ነው እስራቱ የተፈረደባቸው፡፡

በከፍተኛ ደረጃ የአሜሪካን ሕዝብ ከወከለ እንደሳቸው ዓይነት ካለ ሰው በማይጠበቅ መልኩ ሌላ ሀገርን በመርዳት 16 ክሶች የቀረቡባቸው ሜንዴዝ፣ ይህም ቢያንስ 15 ዓመታት ሊያስፈርድባቸው እንደሚገባ ዐቃቤ ሕግ ክርክር አቅርቦ እንደነበር የቢቢሲ መረጃ ያመላክታል፡፡

በተለይም ከግብፅ መንግሥት የተቀበሏቸው ጥፍጥፍ ወርቆች፣ ጥሬ ገንዘብ እና መርሴዲስ ቤንዝ መኪና ለወንጀላቸው ማረጋገጫ ተደርገው ለፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡

ሜንዴዝ በጠበቃቸው በኩል ቀለል ያለ የማኅበራዊ አገልግሎት ቅጣት እንዲጣልባቸው ቢጠይቁም ፍርድ ቤቱ ግን የ11 ዓመታት ጽኑ እስራት ፈርዶባቸዋል፡፡

በተያያዘም ሜንዴዝን ከግብፅ መንግሥት ጋር በማገናኘት ወንጀል የተሳተፈ ዋኤል ሃና የተባለ ግብጻዊ-አሜሪካዊ ነጋዴም ከስምንት ዓመት በላይ እስራት እና የ1.25 ሚሊየን ዶላር ቅጣት ተወስኖበታል።


የእባብ አመት ፥ ቻይናውያን እያከበሩት የሚገኘው አዲስ አመት
---------
የቻይና የሉናር አዲስ ዓመት እየተከበረ ነው። በዓሉ በብዙ የእስያ አገሮች እና በዓለም ዙሪያ ባሉ ዜጎቻቸው የሚከበር ጥልቅ በዓል ነው ፡፡

የቻይና ዘመን መለወጫ በዓል የፀደይ ፌስቲቫል ተብሎም የሚጠራ ሲሆን በዚህ ዓመት በቻይናውያን የቀን መቁጠሪያ መሰረት በዛሬው እለት እየተከበረ ይገኛል፡፡ በዓሉም ለቀጣይ ሁለት ሳምንታት የሚቆይ ነው፡፡

የቻይናውያን አዲስ አመት በ12 አመት ውስጥ የሚሽከረከርና በቻይና ኮከብ ቆጠራ ስርዓት ውስጥ ካለው እንስሳ ጋር የሚዛመድ ሲሆን ከአምስት ንጥረ ነገሮች ማለትም ከብረት፣ እንጨት፣ውሃ፣እሳት እና ከመሬት ጋር የተጣመረ ነው፡፡ የዘንድሮ አዲስ ዓመትም የእንጨት እባብ ዓመት ተብሎ እየተከበረ ይገኛል፡፡

የዘመን መለወጫ በዓሉ አመጣጥ በቻይና ቢሆንም እንደ ማሌዥያ፣ ፊሊፒንስ እና ሲንጋፖር ባሉ ሀገራት ያሉ የቻይና ማህበረሰቦች በተመሳሳይ ስም እና ተመሳሳይ ሁነቶች ያከብሩታል ፡፡ እንደ ቬትናም እና ኮሪያ ያሉ ሀገራትም የሉናር አዲስ ዓመትን ስሙን በመቀየር ያከብራሉ፡፡

ቻይናውያን አዲስ ዓመት ከመግባቱ ቀደም ብለው ባሉ ቀናት ያለፈው ዓመት መጥፎ ዕድል ለማባረር በሚል ቤቶቻቸውን በማጽዳት ያሳልፋሉ።

ይህ ጽዳት ለቀጣዩ አመት መልካም እድል እንደሚያመጣ የሚታመን ሲሆን በጌጣጌጦች ፣ መብራቶች፣ በተቆራረጡ ወረቀቶች እና በደማቅ ቀይ ቀለም ቤቶቻቸውን በማስዋብ መልካም እድልን ለማምጣት ይሞክራሩሉ፡፡
በአዲሱ ዓመት ዋዜማም ከቤተሰብ አባላት ጋር እራት በመብላት ያሳልፋሉ፡፡

የአዲሱ ዓመት የመጀመሪያ ቀን ሲገባ አንግ ፓኦ ወይም ሆንግ ባኦ የሚባል ስርዓት የሚከናወን ሲሆን ይህም የቤተሰብ አባላት እና ጓደቾች በአንድ ተሰብስበው የተለያዩ ስጦታዎችን የሚሰጣጡበት ነው ፡፡

የቻይና ተወላጅ የሆነው ኢቮን ጎህ እንደሚለው ፤ አንዳንዶች በመጀመሪያዎቹ ቀናት ቤታቸውን ከመጥረግ ፣ ፀጉራቸውን እና ጥፍሮቻቸውን ከመቁረጥ ይቆጠባሉ፡፡ ይህን የሚያደርጉትም በአዲስ ዓመት የተገኘውን መልካም እድል እንዳያጡ በመፍራት ነው ሲል ይገጻል፡፡

መልካም እድልን የሚጋብዙ እና እርኩሳን መናፍስትን ከቤት እና ከስራ ቦታ የሚያርቁ ባህላዊ የአንበሳ ጭፈራዎችን ማከናወንም የበዓሉ አንዱ አካል ናቸው።

በተለምዶ ያገቡ ሴቶች የቻይና አዲስ አመት የመጀመሪያ ቀንን ከአማቶቻቸው ጋር እንዲያሳልፉ የሚደረግ ሲሆን በሁለተኛው ቀን ደግሞ ሴት ልጆች ወላጆቻቸውን እንዲጎበኙ ይደረጋል።

ሶስተኛው ቀን ፀጥ ያለ እንዲሆን እና በእረፍት እንዲያልፍ ከተደረገ በኋላ አራተኛው እና አምስተኛው ቀን ግን ለሀብት አምላክ የተሰጡ መሆናቸው ይነገራል ፡፡ ስድስተኛው ቀን ላይም ሰዎች ያረጁ ወይም ያልተፈለጉ ዕቃዎችን ጥለው ወደ ሥራ እንዲገቡ ሲደረግ በሰባተኛው ቀን የቻይና እናት አምላክ የሆነችው ኑዋ ሰዎችን እንደፈጠረች ይታመናል ሲል የዘገበው ቢቢሲ ነው።


የእባብ አመት፥ ቻይናውያን እያከበሩት የሚገኘው አዲስ አመት
---------


አሜሪካ ለምትኖሩ የስደተኞች አፈሳና መመለስን በተመለከተ እነኚህ ነጥቦች እወቁ
-----------
በዲሲና በአካባቢዋና በሌሎችም የአሜሪካ ከተሞች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ በተለይም የመኖርያ ፍቃድ የሌላቸውና ህጋዊ ሂደት ውስጥ ያሉት ጭምር በሰፊው እየተወሰደ ባለው የስደተኞች አፈሳና መመለስ (Deportation) ጋ ተያይዞ በቂ መረጃ አለማግኘት፣ ጭንቀትና ስጋት ውስጥ ወድቀዋል። የተለያዩ የኢትዮጵያ የንግድ ተቋማት፣ ሬስቶራንቶች፣ ገበያወች ውስጥ የሚሰሩትም በፍርሃት በመዋጣቸው ከቤት አለመውጣትን መርጠዋል።

በዚህ መነሻነት፣ ጉዳዩ ያስጨነቃችሁ አሜሪካ የምትኖሩ የማህበረሰባችን አባላት በመረጃ ላይ የተመሰረተ ጥንቃቄ ታደርጉ ዘንድ፣ የልዩ ፕሬዝዳንታዊ (Executive Order) ትዕዛዙንና አፈጻጸሙን አገላብጬና የህግ ባለሞያወችን አናግሬ ያገኘሁትን መረጃ ባጭሩ እነሆ።
የዚህ ዘመቻ ዋና ኢላማወች፦
👉 በአሜሪካ ስርዓት ውስጥ ያልተመዘገቡ (Undocumented)፣ በህጋዊ መንገድ ለመቆየት የሚያበቃ መረጃና ፍቃድ የሌላቸው፣ በየትኛውም የስደተኝነት ወይም የጥገኝነት ማመልከቻ ሂደት ውስጥ የሌሉ፣
👉 የጥገኝነት ማመልከቻቸው በሁሉም የማመልከት ሂደቶችና ደረጃወች ላይ ውድቅ ተደርጎ በስደተኞች ፍርድ ቤት ሃገር እንዲለቁ (Removal Order) የታዘዙ
👉 በየትኛውም የጥገኝነት ማመልከቻ ሂደት ውስጥ ያሉ፣ እንዲሁም የስራ፣ የትምህርትም ሆነ የጉብኝት ቪዛ ያላቸው ቢሆኑም በወንጀል የተከሰሱ፣ የተፈረደባቸው፣ የተጠረጠሩ ወይም የወንጀል ታሪክ ያላቸው ከሆነ ለዚህ የአፈሳ ተዕዛዝ የተጋለጡ ናቸው።

ይሄ ዘመቻ የማይመለከታቸው፦
🔻 ህጋዊ ነዋሪወች፤ የመኖርያ ፈቃድ (Green Card) ያላቸው ሰወች ከሃገር የሚያስባርር ወንጀል እስካልፈጸሙ ድረስ
🔻 ቀኑ ያላለፈ ቪዛ ያላቸው፤ የተማሪ፣ የስራ፣ የጉብኝት ቪዛ ያላቸው እና በቪዛው ላይ ያለውን የመቆያ ጊዜና ደንብ/ ግዴታ ያከበሩ
🔻ጥገኝነት (Asylum) ያመለከቱ ጉዳያቸው በየትኛውም ደረጃም ላይ ቢሆን በሂደት ላይ ያለ፣ የስራ ፈቃድ ያላቸው እና ምንም አይነት የወንጀል ታሪክ የሌላቸው

ይሄ ጉዳይ የሚመለከታቸው ሰወች ማደረግ ያለባቸው፦
🔶 የስደተኛ ጉዳይ አስፈጻሚ ሃይሎች የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ካልያዙ በስተቀር የቤታችሁን በር ያለመክፈት መብት አላችሁ
🔶 በቁጥጥር ስር ቢውሉም ለማንኛውም ጥያቄ መልስ አለመስጠት እና ጠበቃ የመጠየቅ መብት አላችሁ
🔶 ከቦት ቦት ሲንቀሳቀሱ መታወቂያ እና የህጋዊነት መኖርያ ፈቃድ ወይም የማመልከቻ ደረሰኝና ማስረጃወች መያዝ
🔶 ለክፉም ለደጉም የአደጋ ጊዜ እቅድ ማውጣት፣ የአስፈላጊ የቤተሰብ ተጠሪወችንና የህግ ባለሞያወችን ስልክ መያዝ
🔶 በማመልከቻ ሂደት ላይ ያላችሁ ከጠበቆቻችሁ ጋ መማከር፣ ማመለከቻችሁ ያለበትን ደረጃ በሚገባ ማወቅ፣ የፍርድ ቤት አልያም የቃለመጠይቅ ቀጠሮወችን አለማሳለፍ
✅ የወንጀል ክስ ወይም ታሪክ ካለ የህግ ድጋፍ መፈለግ
✅ ከመጨነቅ ይልቅ ተረጋግቶ ህጋዊ መሰረት ካላቸው እና ከታመኑ ምንጮች ብቻ ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃወችን ማግኘት

ይሄ መረጃ ግንዛቤን ለማስፋት የቀረበ እንጂ የህግ ባለሞያን ምክር የሚተካ አለመሆኑን ከወዲሁ መግለጽ እወዳለሁ። መደረግ ያለባቸው ጥንቃቄወች ሁሉም ሰው እንዳለበት ሁኔታ የሚወሰኑና የሚለያዩ ስለሆኑ ራስን መጠበቅ፣ በእውቀት ላይ የተመሰረተ በቂ መረጃ ላይ መመርኮዝ እና፣ ሁል ጊዜም ቢሆን ህጋዊ ድጋፍን ማግኘት አስፈላጊና ጠቃሚ ነው።
በአበቀ ፈለቀ
#Ethiopia


አሜሪካ ለምትኖሩ የስደተኞች አፈሳና መመለስን በተመለከተ እነኚህ ነጥቦች እወቁ
-------------


የኢትዮጵያ ወዳጅ የሆኑት ዲኘሎማት የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትር ሆኑ
---------
👉 ሹመቱ ኤርትራን አበሳጭቷል

ለኢትዮጵያ ወዳጅ ናቸው የሚባሉት አምባሳደር ቲቦር ናዢ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ የአስተዳደር ጉዳዮች ዘርፍ ተቀዳሚ ምክትል ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል።

ሹመቱ ከምክትል ሚኒስትር ቀጥሎ በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥ ቁልፍ እና ከፍተኛ ከሆኑ የስልጣን እርከኖች አንዱ ነው።

ቲቦር ናዢ የተሰጣቸው ስልጣን ዋንኛ ሃላፊነት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤትን በጀት ፣ የሰው ሃይል እና ንብረትን መምራት እና መስተዳደር እንደሆነ ታውቋል።

እንዲሁም የእለት ተዕለት ስራዎችን ማስፈፀም ፣ እቅዶችን መከታተል እና የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን አሰራር እና ሪፎርም የመምራት ሃላፊነትም የእርሳቸው ነው።

ቲቦር ናዢ ለኢትዮጵያ ቀና አመለካከት አላቸው ከሚባሉ የአሜሪካ አንጋፋ ዲኘሎማቶች መካከል አንዱ ናቸው።

በአንፃሩ የኤርትራ መንግስትን አምርረው የሚቃወሙ ሲሆን ፥ የኢሳያስን አስተዳደር " አምባገነን እና ፀረ ዲሞክራሲ" መሆኑን በአደባባይ የሚኮንኑ ናቸው።

በኤርትራ የስርዐት ለውጥ እንዲኖር የሚያቀነቅኑም ናቸው።

በአፍሪካ በተለይ በአፍሪካ ቀንድ ቀጠና የካበተ ልምድ ያላቸው አምባሳደር ቲቦር ናዢ የሶማሌላንድን ነፃ ሃገር መሆን በቀዳሚነት ይደግፋሉ።

አዲሱ የአሜሪካ አስተዳደር ለሶማሌላንድ ነፃ ሃገርነት እውቅና መሰጠት አለበት የሚል አቋማቸው ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በስፋት ሲያሰሙ ተደምጠዋል።

በቀጠናው ላይ ባላቸው አመለካከት መነሻነት ሹመታቸው ኢትዮጵያን እና ሶማሌላንድን የሚያስደሰት በአንፃሩ ኤርትራን ያስደነገጠ ሆኗል እየተባለ ነው።


ሰኞ ከሦስት መቶ ሺህ በላይ ፍልስጥኤማዊያን ተፈናቃዮች ወደጋዛ ተመለሱ
----------
በእስራኤል እና በሐማስ ጦርነት የተፈናቀሉ ከሦስት መቶ ሺህ የሚበልጡ ፍልስጥኤማዊያን ተፈናቃዮች ትላንት ሰኞ ወደ ሰሜናዊ ጋዛ መመለሳቸውን በሐማስ የሚመራው የጋዛ ሰርጥ መንግሥት ባለስልጣናት ተናገሩ።

ተፈናቃዮቹ የተመለሱት እስራኤል የፍተሻ ኬላዎቹን ከፍታ እንዲመለሱ መፍቀዷን ተከትሎ ነው።

ፍልስጥኤማዊያኑ አብዛኞቹ በእግራቸው የቻሉትን ያህል ዕቃ ተሸክመው ጦርነቱ እንደተጀመረ ጥለውት ወደሸሹት እና ይኑር ይፍረስ ወደማያውቁት የቀድሞ መኖሪያቸው ተጉዘዋል።

እስራኤል የሐማስ ታጣቂዎችን እና ፈንጂ ያጠመዱባቸውን ህንጻዎች ዒላማ አድርጋ ባደረሰችው የቦምብ ድብደባ አብዛኛው አካባቢ ወድሟል።

እስራኤል እ አ አ በ2023 ጥቅምት ውስጥ ጥቃቱን እንደጀመረች ወደአንድ ሚሊዮን የሚሆኑ ነዋሪዎች ከሰሜናዊ ጋዛ እንዲወጡ ማዘዟ ይታወሳል።

ከተኩስ አቁም ስምምነቱ በኋላ ዳግም መመለስ ጀምረዋል።


የአሜሪካ እርዳታ መቆም!
------------
በአሜሪካ መንግስት የረድኤት ተቋም ዩኤስኤይድ USAid የሚደረጉ የእርዳታ ስራዎች እንዲቋረጡ መድረጉ ጫናዉ በሌሎች አለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ላይ አድርጎታል።

'የዮኤስኤይድ" የስራ እንቅስቃሴ በድንገት እንዲያቆም መደረጉ ከፍተኛ ክፍት መፍጠሩ የተገለፀ ሲሆን ይህም በሌሎች አለም አቀፍ መንግስታዊ ያልሆኑ የእርዳታ ድርጅቶች ላይ እንዲወድቅ ማድረጉ ተሰምቷል ።

ድርጅቶቹ በኢትዮጵያ ጤና፣ ትምህርት፣ ግብርና፣ ሰብአዊ እርዳታ እና የአካባቢ ጥበቃ ያሉ የልማት ዘርፎች ላይ እየተሳተፉ የሚገኙ ናቸው።

እናም አሁን የአሜሪካ መንግስት ድንገት በመቋረጡ፣ በዩኤስኤይድ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን እንዲጨርሱ ወይም እንዲሸፍኑ እየተደረጉ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።

ይህን ዉሳኔዉ በተመሳሳይ በኢትዮጵያ ተግባራዊ መደረግ የጀመረ ሲሆን በድርጅቱ ቀድሞ የተጀመሩ ፕሮጀክቶች በሌሎች መሰል የእርዳታ ድርጀቶች ላይ ኃላፊነቱ ወድቋል ።

ፕሬዝዳንት ትረምፕ መንግስቴ ተገቢነታቸውን እስኪያረጋግጥ ማንኛውም እርዳታ ይቁም ብለዋል።

ያልተቋረጡት ብቸኛ ድጋፎች ለእስራኤልና ግብፅ የሚደረጉ ብቻ ናቸው መባሉን ቅዳሜ ገበያ መዘገቧ ይታወሳል።

ምንጭ👉 ቅዳሜገበያ


ፆታ የቀየሩ ወታደሮችን ከአሜሪካ መከላከያ የሚያግድ ኘሬዝደንታዊ ትዕዛዝ ትራምኘ ዛሬ ይፈርማሉ
-------

ፆታ የለወጡ ወታደሮች ከአሜሪካ ሰራዊት አባልነት እንዲታገዱ ዶናልድ ትራምኘ ኘሬዝደንታዊ ውሳኔ ዛሬ ያሳልፋሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው።

በአሜሪካ መከላከያ ሰራዊት ውስጥ ብዝሃነትን ማስተናገድ በሚል ማዕቀፍ ፆታ የቀየሩ እና የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻን የፈፀሙ ግለሰቦችን በሰራዊት አባልነት እንዲሆኑ ሲደረግ ነበር።

ኘሬዝደንት ትራምኘ በምርጫ ውድድር ወቅት ከፆታ ጋር በተያያዘ ከተፈጥሮአዊ መንገድ ውጭ አካሄዶችን በፅኑ ሲኮንኑ እና ቢመረጡ መንግስታቸው እርምጃዎችን እንደሚወስድ ሲገልፁ እንደነበር ይታወሳል።

ዛሬ ኘሬዝደንቱ ሶስት ኘሬዝደንታዊ ትዕዛዞችን እንደሚፈርሙ የሚጠበቅ ሲሆን ከነዚህ አንዱ ፆታ የቀየሩ በአሜሪካ ሰራዊት ውስጥ እንዳያገለግሉ ክልከላ የሚጥለው ውሳኔ ዋንኛው እንደሆነ ታውቋል።


ላኩራዋ ፥ በናይጄሪያ ተጨማሪ ስጋት የደቀነው የሽብር ቡድን
-------------

ናይጄሪያ ላኩራዋ የተሰኘውን ታጣቂ ቡድን በሽብርተኝነት በመፈረጅ በመላ ሀገሪቱ እንዳይንቀሳቀስ አገደች።

ላኩራዋ ታጣቂ ቡድን ሙዚቃ የሚሰሙ ሰዎችን የሚገርፍ፣ ጥቃት የሚፈፅም እና በሰሜን ምዕራብ ናይጄሪያ እና ከኒጀር አዋሳኝ ድንበር አካባቢ ያሉ ነዋሪዎችን ዒላማ የሚያደርግ አዲስ ታጣቂ ቡድን መሆኑ ተገልጿል።

የናይጄሪያ ባለሥልጣናት እንዳሉት ላኩራዋ በማሊ እና ኒጀር ካሉ 'ጂሃዲስት ቡድኖች' ጋር ግንኙነት ያለው ሲሆን፤ ታጣቂዎቹ ለዓመታት በናይጄሪያ እና ኒጀር ድንበር ላይ ተቀምጠው የአካባቢውን ሴቶች ያገባሉ፤ ወጣቶችን ይመለምላሉ።

ይህም ከእስላማዊ ታጣቂ ቡድን ቦኮሃራም እስከ አጋች ወንበዴዎች እንዲሁም ከሌሎች በርካታ ታጣቂ ቡድኖች ጋር እየተዋጋች ላለችው ናይጄሪያ ተጨማሪ የደኅንነት ስጋት ሆኖባታል ተብሏል።

በዚህም የናይጄሪያ መንግሥት ሐሙስ ዕለት የቡድኑን ተግባራት በመዘርዘር በዋና ከተማዋ አቡጃ ለሚገኘው ከፍተኛ ፍርድ ቤት የክስ ሰነድ አስገብቶ ነበር።

ሰነዱ ላኩራዋ ከብቶችን መዝረፍ እና ለገንዘብ ሰዎችን ማገትን፣ ጠለፋን፣ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ላይ ጥቃት መፈፀምን ጨምሮ በሽብር ተግባራት ላይ ሲሳተፍ መቆየቱን ያስረዳል።

ከዚህም በተጨማሪ ቡድኑ በአካባቢው የሰላማዊ ሰዎችን ሕይወት ያጠፋ፣ ጉዳት እና የንብረት ውድመትን ያስከተለ ጎጂ የሆነ ርዕዮተ ዓለምን በማሰራጨት እና ነዋሪው ባለሥልጣናትን እንዳያከብር በማበረታታት ተከሷል ነው የተባለው።

ቡድኑ የተፈጠረው በሶኮቶ እና ኬቢ ግዛቶች ውስጥ በሚገኙ መንደሮች ውስጥ ከጥቂት ዓመታት በፊት የነበረ ሲሆን የአካባቢው ሰዎች ለባለሥልጣናት ቢያሳውቁም የተሠራ ሥራ አልነበረም።

መጀመሪያ ላይ የላኩራዋ አባላት የአካባቢውን ማኅበረሰቦች ከታጣቂዎች እና ከከብት ዘራፊዎች እንደሚጠብቁ ቃል ገብተው እንደነበር ነው የተገለጸው።

ሆኖም የነዋሪዎችን ስልክ መፈተሽ እና በስልካቸው ላይ ሙዚቃ የጫኑ ሰዎች ሙዚቃውን ከማጥፋታቸው በፊት መግረፍ ሲጀምሩ ነገሮች እንደተባባሱ አንድ ግለሰብ ተናግሯል።

ለፍርድ ቤቱ በቀረበው ሰነድ ላይም የናይጄሪያ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ እና የፍትሕ ሚኒስትሩ ላቴፍ ፋግቤሚ፣ የቡድኑ ድርጊቶች ለብሔራዊ ደኅንነት ከፍተኛ ስጋት ሆኗል ብለዋል።

ባለፈው ዓመት የጦሩ ቃል አቀባይ ሜጄር ጀኔራል ኤድዋርድ ቡባ፣ የላኩራዋ ቡድን መፈጠር በጎረቤት ሀገራት ማሊ እና ኒጀር ካለው የፖለቲካ አለመረጋጋት ጋር በቀጥታ እንደሚያያዝ መናገራቸው ይታወሳል።

ጦሩ በእስላማዊ ሽምቅ ተዋጊዎች ግፊት ምክንያት በሁለቱም ሀገራት ተሰማርቶ ነበር።

ዳኛ ጀምስ ኦሞቶሾ ባሳለፉት ፈጣን ውሳኔም ቡድኑን የሽብርተኛ ድርጅት ብለው የፈረጁ ሲሆን ሌሎች ተመሳሳይ ቡድኖችም በመላ ሀገሪቱ በተለይም በሰሜን ምዕራብ እና ሰሜን ማዕከላዊ ክልሎች እንዳይንቀሳቀሱ የጣለውን እገዳ አራዝመዋል።

ይህ ውሳኔ የናይጄሪያ መንግሥት በቡድኑ ላይ ጠንካራ እርምጃ ለመውሰድ ሥልጣን ይሰጠዋል ነው የተባለው።

የፀጥታ ተቋማትም የቡድኑን እንቅስቃሴ የማደናቀፍ እና የማፍረስ ሰፊ ሥልጣን ያላቸው ሲሆን ይህም እስራትን፣ ክስ ማቅረብን፣ የንብረት እገዳን እና ክትትልን ይጨምራል።

ከዚህም በተጨማሪ በሽብር ከተፈረጀው ቡድኑ ጋር ግንኙነት ያላቸው ግለሰቦች ላይ መገለልን ሊያስከትል ይችላል።

በመላ ሀገሪቱ በተለይም በሰሜናዊ ናይጄሪያ በአውሮፓውያኑ 2000 መጨረሻ ላይ ብቅ ካለው ቦኮሃራም ጋር ተመሳሳይነት ያለው ሁኔታ እንዳይፈጠር ነዋሪዎች ሰግተዋል።

ቦኮሃራም ማለት " የምዕራባውያን ትምህርት የተከለከለ ነው" ማለት ሲሆን በክልሉ እስላማዊ አገዛዝ ለመመሠረት በተደጋጋሚ ዓለማዊ ትምህርት ቤቶችን ዒላማ ያደርጋል።

ቡድኑ እንደ አውሮፓውያኑ በ2014 ከሰሜን ምሥራቃዊቷ ከተማ ቺቦክ ከ200 በላይ ሴት ተማሪዎችን አግቶ ከወሰደ በኋላ ስሙ በዓለም አቀፍ ደረጃ ታውቋል።

https://t.me/Ethioplus_s


ላኩራዋ ፥ በናይጄሪያ ተጨማሪ ስጋት የደቀነው የሽብር ቡድን
-------------


ቀያይ ሴጣኖች አሸንፈዋል
------------

ማንችስተር ዩናይትድ በውድድር አመቱ ለሶስተኛ ጊዜ ከሜዳው ውጭ አሸናፊ ሆኗል።

ክራቫንኮቴጅ ላይ ከፉልሃም ጋር ያደረገውን ጨዋታ ተከላካዩ ማርቲኔዝ ባስቆጠረው ብቸኛ ግብ አንድ ለባዶ አጠናቋል።

20 last posts shown.