GSFGBC፡ ጎሮ ሰፈራ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤ/ክ


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


ይህ የቴሌግራም ቻናል በኢትዮጽያ ሙሉ ወንጌል አማኛች ቤተክርያን የጎሮ ሰፈራ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ፣የሚከናወኑና የሚተገበሩ ፕሮግራምዎችን መከታተያ page ነው፡፡
this is official page of goro sefera full gospel believers church...
If you have any question Contact:
@Kirubel76
@pastor_sisay

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


በሥጋ መጣ

ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ መጣ ማለት በሥጋ ሳይመጣ በፊት ያለ ሥጋ ነበረ፤ ኋላ ግን በሥጋ መጣ ማለት ነው። በሥጋ ሳይመጣ በፊት ያለ ሥጋ ነበረ፤ ቃል ነበረ፤ መለኮት ነበረ። በሥጋ ሲመጣ ደግሞ መለኮትን ሳይተው ሥጋን ጨመረ።

ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ ሲመጣ፥ ካለመኖር ወደ መኖር አይደለም የመጣው። ከመኖር ወደ መኖር ነው የመጣው። መለኮት ብቻ ሆኖ ከቀድሞው ለዘላለም መኖር፥ መለኮትም ሰውም ሆኖ በአንድ አካል ከመጣበት ወዲህ ለዘላለም ወደ መኖር ነው የመጣው።

ይህንን በሥጋ መምጣቱን የማይቀበል፥ የማያምን፥ የማይታመን ሁሉ፥ ኢየሱስ መለኮት አይደለም፤ ሰው ብቻ ነው፤ የሚል ሁሉ፥ ከእግዚአብሔር አይደለም፤ እርሱ የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ ነው።

የእግዚአብሔርን መንፈስ በዚህ ታውቃላችሁ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ የሚታመን መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው፥ ኢየሱስ ክርስቶስም በሥጋ እንደ መጣ የማይታመን መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም፤ ይህም የክርስቶስ ተቃዋሚው መንፈስ ነው፤ ይህም እንዲመጣ ሰምታችኋል፥ አሁንም እንኳ በዓለም አለ። 1ዮሐ. 4፥2-3

ብዙ አሳቾች ወደ ዓለም ገብተዋልና እነርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ የማያምኑ ናቸው፤ ይህ አሳቹና የክርስቶስ ተቃዋሚው ነው። 2ዮሐ. 7


ፓስተር ጻዲቁ አብዶ
22/3/2017 ዓም


ጳውሎስ ለአብያተ ክርስቲያናት መታነጽ እና ለክርስቶስ ወንጌል ስለከፈለው ዋጋ ሲገልጽ እንዲህ አለ፦

​1. ብዙ ጊዜ በሥራ ደክሜአለሁ፤
2. ​ብዙ ጊዜ ታስሬያለሁ፤
3. ​ብዙ ጊዜ ተገርፌአለሁ፤
4. ​ብዙ ጊዜ ለሞት ተቃርቤአለሁ።
5. ​አይሁድ ለአርባ ጅራፍ አንድ የቀረው አምስት ጊዜ ገርፈውኛል።
6. ​ሦስት ጊዜ በዱላ ተደብድቤአለሁ፤
7. ​አንድ ጊዜ በድንጋይ ተወግሬአለሁ፤
8. ​ሦስት ጊዜ የመርከብ አደጋ ደርሶብኛል፤
9. ​አንድ ሌሊትና ቀን በባሕር ላይ አድሬአለሁ፤
10. ​ብዙ ጊዜ በጒዞ ተንከራትቻለሁ፤
11. ​ደግሞም ለወንዝ ሙላት አደጋ፣
12. ​ለወንበዴዎች አደጋ፣
13. ​ለገዛ ወገኖቼ አደጋ፣
14. ​ለአሕዛብ አደጋ፣
15. ​ለከተማ አደጋ፣
16. ​ለገጠር አደጋ፣
17. ​ለባሕር አደጋ እንዲሁም ለሐሰተኞች ወንድሞች አደጋ ተጋልጬ ነበር።
18. ​ብዙ ጥሬአለሁ፤
19. ​ብዙ ደክሜአለሁ፤
20. ​ብዙ ጊዜ እንቅልፍ አጥቻለሁ፤
21. ​ተርቤአለሁ፤
22. ​ተጠምቻለሁ፤
23. ​ብዙ ጊዜ ምግብ ሳልቀምስ ኖሬአለሁ፤
24. ​በብርድና በራቍትነት ተቈራምጃለሁ።

ሌላውን ነገር ሳልቈጥር፣ ዕለት ዕለት የሚያስጨንቀኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ሐሳብ ነው። (2ቆሮ.11:23-28)


Video is unavailable for watching
Show in Telegram


"...እግዚአብሔር የፈቃዱን ዕውቀት በመንፈሳዊ ጥበብና መረዳት ሁሉ ይሞላችሁ ዘንድ ስለ እናንተ መጸለይና መለመን አላቋረጥንም፤"

(ቈላ 1፥9 አመት)


የእግዚአብሔር ፈቃድ እንዲፈጸም የሚጸለየውን ያህል እንዲታወቅም መጸለይ ያስፈልጋል። 'በዚህ ጉዳይ ላይ የጌታ ፈቃድ ምንድነው?' ተብሎ ይጠየቃል። የፈቃዱን ዕውቀት ለማወቅ ደግሞም ይጸለያል። ይህም ሰማያዊ ጥበብና ግልጽ መረዳትን የሚፈልግ ነው፤ ጳውሎስ እንዲህ ብሎ እንደ ጻፈ፤ "እግዚአብሔር የፈቃዱን ዕውቀት በመንፈሳዊ ጥበብና መረዳት ሁሉ ይሞላችሁ ዘንድ ስለ እናንተ መጸለይና መለመን አላቋረጥንም" (ቈላ 1፥9)። ፈቃዱን ለማወቅና ለመረዳት፣ ሌሎችም እንዲሁ የፈቃዱን ዕውቀት እንዲያስተውሉ መጸለይ፣ ፈቃዱን ለመለየትና ለመፈጸም ዐይነተኛ መፍትሄ ነው። ብርሃን ያላገኘ ዐይን ማየት እንደማይችል ሁሉ፣ "መንፈሳዊ ጥበብና መረዳት" ያላገኘ ልብና አእምሮ ፈቃዱን መለየት ይቸገራል።


የእግዚአብሔር ፈቃድ የሚታወቅ፣ የምንረዳው ነው። ለመረዳት ግን የታደሰ አእምሮ ይጠይቃል፤ ፈቃዱ ከመረጃ ያለፈ ነውና። መንፈሳዊ ስለሆነም ልብ ብቻ የሚሳተፍበት አይደለም፤ የተለወጠና የጠራ አእምሮ ይፈልጋል ፤ "መልካም፣ ደስ የሚያሰኝና ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔር ፈቃድ ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በአእምሯችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ" (ሮሜ 12፥2)። ፈቃዱ ከመልካምነት ፈጽሞ የማይጎድል፣ የውስጥ ደስታ—ርካታ—ያለበት፣ እንዲሁም ፍጹም (እንከን አልባ) ነው። ይህን ለመረዳት ነው እንግዲህ የተለወጠ፣ በቃሉም ሁልጊዜ የሚታደስ አእምሮ የሚያስፈልገው። ፈቃዱን በዓለም ካለው አሠራር ጋራ እያነጻጸርን ወይም እየተነተንን የምንረዳው አይደለም፤ አእምሮን የሠራው ራሱ አዳሽ ስለሆነ፣ በርሱ እየታገዝን የምንረዳውና በተረዳንበት አቅም የምንፈጽመው እንጂ!


የሚጀመረው፣ የሚቀጠለውና የሚቆመው!

መጀመር፡- አንዳንዶቻችን አንድን ነር መጀመር ነው የሚያስቸግረን፡፡ ይህ ሲሆን፣ የምናስባቸውና የምናቅዳቸው ነገሮች ሁሉ እየተንከባለሉ ከንቱ ሆነው ይቀራሉ፡፡ 

መቀጠል፡- ሌሎቻችን ደግሞ መነቃቃትና መጀመር ችግር የለብንም፣ የጀመርነውን መቀጠል ግን ያስቸግረናል፡፡ ይህ ሲሆን፣ ነገሮችን እየጀመርንን እያቆምም ጊዜን፣ ስሜትን፣ ገንዘብንና በሰዎች የመታመንን ሁኔታ እየከሰርን እንሄዳለን፡፡

እንደገና መጀመር፡- ከዚህ በተጨማሪ፣ አንድን ያቆምነውን ነገር በእንዴት አይነት ሁኔታ እንደገና መጀመር እንዳብን የማናውቅና የሚያስቸግረን ሰዎች አለብ፡፡ ይህ ሲሆን፣ ጀምረን ያቆምናቸውን ነገሮች ምነው ባላቆምኩኝ በሚል ጸጸት ውስጥ እንኖራለን፡፡

ማቆም፡- ከላይ ከተጠቀሱት ትንሽ ለየት ያለው ደግሞ ካቆምናቸው ነገሮች መካከል የትኞቹ እንደገና መቀጠል፣ የትኞቹ ደግሞ በዚያ መተው እደሚገባቸው የመለየጥ ጥበብ የሚጎድለን አለን፡፡ ይህ ሲሆን፣ ካቆምነው በኋላ ጊዜው ያለፈበትን ነገር እንደገና ለመጀመር እንታገላለን፡፡ 



ምንጭ ዶክተር ኢዮብ


Forward from: GSFGBC፡ ጎሮ ሰፈራ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤ/ክ
የክርስቶስ ፍቅር ግድ ይለናልና፤ ምክንያቱም አንዱ ስለ ሁሉ እንደ ሞተ እርግጠኞች ሆነናል፣ ከዚህም የተነሣ #ሁሉ ሞተዋል።  #በሕይወት ያሉትም ለሞተላቸውና ከሙታን ለተነሣላቸው እንጂ ከእንግዲህ #ለራሳቸው እንዳይኖሩ እርሱ ስለ ሁሉ ሞተ።
2 ቆሮንቶስ 5:14-15

እግዚአብሔር ወልድ የሞተው እኔ ለራሴ እንዳልኖር ፤ ከፍለጎቴ በፊት ሀሳቡን እንዳስተውል የኑሮዬ ሚዛን በእርሱ ፈቃድ እንዲለካ ለርሱ እንድኖር ነው።




Forward from: Ethiopian Full Gospel Believers Church
Video is unavailable for watching
Show in Telegram
#አስቸኳይ_የማሳሰቢያ_መልዕክት!!
   ከኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የተላለፈ መልዕክት !!
ለበለጠ መረጃ፡
በዩትዩብ፡ https://www.youtube.com/@efgbc
ፌስቡክ፡  https://www.facebook.com/etfullgospel/
ቴሌግራም፡ https://t.me/EFGBC_HO እንዲሁም በሌሎች ፕላትፎርሞቻችን ይከታተሉን።


Forward from: Ethiopian Full Gospel Believers Church
#አስቸኳይ_የማሳሰቢያ_መልዕክት!!
   በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያንና በፓስተር ዮናታን አክሊሉ በትብብር የሚሰራ የገቢ ማሰባሰቢያ ስራ እንዳለ ተደርጎ እየተሠራጨ ያለው ማስታወቂያ ፍፁም ሀሰትና ማጭበርበር ስለሆነ ቅዱሳን ከዚህ የማታለል ድርጊት ራሳችሁን እንድትጠብቁ እያሳሰብን በነገው እለት ቤተክርስቲያኗ ማብራሪያ የምትሰጥ መሆኑን በጌታ ፍቅር እናሳስባለን።
  👉ለሁሉም እንዲደርስ በአስቸኳይ share share ይደረግ!!
ለበለጠ መረጃ፡
በዩትዩብ፡ https://www.youtube.com/@efgbc
ፌስቡክ፡  https://www.facebook.com/etfullgospel/
ቴሌግራም፡ https://t.me/EFGBC_HO እንዲሁም በሌሎች ፕላትፎርሞቻችን ይከታተሉን።


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
https://vm.tiktok.com/ZMkkgLdDk/






ሰላም ለእናንተ ይሁን ቅዱሳን

ነገ ጠዋት 3 ሰዓት ላይ የጸሎት ቤቱ ጽዳት ሰላለ ሁላችሁም እንድትገኙና እንዳጸዳ በጌታ ፍቅር እንጠይቃለን


Forward from: GSFGBC፡ ጎሮ ሰፈራ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤ/ክ
ሰላም ለእናንተ ይሁን ቅዱሳን

ወንድማችን ቢቂላ ሂካ አባቱ አርፈው ለቀብር ሰለሄዱ ሲመጣ ልቅሶ እንድትደረሱ እና ሰልክም በመደወል እንድታጽናኗቸው በጌታ ፍቅር እናሳስባለን

ሰልክ
091 181 5682


አስሩ ምርጥ ምርጫዎች!

1.  ከመጥላት ይልቅ መውደድን እንምረጥ!

2.  ከመኮሳተር ይልቅ ፈገግታን እንምረጥ!

3.  ከማፍረስ ይልቅ መገንባትን እንምረጥ!

4.  ከማቆም ይልቅ እስከ ግባችን ድረስ መቀጠልን እንምረጥ!

5.  ከማማት ይልቅ ማመስገንን እንምረጥ!

6.  ከማቁሰል ይልቅ መፈወስን እንምረጥ!

7.  ከመውሰድ ይልቅ መስጠትን እንምረጥ!

8.  ከመዘግየት ይልቅ እርምጃን መውሰድ እንምረጥ!

9.  ከመጨነቅ ይልቅ መጸለይን እንምረጥ!

10.  ከመቀየም ይልቅ ይቅርታን እንምረጥ!


ምንጭ ኢዮብ


ሰላም ለእናንተ ይሁን ቅዱሳን

ወንድማችን ቢቂላ ሂካ አባቱ አርፈው ለቀብር ሰለሄዱ ሲመጣ ልቅሶ እንድትደረሱ እና ሰልክም በመደወል እንድታጽናኗቸው በጌታ ፍቅር እናሳስባለን

ሰልክ
091 181 5682


ሰላም ለእናንተ ይሁን ቅዱሳን

ከፊታችን ሰኞ 21/04/2017 ዓም እሰከ 27/2017ዓም ድረስ ጾምና ጸሎት ይኖረናል ሁላችን ተገኝተን በጋራ የእግዚአብሔር የእግዚአብሔርን ፊት እንድንፈልግ ሰንል በጌታ ፍቅር እናሳስባለን


በጾምና ጸሎት መጨረሻ ቀን ማለትም በ27/04/2017 ዓም እሁድ የጌታ እራት ይኖረናል

ፕሮግራሙ ከጠዋቱ 2:30 ይጀምራል


የተለያዩ አዋቂዎች የሚነግሩን በጥቂቱ ቢለያይም አንድ ጤናማ ሰው በደቂቃ በአማካኝ በደቂቃ ከ 20 ጊዜ በላይ ሊተነፍስ ይችላል፡፡

ይህ የመተንፈስ ስጦታ በዚህች ምድር ላይ በሕይወት እንድንኖር ፈጣሪ ከሰጠን ታላላቅ ስጦታዎች መካከል ዋነኛው ነው፡፡

ይህንን ሰዎች ከእነሱ እንዳይወሰድባቸው ምንም ነገር ከመክፈል ወደኋላ የማይሉትን በደቂቃ ከ 20 ጊዜ በላይ የመተንፈስ ስጦታ በየደቂቃው እደጋገመ ከ 20 ጊዜ በላይ ፈጣሪ ከሰጠን፣ ለህልውናችን እምብዛም መዋጮ ለሌላቸው ነገሮች መጨናነቃችንን ትንሽ ቀነስ አድርገነው ወደ ሰራችን ብንሄድ ምን ይመስላችኋል?


መልካም የሰራ ቀን

ምንጭ ዶክተር ኢዮብ

20 last posts shown.