"...እግዚአብሔር የፈቃዱን ዕውቀት በመንፈሳዊ ጥበብና መረዳት ሁሉ ይሞላችሁ ዘንድ ስለ እናንተ መጸለይና መለመን አላቋረጥንም፤"
(ቈላ 1፥9 አመት)
የእግዚአብሔር ፈቃድ እንዲፈጸም የሚጸለየውን ያህል እንዲታወቅም መጸለይ ያስፈልጋል። 'በዚህ ጉዳይ ላይ የጌታ ፈቃድ ምንድነው?' ተብሎ ይጠየቃል። የፈቃዱን ዕውቀት ለማወቅ ደግሞም ይጸለያል። ይህም ሰማያዊ ጥበብና ግልጽ መረዳትን የሚፈልግ ነው፤ ጳውሎስ እንዲህ ብሎ እንደ ጻፈ፤ "እግዚአብሔር የፈቃዱን ዕውቀት በመንፈሳዊ ጥበብና መረዳት ሁሉ ይሞላችሁ ዘንድ ስለ እናንተ መጸለይና መለመን አላቋረጥንም" (ቈላ 1፥9)። ፈቃዱን ለማወቅና ለመረዳት፣ ሌሎችም እንዲሁ የፈቃዱን ዕውቀት እንዲያስተውሉ መጸለይ፣ ፈቃዱን ለመለየትና ለመፈጸም ዐይነተኛ መፍትሄ ነው። ብርሃን ያላገኘ ዐይን ማየት እንደማይችል ሁሉ፣ "መንፈሳዊ ጥበብና መረዳት" ያላገኘ ልብና አእምሮ ፈቃዱን መለየት ይቸገራል።