ከ2 ሺ በላይ የሚሆኑ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና የአካዳሚክ ማኅበረሰብ አባላት በ5 ሚሊዮን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ዙሪያ የቪዲዮ ኮንፈረንስ ውይይት አደረጉ
አዲስ አበባ፡ ጥቅምት 21/2017 ዓ/ም፡ የአምስት ሚሊዮን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ለሳይበር ደህንነት የሚጫወተው ሚና በሚል ርዕስ በመላ ሀገሪቱ ከሚገኙ ተማሪዎች እና የአካዳሚክ ማኅበረሰቡ ጋር የቪዲዮ ኮንፍረስን (Video Conference) የውይይት መድረክ የተካሄደ ሲሆን፤ በዚህም ከ43 ዩኒቨርሲቲዎችና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከሚገኙ 30 ከሚሆኑ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች የተውጣጡ ከሁለት ሺ በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
በቪዲዮ ኮንፈረንሱ ላይ 5 ሚሊዮን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ በግለሰብ፣ በተቋም እና ሀገር ደረጃ ስለሚያስገኘው ፋይዳ፣ የባለድርሻ አካላት እና የዜጎች ሚና እንዲሁም ኢኒሼቲቩ ለሳይበር ደህንነት ስለሚኖረው አበርክቶ ገለጻ ቀርቧል፡፡ ገለጻውን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የሳይበር ልህቀት ማእከል ዳይሬክተር አቶ ቢሻው በየነ ያቀረቡ ሲሆን፤ ኢኒሼቲቩ በየትኛውም የትምህርት ዘርፍ እና የእድሜ ደረጃ ላይ ያሉ ዜጎች ሊወስዱት እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡ ባለንበት የዲጂታል ዘመን ቴክኖሎጂው ይዞልን የመጣቸው መልካም አጋጣሚዎች እንዳሉ ሁሉ ከፍተኛ የስጋት ተጋላጭነትም ይኖረዋል፤ ለዚህም የዲጂታል ምህዳሩ ላይ መሰረታዊ እውቀት እና ንቃተ ያለው ዜጋ ለመፍጠር ኢኒሼቲቩ ላይ ያሉ ስልጠናዎች ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወቱ አቶ ቢሻው ተናግረዋል፡፡
የአምስት ሚሊዮን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ የተማሪዎችንም ሆነ በአጠቃላይ የታዳጊ ወጣት ኢትዮጵያውያንን መሰረታዊ የቴክኖሎጂ ክህሎት የሚያጎለብት ስልጠና በመሆኑ ሁሉም ሰው መውሰድ እንደሚገባው በኮንፈረንሱ ላይ ተሳታፊ የነበሩ ተማሪዎችና የአካዳሚክ ማኅበረሰብ አባላት ተናግረዋል፡፡ ከዚህ አኳያ በዛሬው እለት የተካሄደው ኮንፍረንስ ተማሪዎችም ሆነ የአካዳሚክ ማኅበረሰቡ በስልጠናው ላይ በስፋት እንዲሳተፉ የሚያነቃቃ ነው ብለዋል፡፡
በውይይት መድረኩ ላይ ከተሳታፊዎች በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን ከእነዚህም መካከል፤ በኢኒሼቲቩ አጠቃላይ አተገባበር፣ ኢኒሼቲቩን ተግባራዊ ለማድረግ ሊኖሩ በሚገቡ የፖሊሲ አቅጣጫዎች ዙሪያ ጥያቄዎች ተነስተዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በኢኒሼቲቩ ላይ ከቀረቡት ስልጠናዎች በተጨማሪ መሰረታዊ የሳይበር ደህንነት ስልጠና በሚካተትበትና በሚሰጥበት አግባብ ዙሪያ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ማብራሪያ እና ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል ፡፡
በቪዲዮ ኮንፈረንሱ ማብቂያ ላይ የመዝጊያ ንግግር ያደርጉት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነተ አስተዳደር ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮዳሄ አርአያሥላሴ እንዳሉት 5 ሚሊዮን ኮደርስ ኢንሼቲቭ የኢትዮጵያ ወጣቶችን ከመጻኢው ዘመን ጋር የሚያስተሳስር መልካም አጋጣሚ መሆኑን ገልጸው፤ ይህን ወርቃማ እድል በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባቸው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
#5_Million_Ethiopian_Coders #Digital_Ethiopia #INSA
http://www.ethiocoders.et
════❁✿❁ ═══════
ለበለጠ መረጃ
ከዚህ ታች ባለው አድራሻ በፌስቡክና በቴሌግራም ይከተሉን
ፌስቡክ አድራሻችንን
Gettechinfofb (https://www.facebook.com/profile.php?id=100022088745521)
የቴሌግራም አድራሻችንን
https://t.me/Gettechinfonow