ጀነት እንገናኝ
〰〰〰〰
ክፍል ዘጠኝ
〰〰〰〰
«ዛሬን እንደ እድሜህ ኑር ። አስተሳሰብህን አዳብር ፣ ንግግርህን አሳምር ፣ ልብህን ከኒፋቅ ፡ ሰውነትህን ከኩራት ፡ ምላስህን ከሀሜት ውሸት አፅዳ ፡ ወሬ ማመላለሱ ይቅርብህ ፡ ቅናት ምቀኝነቱስ ምን ሊጠቅምህ !
ዛሬ ብቻ ነው ቀንህ …. ዛሬ ብቻ ነውና ህይወትህ ህያው የሆነን ኑሮ ለመኖር ዛሬዉኑ ጣር … እናት አባትህን አስደስት ፡ ዘመዶችህን ቀጥል ፡ በሽተኞችን ዘይር ፡ ደካሞችን ደግፍ ፡ ችግረኞችን አስታውስ ፡ ለፍጥረታት ሁሉ እዘን ፡ የመልካም ስራ መንገዱ ብዙ ነው እያሳደድክ አከማች ።
ዛሬ ብቻ ነው ቀንህ -- ስለ ትናንቱ ስታስብ የዛሬው ቀን አያምልጥህ ፡ ዛሬ ነውና ቀንህ በሱ ውስጥ ሳትጨነቅ ሳትማረር ደስተኛ ሆነህ ኑር ። ትናንት በጥሩ ይሁን በመጥፎ የያዘውን ይዞ አልፏልና ላይመለስም ሂዷልና ስለሱ አትጨነቅ እሱም እንደ ፀሐዩ ይጥለቅ ። በእጅህ ስላልገባው ስለ ነገውስ ምን አሣሰበህ ከሌለ ነገር ጋር ለመኖር ምን አዳከረህ !
ዛሬን የተሟላና መልካም ኑሮን ኑር - ነገንም አላህ ካበቃህ እንደዛሬው ኑር ፡ ትላንት ሙቷልና ከቀብር ጎትተህ አታዉጣው ፡ ነገን አልደረስክበትምና በእጅህ የሌለዉን ኑሮ አትኑር ፡ ዛሬ ብቻ ነዉ ቀንህ ፡ ዛሬዎች ተደማምረውም ሙሉ ዕድሜህ ይሆናሉ ፡ ዛሬን ተደስተህ ከኖርክ ነገንም ደርሰህባት እንደ ዛሬው ከኖርክ ሙሉ ዕድሜህን ደስተኛ ሆነህ ኖርክ ማለት ነው ።
መሪነት ህዝብን ለማገልገል ወይንስ በህዝብ ለመገልገል !