ወርቃማ ንግግሮች


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


ሰው የለበስክ ሰው እንጂ ልብስ የለበስክ ሰው አትሁን.. ሰውነት የአለም ምርጡ ጌጥህ እሱ ነውና።
አስተያየት እንቀበላለን.. @Golden_SpeechBot
🍂

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


Forward from: ትዳር እና ኢስላም 🌷🌹🥀
☹️☹️☹️🤩😜🥳😖☹️

የመጀመሪያው ፕሮግራም

📣  🥳🥳😣☹️☹️😭😏🤩
​•┈┈•┈┈•⊰✿◇✿⊱•┈┈•┈┈•

🎤
      ተ
⭐️
             ጀ
⭐️
                  መ
⭐️
                          ረ
⭐️

ገባ ገባ በሉ ባረከሏሁ ፊኩም!
ሊንኩን ለሌሎችም ሼር አድርጉት‼

 ➘  ➘ ➘ ➘➘ ➘ ➘ ➘  ➘ ➘ ➘
https://t.me/tdarna_islam?livestream
https://t.me/tdarna_islam?livestream


🙁☹️😭🙁😭🙁☹️🙁
😊አዲስ የሙሀደራ ፕሮግራም 🎁
🙁🙁🙁🙁🙁🙁☹️🥳

🎁ነገ ሰኞ ማታ ለየት ያለ ፕሮግራም
🔥በትዳር እና ኢስላም ቻናል ✅
☹️🙁🙁☹️🙁🙁🙁😭
የረመዳን ዝግጅት አስመልክቶ

ተጋባዥ ኡስታዞች
⭐️
⚙️አቡ ሂበቱላህ
⚙️አብዱረዛቅ አል ባጂ
⚙️አብደሽኩር አቡ ፈውዛን
⚙️አቡ ሁዘይፋ
⚙️አቡ አይመን

☹️🙁😭🥳🙁🤩😭🙁
🏠ቀን እና ሰዓት  ነገ/ ሰኞ ማታ

😓ከምሽቱ 3:30 ጀምሮ🔋

0️⃣0️⃣0️⃣የሚተላለፍበት ቻናል✨
😋
🙁🙁☹️😶🙁☹️😏😣
t.me/tdarna_islam
t.me/tdarna_islam
🙁🙁☹️😶🙁☹️😏😣


☹️ኢህሳን 😤🔠🔠🔠🔠😤✈️


ይህ ቻናል ነፃ የስራ ማስታወቂያ የሚለቀቅበት ቻናል ነው☹️ ቻናሉ ለየት የሚያደርገው ሁሉም ነገር በነፃ መሆኑ ነው
☹️🙁🙁☹️🙁🙁🙁😭
ቻናሉን በበለጠ እንዲዳረስ join እንዲሁም ሼር በማድረግ የበኩላችሁን ተወጡ☹️

😣🙁🙁☹️🙁🥳🤩☹️
ቻናሉን ለመቀላቀል
🙁☹️⚡️

t.me/ihsan_jobs 🎁
t.me/ihsan_jobs 🎁


እውነት/ሀሰት

_በአላህና  በመልእክተኛው እንዲሁም በቁርአን መቀለድ ከእምነት ያስወጣል ❓

⚙️ከትክክለኛው  መልስ ጀርባ የሚሰጣችሁ አድድ በማድረግ ተቀላቀሉ
    👇👇👇


"አላህ አዳዲስ ጅማሮዎችን ሲሰጥህ… የበፊት ስህተቶችን አትድገም።"
[ነጂብ መህፉዝ ]

ምናልባት ትናንትህ  በብዙ ስህተቶች ተሞልቷል። ትናንት ላይ ያባከንካቸው በርካታ እድሎች ይኖራሉ። ግን አስተውል ዛሬ አዲስ ጀንበር ወጥታለች… ጨለማውን የገረሰሰች ጀንበር… ስለዚህ አዲስ ጅማሮን አላህ ሲሰጥህ የትናንቱን ብኩንነትና ስህተት አትድገም።


~🍂

በጊዚያዊ ስሜቶች ለሚያስተናግዱህ ሰዎች ክፍት ሁን ብዬ አልመክርህም። ሲፈልጉህ እላፊ ተጠግተው የነፍስ ዓለም የሚያደርጉህና ስትፈልጋቸው ደግሞ ሽታቸው የሚርቅህ ዓይነት ሰዎች ማለቴ ነው። እና እዚህ ዓይነት ብቻህን የምትፋለምበት ግንኙነት ውስጥ ሰላምም ህይወትም የለም። መራራቅ የማያደበዝዘው፣ መከራና ደስታን የሚጋራና መከታ የሚሆን ግንኙነት ውስጥ ራስህን ኢንቨስት አድርግ። ጓደኞችህንም  በመመርጥ ላይ እያልኩህ ነው።


አዋጅ ሰዎች ሆይ ንቁ!!
ኢማናችሁን ጀድዱ። አካላችሁን በስፖርት መንፈሳችሁን በዒባዳ አንፁ። ማንነታችሁን በዚክር ገንቡ። መጪው ጊዜ ከባድ የዕልቂት ዓመት ነው። በኢማን ብርሃን ጨለማውን የሚሰነጥቁ ሰዎች ብቻ ነጃ የሚወጡበት ዘመን!! አላህ ለጦርነት የፈጠራቸው ሙጃሂዶች እንጂ የማይድኑበት ወቅት

አዋጅ ሰዎች ሆይ ንቁ!!
ምድርና ሰማያት የተመሰረቱባትን ቃል አጥብቃችሁ ያዙ። ፍጥረታት ወደዚህ ምድር የመጡባት፣ ይቅጣጩበት ዘንድ ቂብላ የተተከለባት፣ የጂሃድ ሰይፎች የተመዘዙባት፣ የአላህ መብት በባሪያው ላይ ሁሉ የተደነገገባት ቃል!! ላኢላሀ ኢለላህ!! በእርሷ መንገድ ኑሩ በእርሷ መንገድ እንደፀናችሁም ሙቱ። ራሳችሁን ለመጪው ጊዜ አዘጋጁ።


የአክሱም ሙስሊሞች ጭቆና በአክሱማዊቷ የቁርአን መምህርት (ኡስታዛ)

📍ሐምሌ 1984 አክሱም ላይ ምን ተፈጥሮ ነበር?

📍ይህ ፅሑፍ "አክሱማዊቷ የቁርአን መምህርት" በሚል ነሐሴ 1985 ከታተመው ቢላል መፅሔት የተወሰደ ነው።

"በትግራይ ክልል፤ አክሱም ከተማ ውስጥ የከፍተኛ 2 ቀበሌ 05 ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ ሸምሲያ ሸህ ሷሊህ ለዲናችን መጠናከር የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ በቅርብ የመከታተል እድል አጋጠመኝና አርአያነታቸውን ላወሳችሁ ወደድኩ።

ወ/ሮ ሸምሲያ ሸህ ሷሊሕ ከሰላሳ አምስት በላይ ህፃናትን ቁርአን በማስቀራት ታላቅ ተግባር የፈፀሙ የሙስሊሞች መኩሪያ ናቸው። እኚህ ደርባባ ወ/ሮ ሲናገሩ ረጋ ያሉና ገፅታው የበራ ነው። ቁርአን ማስቀራት የመጀመራቸው ጉዳይ ከአባታቸው ጋር የተያያዘ ነው። አባታቸው ሸህ ሷሊህ ቁርአን ያስቀሩ ነበር። እርሳቸው ሲሞቱ የቁርአን ትምህርቱ ተቋረጠ። በዚህን ጊዜ በአካባቢው የሚገኙ ሙስሊሞች ወ/ሮ ሸምሲያን "ለምን አንቺ አታቀሪም? እርሳቸው ሳሉም ብዙውን ጊዜ የምታቀሪና ቁርአኑን በሉህ (አነስተኛ ጣውላ) የምከትቢው አንቺው አልነበርሽምን?" ብለው ወተወቷቸው። ወ/ሮ ሸምሲያም "እናንተ ከተቀበላችሁኝ ደስታዬ ነው" በማለት ልጆቹን ሰብስበው ማቅራት ጀመሩ። ቁርአንን ለማስቀራት የሚከለክል ምክንያት /ዑዝር/ ሲገጥማቸው አንጋፋ ተማሪዎቸቸው በዝቅተኛ ደረጃ ላይ ያሉትን እንዲያቀሩ ውክልና እንደሚሰጡ አውግተውኛል-በጣፋጭ አንደበት።

ወ/ሮ ሸምሲያ ቁርአን ማስቀራት ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ [1980ዎቹ] ድረስ አያሌ ተፈታታኝ ችግሮች ገጥሟቸዋል። ከእነዚህም ውስጥ ጎላ ብለው የተፈታተኗቸውን እንዲህ ሲሉ አወጉኝ። "እንደምታውቀው እኛ የአክሱም ሙስሊሞች የግላችን ቤት አልነበረንም። ሀብታምም ይሁን ድሃ የአክሱም ሙስሊም የሚኖረው በኪራይ ቤት ነበር። ቤት ለመስራት አይፈቀድልንምና! ይህ በኋይለስላሴ ጊዜ የነበረ ጭቆና ሲሆን ደርግ መጣና ሙስሊም አክሱም ውስጥ ቤት እንዳይሰራ የሚከለክለውን እገዳ አንስቶ መሬት ሰጠን። ታዲያ በክራይ ቤት እኖር በነበረበት ጊዜ ልጆችን ሰብስቤ ቁርአን ሳቀራ አከራዮቼ "ቤታችንን የልጆች መሰብሰቢያ አድርገሽ ልታፈርሺብን ነው..." በማለት በማቅራቴን እንዳቆም ይጠይቁኝ ነበር። እኔ ግን ጥያቄያቸውን አልቀበል ብዬ ማቅራቴን እቀጥላለሁ። እነርሱም ከቤታቸው ያስወጡኛል። እንደገና ሌላ ቤት ተከራይቼ ማቅራቴን እቀጥላለሁ። ትንሽ ቆይተው እነዚህም ይቃወሙኛል። እንዲህ እያልኩኝ የግሌን ቤት እስካገኝ ድረስ ከሀያ ቤቶች ተባርሬያለሁ።

ይህን ካወጉኝ በኋላ የትዝታ ቅኝታቸውን ወደቅርቡ ዘመን መለሱት። እናም እንዲህ አሉኝ። "እንደምታስታውሰው ሐምሌ 1984 በአክሱም ሙስሊሞች ላይ የ"ክተት" አይነት ዘመቻ ተጠንስሶ ነበር። በዚያን ጊዜ እኔ ከሌሎች ሙስሊም ጎረቤቶቼ በበለጠ ተሳድጃለሁኝ። የዚህም ምክንያት ቁርአን የማቀራ ስለሆንኩኝ ነው። አልሐምዱሊላሂ ጎረቤቶቼ ጋር ተደብቄም ቢሆን ነፍሴን አትርፌአለሁ። ሆኖም ግን እኛን ለማጥቃት የተነሱት ሰዎች እቤቴ ድረስ ገብተው የማቀራበትን ቁርአን ቀደድው ሉሑን ሰባብረው ቤቴ ላይ ያለ እቃ አንድ እንኳ ሳይቀር ሰባብረውብኛል።

በውይይታችን መሀል "እስላም የሴቶችን የመማር እድል ይነፍጋል" የሚለው የአላዋቂዎች አሉባልታ ድንገት ትውስ አለኝና ነገሩን አጠገቤ ካሉት እንስት መምህር ጋር አስተያይቼው በውስጤ ሳቅሁኝ። እናም "ሴት አስተማሪ /ቁርአን አቅሪ/ በመሆንዎ የደረሰብዎት ችግር አለን" ብዬ ለወ/ሮ ሸምሲያ ጠየቅኋቸው።

"በእውነቱ ሴት አቅሪ በመሆኔ አንድም የደረሰብኝ ችግር የለም፤ እንዲያውም ብዙዎች ይደሰቱብኛል። ባለቤቴም ለዲኔ በማደርገው እንቅስቃሴ ፍፁም ደስተኛ ከመሆናቸውም ባሻገር አጥብቀው ያበረታቱኛል። እንዳውም አንዳንድ ጊዜ ህመም ቢጤ ጫን ሲለኝና ድካም ሲበረታብኝ ህፃናቱ እንዳይጉላሉና እንዳልጨነቅ ብለው እርሳቸው ያስቀራሉ።" አሉኝ።

ወ/ሮ ሸምሲያ ቁርአን በማቅራት ላሳለፏቸው ረዥም አመታት በእጅጉ እንደሚያስደስታቸው አውግተውኛል። "አየህ" አሉኝ በጣፋጭ አንደበታቸው "ሌሊቱን ታምሜ አድሬ ጠዋት ተማሪዎቼ ሲመጡ በሽታዬ ይለቀኛል። መቼም እነሱን በማቅራቴ የሚሰማኝን ደስታ እኔን አንድ አላህ ብቻ ነን የምናውቀው። "

እኒህ የተባረኩ ወ/ሮ በአሁኑ ጊዜ [1985] ከሁለት መቶ ህፃናት በላይ በግቢያቸው ውስጥ ያቀራሉ። ልጆቹን ሰብስበው የሚያቀሩት በግቢያቸው ውስጥ በሚገኝ ጥላ ቦታ ላይ ነው። ይህ ቦታ ጠንከር ያለ ፀሐይ እንዳያጠቃቸው የሚከላከልላቸው ቢሆንም ቅሉ ዝናብ በሚዘንብበት ጊዜ ለማቅራት አመቺ አይደለም። ወ/ሮ ሸምሲያ እንደነገሩኝ ከሆነ አላህ በጭድ የተሸፈነ ጣሪያ ቢጤ ያለው ቤት እንኳ የመስራት አቅም ቢሰጣቸው በእጅጉ ይደሰቱ ነበር። ትልቁ ችግርና ጭንቀታቸውም ከፀሐይና ከዝናብ የሚከላከል ጎጆ ቢጤ መቀለሱና ህፃናቱም ተመቻችተው የሚቀመጡበት ወንበር አለማግኝታቸው ነው። ወ/ሮ ሸምሲያ ለዲናችን ከሚያበረክቱት ታላቅ አስተዋጽኦ አኳያ ያለባቸውን ችግር ከጎናቸው ሆኖ መቅረፉ የአህለል ኸይሮችን ትኩረት የሚሻ ይመስለኛል። የሚመለከተውም ክፍል ችላ ሊላቸው አይገባም ባይ ነኝ። "

_
በነገራችን ላይ ኡስታዛ አላህ ረጅም እድሜ ሰጥቷቸው አሁኑም በአክሱም ከተማ በህይወት አሉ። ከአንድ አመት በፊት Nur Quran Bank Islamic Association / ኑር የቁርኣን ባንክ ኢስላማዊ ማህበር ወደ አክሱም ተጉዘው በነበሩ ጊዜ በኔ ጥቆማ ቤታቸው ድረስ ሄደው እንደዘየሯቸው እና በነብዩ ሙሐመድ ሰላዋት ሲያወርዱ ቀርጿቻዋል።




~

ይህ የምድራችን ትልቁ ፍጥረት የሆነው ሰማያዊ ዓሳ ነባሪ ነው። ቁመቱ 30 ሜትር ይደርሳል። ክብደቱ 180ሺህ ኪሎግራም ይመዝናል። ይህም በአማካኝ 33 ዝሆኖች ያህል ማለት ነው። ልቡ ብቻ ቁመቱ 1.5 ሜትር ሲሆን ክብደቱ 180ኪሎግራም ነው። የሰው ልጅ የልቡን ያህል እንኳን ክብደት የለውም። እንዲሁም በአንዱ የልቡ የደም ቧንቧ ውስጥ ገብቶ በሌላኛው መውጣት ይችላል።

ይህ ግዙፍ የአላህ ፍጥረት ታዲያ ጌታውን ከመታዘዝ አይኮራም። ሰው ግን ከሁሉም በላይ ነኝ ብሎ ይንጠባረራል።

አላህም እንዲህ አለ፦

«በምድርም ላይ የተንበጣረረክ ሆነህ አትሂድ። አንተ ፈፅሞ ምድርን አትሰረጉድምና። በርዝመትም ፈፅሞ ጋራዎችን አትደርስምና።»
(ኢስራዕ 37)


Forward from: ካነበብኩት
🍃 ዱ ኒ ያ 🍂


👑          ⭐️             ⚡️
ٰ    • ○ ° 🌹🌹🌹• ○ °• ○ °• ○ °
 • ○    🌹🌹🌹🌹    • ○ °  👈አበባውን
• ○ °🌹🌹🌹🌹🌹           በመንካት• ○ °
  • 🌹🌹🌹🌹🌹🌹    ብቻ ምርጥ
○ 🌹🌹🌹🌹🌹🌹    የሱና 𝙘𝙝𝙖𝙣𝙣𝙚𝙡  ° :.
   🌹🌹🌹🌹🌹🌹         ያገኛሉ📡
 • 🌹🌹🌹🌹🌹      ° :.   * • ○       
• ○  🌿🌹🌹🌿      
  • ○ °   🌿🌿            👈
     •        🌿   • ○ °        🌿🌿
 • ○ °        🌿     • ○ ° 🌿🌿🌿
   • ○ °         🌿       🌿🌿🌿🌿
    • ○ °          🌿  🌿🌿🌿🌿🌿
        • ○ °       🌿   🌿🌿🌿🌿
      • ○ °         🌿  🌿🌿🌿
          • ○ °     🌿  🌿° :. * • ○
         °• ○ °      🌿° :.   * • ○
                    🌿° . °☆  . * ● ¸
.    ★  🌿° :.   * • ○ °
        ° .     🌿. * ● ¸
                  🌿       በቀላሉ ይቀላቀላሉ ።
☆  . * ● ¸ .
★ ° . *   ° . °☆  . * ● ¸
.    ★  ° :.   * • ○

🅰️🅰️🅰️⭐️✅🔗🔡🔡🔡
ለተጨማሪ ሀሳብ አስተያየት  ጥቆማ
@twhidfirst1 ⭐️🔗🔡🔡🔡




➡️ኢህሳን jobs Advertising

⚙ይህ ቻናል በሀገር ውስጥ ያሉ ስራ አጥ
            ወንድም እህቶች
በአላህ ፍቃድ  የስራ ማግኛ ሰበብይሆን ዘንድ
ታስቦ የተከፈተና የስራ ማስታወቂያ የምንለቅበት
አዲስ ⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️ ነው  ✅

በቻናሉ ያለምንም ክፍያ የስራ ማስታወቂያ
የሚለቀቅበት ቻናል ሲሆን

እናንተም ወደቻናሉ በመቀላቀል የቻናሉ
አባል ሁኑ እናንተም ይህንንም ቻናል
ሼር በማድረግ የቻናሉን እድገት አስቀጥሉ

አላማችን ወንድምና እህቶቻችን ስራ አጥ
እንዳይሆኑ ሰበብ ማድረስ ነው
🔗ተቀላቀሉ ✅

https://t.me/ihsan_jobs
https://t.me/ihsan_jobs


በሰው ተፈጥራዊ ቅርፅ ላይ አንድ ነገር ቢጨመርበት እንኳን አያምርም። እንዲሁ አንድ ነገር ቢቀነስ ያስጠላል።

የዓለም ሰዓሊዎችና ዲዛይነሮች ተሰባስበው በሰው ቅርፅ ላይ አንድ የሚያስውብ ነገር እንፍጠር ቢሉ አይችሉም። ወይም ይህ አያስፈልግም ብለው ቢቀንሱ ያስጠላልም፥ እንዲሁም ይበላሻልም።

ሌላው ቀርቶ ከሰው ተፈጥሮ ጋር የማይመሳሰል አዲስ ነገር እንኳን መሳል አይችሉም። ምሳሌ ስላልታወቁ ፍጥረታት (Aliens) የተሰሩ የአሜሪካ ፊልሞችን ካያችሁ ሁሉም ኤሊዬንሶች ከሰው ጋር የሚመሳሰሉና የሆነ ተፈጥሮ የጎደላቸው አስቀያሚ ፍጥረታት ናቸው። የዚህ ምክንያቱ በፊልሞቹ ላይ በርካታ “ጠበብት” ዲዛይነሮች ቢሰባሰቡም ከሰው የተለዬ አዲስ ፍጥረት መቅረፅ ስላልቻሉ ነው።

ይህ የሰው ልጅ በሌላ ሰው ወይም ፍጥረት ሊፈጠር ቀርቶ ሊሳል እንኳን እንደማይችል የሚያሳይም ነው።

አላህ የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ ቅርፅ እንከን የሌለው የተሟላና የተዋበ እንደሆነ ሲነግረን እንዲህ አለ፦

❝ቀረፃችሁም! ቅርፃችሁንም አሳመረ።❞
(አት-ተጋቡን 3)


~

ለአመታት ግንባታው ተቋርጦ የነበረው የደሴው አንጋፋው የአረብገንዳ መስጂድ የሚናራ ግንባታ ስራ ተጀምሯል። የመስጂድ አስተዳደሩና የከተማው መጅሊስ ባደረገው ትግል የማስፋፊያ ቦታ በቅርቡ መሰጠቱ የሚታወስ ነው። በርቱ…


~ ዛሬ በመዲናችን አዲስ አበባ


የጎሮው መስጅድ ኢማም መታሰራቸውን ሰምተናል። ምክንያቱም ደግሞ ለምን ዳእው ለምን አደረጋችሁ በማለት ጥዋት ላይ መታሰራቸውን ከቦታው የነበሩ አማኞች ተናግረዋል።

ዳእዋውን ያደረገውም ወንድም ወንድም ሬድዋን እኔ ነኝ ያደረኩት እሰሩኝ እኔንም በማለት እሱም አብሮ መታሰሩ ተሰምቶል። የታሰሩት ውጡ ቢባሉም ያ ሰረን አካል ለምን አሰረን በማለት ህዝቡም በቁጣ አንድ ላይ ይምጣና ያናግረን የከሰሰንም ካለ ይምጣ በማለት በፖሊስ ጣቢያ እንደታሰሩ ተሰምቶል


የነፃነቱ ጉድጓድ ባለ ድል!

ሴፕቴምበር 6/2021 ማለዳ ላይ እስራኤላዊያኑን ያስደነገጠ አንድ ክስተት ተከስቶ ነበር።ወራሪው "የብረት ቁልፍ" ብሎ ከሚጠራው እጅግ ጥብቅ ቁጥጥር ከሚደረግበት የጊልቦአ እስር ቤት ስድስት ታሳሪዎች ማምለጣቸው ተሰማ።በየት በኩል አመለጡ ተብሎ ሲፈለግ ወደ እስር ቤቱ የሚወስድ ረጅም ጉድጓድን ያገኛሉ።ታዲያ ታሳሪዎቹ ረጅም ቀናትን ከፈጀ ቁፋሮ በኃላ ከእስርቤቱ ማምለጥ ችለዋል።ይህ በወቅቱ የእስራኤል የደህንነት መረብን መበጠስ የቻለ ታላቅ ጀብዱ ሆኖ ተወርቶ ነበር።ታዲያ ይህን ታላቅ ሚሽን የመራውን የሹሀዳኡል-ቁድስ ብርጌድ አመራር የነበረው ዘከሪያ አዝ-ዙቤይዲና ሌሎችም ታሳሪዎች ከቀናት አሰሳ በኃላ በጠቋሚዎች ተባባሪነት ዳግም ይያዛሉ።
ዘከሪያ አዝ-ዙበይዲ ዳግም ሊፈረድበት በዳኛው ፊት ቆሞ የተናገረው ይህ ነበር:-
"አንዲት ክፍተት ካገኘሁ እጄን አጣጥፌ የምቀመጥበት ምክኒያት የለም።አሁንም ከእስር ወጥቼ ነፃነቴን ለማረጋገጥ እሞክራለሁ።"

ታዲያ ይህ ጀግና ከ3 ዓመታት የእስር ቆይታ በኃላ በፍልስጤማዊያኑ የትግል ቡድኖች ተፅዕኖ አንገቱን ቀና አድርጎ በበሩ በኩል ለመውጣት ችሏል።


የ #ዲላ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ኒቃብ ለብሰው እንዳይገቡ በመከልከላቸው #በመስጂድ ውስጥ ለመቆየት መገደዳቸውን ተናገሩ!!!

#አርባ_አራት የሚሆኑ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ኒቃብ ለብሰው ወደ ግቢው እንዳይገቡ እንደተከለከሉና አንዳንዶቹም ከአምስት ቀናት በላይ በመስጂዱ ውስጥ ለመቆየት መገደዳቸውን ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጹ።

ከአዲስ ስታንዳርድ ጋር ቆይታ ያደረጉ ተማሪዎች፤ ቀደም ባሉት ዓመታት ኒቃብ መልበስ ይፈቀድ የነበረ ቢሆንም ዩኒቨርሲቲው በቅርቡ “የደህንነት ስጋትን” በመጥቀስ ያለቅድመ ማስጠንቀቂያ ኒቃብ መልበስን እንደከለከለ ተናግረዋል።

በዲላ ዩኒቨርስቲ የሙስሊም ተማሪዎች ማህበር ሊቀመንበር የሆነው ኑረዲን አብደላ በበኩሉ ጉዳዩን ከዩኒቨርስቲው የስራ ሃላፊዎች ጋር በጽሑፍም ሆነ በአካል ለመፍታት የተደረጉ ተደጋጋሚ ጥረቶች መፍትሄ አለማምጣታቸውን ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግሯል።

አክሎም “በርካታ ሙስሊም ተማሪዎች ላለፉት አምስት ቀናት በመስጂድ ውስጥ ቆይተዋል። በዚህ ጊዜ ለፈተና መቅረብም ሆነ የሚጠበቅባቸውን አሳይመንት ለማጠናቀቅ አልቻሉም” ብሏል።


أشهد أنْ لا إله إلا الله وحده لا شريك له، وأشهد أن محمدًا عبده ورسوله

20 last posts shown.