✍️ከሁለት የጎንደር ተወላጅ ፌደራሎች ጋ ከአድስአበባ ፖሊስ ኮሚሺን በሰርቪስ ጉዞ ጀመርን ወደ ቂሊንጦ። ነገር ግን የኳራንታይኑ ቦታ የገቡ 3ቀን የሆናቸው እስረኞች ነበሩና ቂሊንጦ ስንደርስ እዚህ ማን አምጡ አላችሁ ከላይ አልተነገረንም ብለውን ተመለስን።
✍️ፌደራሎቹ ወደ አለቆቻቸው ደውለው የተፈጠረውን ነገሯቸው።አለቆቹም የሚወስዱብኝን ቦታ ነገሯቸው።
✍️አባ ሳሙኤል ይባላል።በወያኔ የመጨረሻ ጊዜ አካባቢ የተሰራ አድስ እስርቤት ነው።ሕንፃው ሲሰራ ሰፋ አድርጋችሁ ስሩት እናንተም ልትገቡበት ትችላላችሁ ብሏቸው ነበር አሉ በቀለ ገርባ😂
✍️ይህ አስፈሪ ውስጥ ከገባህ ከሰማይ በስተቀር ምንም የማይታይበት እስርቤት እንደደረስን ፌደራሎቹ ፖሊሶቹን አናገሯቸው።አድስ ሰው አምጥተናል ሲሏቸው አናስገባም እነዚህ ኳራንታይን የጀመሩት ሳይጨርሱ አሉና መቸም እርስበርስ ደርቢ ናቸውና ተጨቃጨቁ ተጣሉ የሲጅኑ ፖሊሶች ከላይ ትእዛዝ አልደረሰንም በማለት ገገሙ።እዛው የለመድኩት ፖሊስ ኮሚሽን ይመልሱኝ ይሆን ብዬ አሰብኩ።
✍️ወቅቱ እየሮጠ ነው ፌደራሎቹም ተበሳጩና ለአለቆች ደውለው ቂሊንጦም አባሳሙኤልም አናስገባም አሉ ልንመልሰው ነው በማለት ነገሯቸውና መንገድ እንደጀመርን አይይ ተመለሱ እናናግራቸዋለን የሚል ትእዛዝ ተሰጣቸው።
✍️በጣም ተንገላታሁ ፌደራሎቹም አሳዘንኳቸው ፆመኛውን አሰቃየነው በቃ ፆሙን ፍታ ምግብ እናብላህ እምነታችሁስ አስቻጋሪ ነገር ላይ ማፍጠርን ይፍቅድ የለ አሉኝ የጎንደር ተወላጅ ክርስቲያን ናቸው። እዛ እርስበርስ ወገናዊነት ስላለ ለእኔ ወገናዊነት ተሰምቷቸው እኮ ነው።
✍️መግሪብ እየደረሰ ነው።ቂሊንጦ አምጡትና አሻራ ሰጥቶ አባሳሙኤል እኛው እንወስደዋለን ተብለው ቂላንጦ ወስደው አስረከቡኝና እቅፍ አድርገው ቻው አሉኝ ብዙ ጊዜ መሕከማ ስለአጀቡኝ ተቀራርበናልና።
✍️ቂሊንጦ አሻራውንም ተስዊሩንም ጨርሰው ወደ አስፈሪው አባሳሙኤል በፓትሮል ኡፍፍ ይች ፓትሮል ምናለ በሰርቪስ ቢወስዱኝ
✍️አባሳሙኤል ስንደርስ ፉጡር ደረሰ ነገር ግን ሬሽን ተሰጥቶ አልቋል። እስረኛውም ጭጭ አድርጎ በልቶ ጨርሷል።
✍️ፍጡር ሲደርስ ምግብ እንዳለ ሲሰማህ ትንጠራዘዛለህ ግን ምግብ አለመኖሩን ስታውቅ ደግሞ ነገሩ ውስብስብ ነው😂 ፖሊሶቹ አሁን ማፍጠሪያ ከየት ይመጣል ምን እናድርግ እያሉ ሲጨቃጨቁ ድንገት ከቂሊንጦ አመራሮች መጡ ለመሆኑ የየት አገር ልጅ ነህ ወሎየ ነህ ታስታውቃለህ ግን ወሎ የት ሲሉኝ ነገርኳቸው እንዴ የአገሬ ልጅ ሲል አንዱ ሌላው እኔ የተንታ ልጅ ነኝ ግባ አሁን ማፍጠራያ ገዝተን እናመጣልሓለን አሉኝ ኦኦኦ ምቾት
✍️የተመደብኩበት ክላስ ስገባ አልጋው ሙሉ ነውና ለዛሬ በቃ መሬት ላይ ተኛ አሉኝ 👉ደቦቃ እንለዋለን በሲጅን ቆንቋ።
✍️ወቅቱ ቢያልፍም ፍጡር ፖሊሶቹ በየአይነት ከሚሪንዳ ጋ አመጡልኝና አፈጠርኩ።الحمد لله
ይቀጥላል
እረ ይሄ ነገር በpodCast ይሁን ዋይ አያልቅምኮ