"ተማሪ በሞተ ፣ በሰባት አመቱ
ተምሮ ይመጣል ፣ ትላለች እናቱ"... የሚል ግጥም በተመስገን ገብሬ "ህይወቴ" የሚለው መፅሀፍ ውስጥ ማንበቤን አስታውሳለሁ።
ይሄን hazy memory ወልወል ወልወል ካደረጉት የማያሳዮት ነገር የለም መቸስ። ልክ የዛሬ ሰባት አመት ከምናምን ሩቅ አዳሪ ልቤን እና ወፍራም ተስፋዬን ከቡራቡሬ ብርድ ልብሴ ጋር ተሸክሜ ህክምና ትምህርት ገባሁ(ሁለቱን እንጃ እንጂ ቡራቡሬ ብርድ ልብሴ እስካሁን አለ)።
ከዚያስ
የመጀመሪያዎቹ ሰሞናት እንደዋዛ አለፉ። ጉንጭ አልፋ ወሬህን እያወራህ፣ ምግብ እየበላህ ፣የፈረደበት F.R.I.E.N.D.S እያየህ ፣ ከfriends ጋር ባስተማሪህ እያሾፍክ ፣ ሲስተሙን እየተቸህ፣በታክሲ ሄደህ ከተማ እያየህ ፣ ቤተስኪያን እየሄድክ ጊዜው ይሄድልሃል።
ከዚያ ግን ባጭሩ ወይ ትምህርት ይከብድሀል ወይ በጣም ያስጠላሀል። Anxiety በገበሬ እጁ በግራም በቀኝም በጥፊ ያጮልሀል። ወይ ድብርት የተባለች አዚማም ጋኔን ትጠቅሳሀለች። ከዚያ ጭልጥ ብለህ ልትጠፋ ትችላለህ።
medicine ይለዋውጥሀል። ዲያቆን ሆነህ ገብተህ existential ሆነህ ልትወጣ ትችላለህ። የLil Wayne አድናቂ ከነበርክ እነሆ እማሆይ ፅጌማርያም ገብሩ ማረፊያህ ሊሆኑ ይችላሉ። ፈጣን ነው ተብለህ ገብተህ ምናልባት ቀርዛዛነትህን እዚያ ቀብረር ብሎ ታገኘዋለህ። Genius አልነበርኩ እንዴ ብለህ ታስብ ታስብና የሆነ ቀን ለካ ትዝ ሲልህ 12ተኛ ክፍል ስትጨርስ cerebral cortexህን መኝታቤትህ ኮመዲኖ ላይ አስቀምጠኸው የመጣህ ይመስል ደንቁረሀል። አንዳንዴ የሆነ ኮርስ እምወድቅ ከመሰለኝ ራሴን "አይዞህ እንኳን አንተ fieldኡስ ወድቆ የለ?አንተ ከፊልዱ ትበልጣለህ?" እለዋለሁ።😁
ማጣፊያው ሲያጥርህ ከዚህኛው self help ወደዚያኛው self help book እያማረጥክ ይሄን motivation ታሻምደዋለህ። ከሞተ የሰነበተ inner strengthህን ትከሻውን ጨምድደህ "ተነስ እንጂ" ትለዋለህ። (አሁን ነው የገባኝ እንጂ አሪፉ self help bookስ ለካ Harrison ነበር።)
Medicine ትምህርቱ ሌሊት 10:15 ላይ እንደሚወጥርህ ሽንት ነው። ወይ ተነስተህ ሸንተኸው አትገላገል ወይ በሰላም አያስተኛህ እንዲሁ እያመነታህ ስትቁነጠነጥ የሚያሳድርህ አይነት። አንዳንዴ ስህተትህ ማለቂያ የሌለው ይሆናል። ተሰፋ የሚባለውን ነገር ቆርጠህ cremate ታደርገውና Rockbottomህ ላይ ፈርሸህ ቁጭ ልትል ትችላለህ። It is what it is ብለህ።
እና በስተመጨረሻ አሁን ከነዚህ ሁሉ አመታት በኋላ ይኼን ነገራ ነገር ልሰናበተው ስል ገረመኝ። እዚህ መድረሴም ትንሽ አሳቀኝ። Woody Allen እንደሚለው "comedy is tragedy plus time" ነውና ነገሩ ባለፉት አመታት ጥሩ የሚባል ጊዜ ባይኖረኝም ከዚህ ሁሉ በኋላ ግን አለመሳቅ አልቻልኩም። መሳቅ ችዬ በመውጣቴም ትንሽ ደስተኛ ነኝ። ያለፈ ሁሉ ያስቃልና። መስፍን ወንድወሰን የተባለ ገጣሚ እንደሚለው ነው የዚህ አለም ነገር እንግዲህ
" አልሻገር አልራመድ፣ ከእዳ ባህር ከቀውስ ወጀብ
ብቻ ማለት ራስ ይዞ፣ ሲመጣ እግዞ ሲሄድ አጀብ።"
Dawit Tefera, Medical Intern at SPHMMC
@HakimEthio