አማኝ የሆነ ሰው ወንጀልን ከሰራ...
———
ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚየህ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ብለዋል:
አማኝ የሆነ ሰው ወንጀልን ከሰራ በአስር ምክንያት ቅጣቷ ከሱ ትከለከልለታለች።
① ወደ አላህ ተውበት አድርጎ ሊመለስ ነው፣ አላህም ይቅር ይለዋል፣ ከወንጀሉ ወደ አላህ የተመለሰ ሰው ምንም አይነት ወንጀል እንደሌለበት ነው።
② አለያም አላህን ምህረት ሊጠይቅ ነው፣ አላህም ይምረዋል።
③ አለያም መልካም ስራዎችን ሊሰራ ነው፣ መልካም ስራዎች ወንጀልን ያስወግዳሉና።
④ አለያም ሞቶም ይሁን በህይወት እያለ አማኝ ወንድሞቹ አላህን (ተባረከወተዓላ) ሊለምኑለት ነው።
⑤ አለያም አላህ ዘንድ ሊጠቅመው ከሚችል መልካም ስራቸው ስጦታ ሊያበረክቱለት ነው፣ (ለሱ ብሎ ሰደቃ መስጠት፣ ዑምራ ማድረግን… ይመስል።)
⑥ አለያም ነቢዩ ﷺ ከአላህ ሊያማልዱት ነው።
⑦ አለያም አላህ (ተባረከወተዓላ) ወንጀሉን ሊያስምርለት የሚችልን ሙሲባ ሊያደርስበት ነው።
⑧ አለያም በቀብር ውስጥ ወንጀሉን ሊያብስለት የሚችልን ቅጣት ሊቀጣው ነው።
⑨ አለያም የቂያማ እለት በመሰብሰቢያው ሜዳ ከቂያማ ሁኔታዎች ወንጀሉን ሊያስምርለት የሚችልን ፈተና ሊፈትነው ነው።
10, አለያም የአዛኞች ሁሉ አዛኝ እንዲሁ ሊያዝንለት ነው።
ይህቺ አስር ነገር የሳተችው ሰው ነፍሱን እንጂ ማንንም አይውቀስ‼
[መጅሙዕ ፈታዋ ጥራዝ 10/45]
✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)
#join ⤵️ ቴሌግራም ቻናል
https://telegram.me/IbnShifa