#ክፍል_14
الحديث الخامس عشر
#15ኛው_ሐዲሥ: #መልካም_ተናገር፣ #ካልሆነ_ዝም_በል
عن أبي هريرة رضي الله عنه، عن رسول الله ﷺ قال: "من كان يؤمن بالله واليوم الآخر فليقل خيرا أو ليصمت، ومن كان يؤمن بالله واليوم الآخر فليكرم جاره، ومن كان يؤمن بالله واليوم الآخر فليكرم ضيفه" رواه البخاري ومسلم.
ከአቡ ሁረይራ رضي الله عنه ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ "በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምን የሆነ ሰው መልካም ይናገር፤ ወይ ዝም ይበል። በአላህና በመጨረሻ ቀን የሚያምን የሆነ ሰው ጎረቤቱን ያክብር። በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምን የሆነ ሰው እንግዳውን ያክብር።" ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። [6018] [47]
#ሐዲሡ_ያለው_የላቀ_ደረጃ፦
➡️ ታላቁ የማሊኪያ ኢማም ኢብኑ አቢ ዘይድ አልቀይረዋኒ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦ "ሁሉም ስነ ምግባራት ከአራት ሐዲሦች የሚመነጩ ናቸው። (እነሱም፦) 'በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምን የሆነ መልካም ይናገር፤ ወይ ዝም ይበል' የሚለው የነብዩﷺ ንግግር፤ 'ከአንድ ሰው የኢስላም ውበት የሆነው የማያገባውን መተው ነው' ማለታቸው፤ "አትቆጣ" የሚለው አጭር ምክራቸው እና 'አንዳችሁ ለወንድሙ የሚወደውን ለራሱ እስካልወደደ ድረስ አላመነም' የሚሉት ናቸው።" [ፈትሑል ቀውዩል መቲን፡ 49]
#ከሐዲሡ_የሚወሰዱ_ቀም_ነገሮች፦
✅ ሁሌም መልካምን መናገር የሚበረታታ እንደሆነ፣
✅ ፍሬ ከሌለው ወሬ ዝምታ እንደሚመረጥ፣
✅ መልካም መናገር፣ ጎረቤትንና እንግዳን ማክበር ከኢማን እንደሆነ፣
✅ ኢስላም በሰዎች መካከል መከባበር ያለበት ጤናማ ማህበራዊ ህይወት እንዲኖር የሚያደርግ ውድ ሃይማኖት እንደሆነ ከሐዲሡ እንማራለን።
#ማሳሰቢያ፦
🛑 አንድ ጎረቤት ሙስሊም እና ዘመድ ከሆነ ከጉርብትና ሐቅ በተጨማሪ የኢስላምና የዝምድና ሐቅ አለው። ሙስሊም ግን ባዳ የሆነ ጎረቤት ደግሞ የጉርብትና እና የኢስላም ሐቅ አለው። ሙስሊም ያልሆነ ዘመድ ጎረቤት የጉርብትናና የዝምድና ሐቅ አለው። ሙስሊም ያልሆነ ባዳ ጎረቤት ደግሞ የጉርብትና ሐቅ አለው።
🛑 ከጎረቤትም በሩ ቅርብ በመሆኑ ወደ ቤት የሚገባውን እየተመለከተ ልቡ የሚንጠለጠል የሆነው ይበልጥ መልካም ሊዋልለት ይገባል። የጎረቤትን ሐቅ ከባድነት ከሚያመላክቱ ማስረጃዎች ውስጥ አንዱ ነብዩ ﷺ እንዲህ ማለታቸው ነው፦ "ጂብሪል በጎረቤት ላይ እኔን አደራ ከማለት አልተወገደም፣ ያስወርሰዋል ብየ እስከምጠረጥር ድረስ!!" [ቡኻሪ፡ 6015፣ ሙስሊም፡ 2624]
ታዲያ እንደዚህ ሐቁ ከባድ የሆነን ጎረቤት ማስቸገር፣ ለጎረቤት ስጋት መሆን ኢማንን ጥያቄ ውስጥ የሚከት ከባድ ጥፋት ነው። ነብዩ ﷺ በአንድ ወቅት "ወላሂ አያምንም! ወላሂ አያምንም! ወላሂ አያምንም!" አሉ። "ማነው እሱ የአላህ መልእክተኛ ሆይ?" ሲሏቸው "ጎረቤቱ ተንኮሉን የማያምነው (የሚሰጋው) ሰው ነው" አሉ። [ቡኻሪ፡ 6016]
🛑 የእንግዳ ሐቅ ደግሞ ከአቅም በላይ ለሆነ ወጭ ሳይዳረጉ ቤት ያፈራውን በማቅረብ፣ በፈገግታ በመቀበል፣ መልካምን በመናገር እንግዳው ዘና እንዲል እንዳይጨናነቅ ማድረግ ነው።
✍ ኢብኑ ሃሩን ከወላይታ ሶዶ በዱአ አትርሱኝ
በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር [ሀፊዘሁሏህ] የተዘጋጀ መጽሐፍ።
👉 የነወውይ አርባ ሐዲሥ ከኢብኑ ረጀብ ጭማሪ ጋር (ገጽ 38-40)
``ኢንሻአላህ ይቀጥላል``
👉 @Twehid12
👉 @IbnTaymiyyahrahimahullah