ሰውነቴን የሆነ ነገር የተጫነ መስሎኝ ስነቃ ዮሴፍ ቁሞ እያየኝ ነበር ምንድንነው ማነው የከፈተልህ በሩን እንዴ ክፍት እኮ ነበር ደሞ ቆንጅዬ ነሽ ብሎ መጠጋት ሲጀምር እየሸሸው ገፍጥሬ ላመልት ብትርምአልቻልኩም ቀና ስል ካሌብ አለ ወደ ጎን ደሞ ሮቤል ቁሞ እየሳቀ ነው እባካቹን ተዉኝ እባካችሁን
ብዙ ጊዜ በአይኔ ብቻ እያየው ተመኝቼ ሻለው ሃሃሃ እኔስ ብትል ስንት ዓመት ተንከባክቤ ይሄን ልጅ ነው ማገባው ብላ ጠፋች እናንተ እኮ ሳታገኙዋት ነው እኔ አለው አ ለስሙ ፍቅረኛ ተብዬ አንድ ቀን ገላዋን ያልቀመስኩ
እባክህ ሮቤል ምንም ቢሆን እኮ ይቅር ብዬሃለው አ ተወኝ እሱ እኮ ቀልድ ነበር ሃሃሃ
ደንግጬ ጩኬ ተነሳው ዮሴፍ ደንግጦ መቶ በሩን ሊከፍት ሲል ዝግ ማያ ማያ ደና ነሽ
ላብ በላብ ሁኘ እንደ ደነገጥኩ ከፈትኩለት ምንሁነሽ ነው
መጥፎ ሕልም አይቼ አትጨነኪ ሕልም እኮ ነው እናቴ ደሞ እናቴ እንዲ ትለኝ ነበር ከመጥፎ ሕልም በዋላ ደስ ሚል ሂወት ይመጣል...
አይቼው ግን እኮ እናትህ ከሞተች ቆይታለች አው ልጅ እያለው ስቃዥ ነው እንዲ ምትለኝ
ልወጣ ስል ነቃሽ ከፈለግሽ አብረን እንዋል ልብስ ቀይሪ ሳሎን ጠብቅሻለው
እሺ ብዬ ሻወር ወስጄ ጥቁር ከሚስ ከረጅም ቡኒ ካፖርት ከነጭ ጫማ ልብሼ ቁርስ በልተን ሥራ ሚፈርመው ነገር ፈርሞ ቀኑን ሙሉ ሲያዝናናኝ አንዴ ሲኒማ አንዴ ጣፋጭ ምግብ ሚሰራበት ጎዳና ሚባል ቦት ሲወስደኝ ሳናስበው መሸ
በህይወቴ በጣም ደስ ሚል ቀን ያሳለፍኩት ዛሬ ነው አመሰግናለው አለኝ
ከዚ በፊትስ
እሱ እንኳን ባላወራው ደስ ይለኛል አለኝ
እሺ ደስ ባለህ ሰዓት ማወራት ስትፈልግ ቅርብህ ነኝ አለው አልኩ
ፈገግ ብሎ አመሰግናለው አለኝ
እረ አይባልም
እሺ
****
በጠዋት ተነስቼ በመስኮት ምትገባውን ምትሽኮረመም ፀሐይ እያየው ሳምንቱን ሙሉ ዮሴፍ እኔን ለማዝናናት ያደረገውን የወሰደኝ ቦታ ያሳየኝ መልካምነትን እያሰብኩ ፈገግ ስል በር ተንኳኳ አቤት ግባ አልኩኝ ኦኦ እንዴ አልተዘጋጀሽም እንዴ ሰዓቱ እኮ ገና ነው ቢሆንም ቀድመን እንገኝ ብዬ እኮ ነው
ከኔ በላይ ወንድሜን ለማየት ጓጉቷል ለምን እንደሆነ ባይገባኝም ስለ እሱ እንዳወራለት ይጠይቀኛል እኔም ብለህኝ ነው ብዬ ምን አይነት መልካም ልጅ እንደሆነ ስነግረው አንድ ቀን አንቺ የምትየው አይነት ልጅ ከዚ በፊት አቀዋለው ልጁ ከኔ በ5 ዓመት ቢያንስ ነው ሲለኝ ምን አልባት እሱ ሊሆንም ላይሆንም ይችላል ብዬው ነበር እና ከኔ በላይ ሊያየው በጣም ጓጉቷል ዛሬም በጥዋት ካሌድን ብሎ አጣድፎ ከቤት አሶጥቶ አየር መንገድ በጊዜ ደርሰን ሁለት ሰዓት ሙሉ ጠበቅን ልክ ወንድሜን ሳየው እና ሳቅፈው ምን አይነት አጋጣሚ ነው ብሎ ወንድሜ ከዮሴፍ ጋር ተቃቅፈው መላቀስ ጀመሩ አላፊ አግዳሚ ሰው እኛ ላይ ሲሆን አይኑ በሉ ቤት ትጨርሳላቹ ብዬ ቤት ሄድን ልክ ከረጅም ጊዜ በዋላ እንደተገናኙ ፍቅረኛ ለረጅም ሰዓት አፍ ለአፍ ገጥመው አወርተው ሲያበቁ ወንድሜ ጥሩ ሰው ገጠመሽ አቃለው ወንድሜ አንተን እንዴት ጓጉቶ ሲጠብቅህ እንደነበር እኮ ባይገርምሽ በህይወቴ የማረሳው ትልቅ ውለታ ነው የዋለልኝ ሲል እረ ተው እንጂ እንዲ አትበል
ወንድሜ እና ዮሴፍ የልብ ጓደኛ እንደነበሩ እና ዮሴፍ ሲሰደድ እንደ ተለያዩ ሲነግሩኝ ያኔ ዮሴፍን ደፍሬ ባወራው ኑሮ ወይ እሱ ደፍሮ ቢያውራኝ ዛሬ ሳይሆን ያኔ ነበር ምንገናኘው ከወንድሜ ጋር እያልኩ ባላወራናቸው ስሜቶች ውስጥ እንዴት እንደተሰቃየን እያሰብኩ ሂወት ያልተወሩ ስሜቶችን ይዛ ምታሰቃይ ህመም ነች ከዛ አልፎ ደሞ ደስታ ነች ልክ እንደ ሕልም ቅዥት.....
ሶስት ዓመት አለፈ ከዮሴፍ ጋር እየኖርኩ ግን እስካሁን ምንም አይነት ይሄ ነው ማይባል ፍቅር ግኑኝነት ውስጥ አይደለንም እሱም ዝም እኔም ዝም
አንድ ቀን ማያ አለኝ
አቤት አልኩ የሆነ ነገር ልነግርሽ ነው
ምን ዛሬ ማታ እራት ላይ
እሺ ብዬ ስሽቀረቀር ዋልኩ
ማታ እራት እየበላን ካሁን አሁን ታገብኛለሽ አለኝ ስል
ማያ ካሁን በዋላ አንድ ላይ መኖር አንችልም
ለምን
ላገባ ነው
የምር
አው ልነግርሽ ያለቻልኩት እወነት መሆኑን ላጣራ ብዬ ነው ይቅርታ
ስሜቶቼን ሳላወራ ይሄው እድሜ 20 መጨረሻ ገባ እጣዬ ይመስል በወንድ አልታደልኩም
እሺ ቤት ፈልጌ ወጣለው ሚያገባትን ሴት አሳየኝ ስለው የሜላትን ፎቶ አሳየኝ
ራስህን ሀብትህን ጠብቅ ምንም አልልህም
ቻዎ ብዬ ጥዬ ሄድኩ
ያልተወሩ ስሜቶቼን ይዤ ከወንድ ዘር ሸሽቼ......
ተፈፀመ ::
Nuhamin (Nami)
🥀ᴊᴏɪɴ & ꜱʜᴀʀᴇ🥀
🔔
@Kurach_Kalat💭
📣
@Kurach_Kalat💬