Forward from: The Federal Supreme Court of Ethiopia
ጉባዔው በ56 አቤቱታዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ሰጠ።
---------------------------------------------------------
የኢፌዴሪ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ሐሙስ ህዳር 05 ቀን 2017 ዓ.ም ባደረገው መደበኛ የጉባዔ ውይይት 56 በሚሆኑ የሕገ መንግሥት የትርጉም አቤቱታዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ፣ የውሳኔ ሐሳብና አቅጣጫ አስቀምጧል።
አጣሪ ጉባዔው በጽ/ቤቱ የሕግ ተመራማሪዎች እና በንዑስ አጣሪ ጉባዔ አባላት ተገቢውን ምርመራ እና ማጣራት ተደርጎባቸው ከቀረቡለት የሕገ መንግሥት የትርጉም አቤቱታዎች መካከል በ56ቱ ላይ የተወያዬ ሲሆን ከእነዚህም መካከል 53 የሚሆኑት ሕገ መንግሥታዊ ጥሰት አልተፈፀመባቸውም በሚል እንዲዘጉ ወስኗል።
በሌላ በኩል በመ.ቁ 3385/10 ላይ የተጠቀሰና በፌዴራል ቤቶች የቀረበ የቤት ክርክርን የሚመለከት አንድ አቤቱታ ላይ ጉባዔው ሕገ መንግሥታዊ ጥሰት ተፈፅሟል በሚል ለፌዴሬሽን ም/ቤት የውሳኔ ሐሳቡ እንዲላክ የወሰነ ሲሆን በአንድ አቤቱታ ላይ ደግሞ በተጠሪ ምላሽ እንዲሰጥበት፤ ሌላ አንድ ጉዳይ ደግሞ ጉዳዩ ተጣርቶ በቀጣይ እንዲቀርብ ይደር በሚል አቅጣጫ ተሰጥቶባቸዋል።
የኢፌዴሪ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ