የኤርትራው ባለሥልጣን የቢቢሲውን ዘገባ “ሃስት” ሲሉ ገለጹ
የቢቢሲ ሶማሊኛ ቋንቋ አገልግሎት፣ አብዱልቃድር ኢድሪስ የተባሉና ‘በኤርትራ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካና ሶማሊያ ጉዳዮች አማካሪ’ መሆናቸው የተገለጸ ባለሥልጣን በኢትዮጵያና በሶማሊያ መካከል አንካራ ላይ የተደረሰው ሥምምነት እንደሚያሳስባቸው ገልጸዋል የሚል ዘገባ ማውጣቱን ተከትሎ፣ የኤርትራው ማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገ/መስቀል "በተጠቀሰው ስም የሚጠሩ ባለሥልጣንም ሆነ በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የተባለው ቢሮ አለመኖሩን" ለቪኦኤ አፍሪካ ቀንድ አስታውቀዋል። ቢቢሲ ሶማሊኛ ባለሥልጣኑ “ኢትዮጵያ የምትሻው የባሕር ኅይል መሠረት እንጂ የባሕር አቅርቦት አይደለም” ሲሉ መናገራቸውን ጠቅሷል። “ሶማሊያ ለኢትዮጵያ የባሕር መሠረት የምትሰጥ ከሆነ፣ ኤርትራ ከሶማሊያ ጋራ ያላትን ግንኙነት እንደገና ታጤናለች” ሲሉ አብዱልቃድር ኢድሪስ የተባሉት ባለሥልጣን...
via የአሜሪካ ድምፅ (author: voadigital@voanews.com (ቪኦኤ ዜና))