Maraki News


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Education


Addisababa, Ethiopia🇪🇹
👇ማስታወቂያ ለማሰራት
@Adis_pro

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Education
Statistics
Posts filter


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
በአሜሪካ ላስ ቬጋስ ነዋሪ የሆኑት አንድ ቤተሰብ ሶስት ሜትር ርዝመት ያለው ሰው መሳይ ነገር በጎሮዋቸው እንደመጣና በደህንነት ካሜራ እንደተቀረፀ ተናግረዋል።

በአሜሪካ ታዋቂው የፎረንሲክ ሳይንቲስት ስኮት ሮደር በላስ ቬጋስ ውስጥ ያለውን የባዕድ ቪዲዮ ትክክለኛነት አረጋግጠዋል።
☑️ @MarakiNews ☑️


የ Notcoin ዋጋ ዛሬ 9 ሰአት ላይ በተለያዩ የDigital Currency መገበያያ መተግበሪያዎች ላይ ይፋ ይደረጋል።

ኖትኮይን በቅርቡ ተወዳጅ እየሆነ የመጣ ጨዋታ ሲሆን የስልክ ስክሪንን በመንካት ሳንቲም የሚያገኙበት ነበር። በዚህ እንቅስቃሴ ወደ 35 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ኖትኮይንን ሰብስበዋል።

ዛሬ 9 ሰአት ላይ ባይናንስን ጨምር በተለያዩ Digital Cryptocurrency exchange ሲስተሞች ላይ List የሚደረግ ሲሆን ከዛ በኃላ ወደ ሌላ Crypto መቀየር መሸጥ እና መግዛት እንደሚችሉ ታውቋል።

ኖትኮይን ያመለጣችሁ ሌላ ተመሳሳይ verified የሆነ ስላለ በዚህ ሊንክ በመግባት እና ተጫውቶ ሳንቲሞችን በማጠራቀም ይፋ ሲደረግ ወደብር መቀየር እንደሚችሉ እናሳውቃለን።
ሊንክ👇👇
https://t.me/tapswap_mirror_bot?start=r_985021045

☑️ @MarakiNews ☑️


2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና መርሐግብር ይፋ ሆኗል፡፡

መርሐግብሩ ከትግራይ ክልል ውጪ በሁሉም ክልሎች እና በሁለቱም የከተማ አስተዳደሮች በወረቀት እና በበይነ መረብ ፈተናውን ለሚወስዱ ተፈታኞች እንደሚያገለግል የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከሐምሌ 3-5/2016 ዓ.ም ለማኅበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች፤ ከሐምሌ 9-11/2016 ዓ.ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ይሰጣል።

(መርሐግብሩ ከላይ ተያይዟል።)
☑️ @MarakiNews ☑️


Telegram Premium መግዛት ለምትፈልጉ
    ⭐ 1 Month
    ⭐ 3 Month
    ⭐ 6 Month
    ⭐12 Month

📩 •➤ Contact @Adis_pro
0954190018


ለአዲስ አበባ (6ኛ፣8ኛ እና 12ኛ) ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች አጭር መረጃ

☑️የ8ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 4-5/10/2016 ዓ.ም ይሰጣል(ፈተናው የ8ኛ ክፍልን ብቻ ይሸፍናል)

☑️የ6ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ  12-14/10/2016 ዓ.ም የሚሰጥ ይሆናል!!(ፈተናው የ6ኛ ክፍልን ብቻ ይሸፍናል)

☑️የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች በአዲስ አበባ   በበይነ መረብ (Online) ብቻ በተመረጡ ት/ቤቶች ይሰጣል::

☑️የ12ኛ ክፍል(Social )ፈተና ከሐምሌ 3-5/2016 ዓ.ም በተመረጡ ት/ቤቶች  ይሰጣል::
(ፈተናው ከ9ኛ-11ኛ ክፍል  በነባሩ ስርዓተ ት/ት(ከኢኮኖሚክስ በስተቀር ) እና 12ኛ ክፍል በአዲሱ ስርዓተ ት/ት እንዲሁም ኢኮኖሚክስ በአዲሱ ስርዓተ ት/ት ይሸፍናል

☑️የ12ኛ ክፍል(ተፈጥሮ ሳይንስl)ፈተና ከሐምሌ  9-11/2016 ዓ/ም በተመረጡ ት/ቤቶች   የሚሰጥ   ይሆናል(ፈተናው ከ9ኛ-11ኛ በነባሩ ስርዓተ ት/ት እና 12ኛ ክፍል በአዲሱ ስርዓተ ት/ት ይሸፍናል

☑️ተማሪዎች ይህንን መረጃ መሰረት በማድረግ አስፈላጊውን ዝግጅት አንድታረጉ::

ትክክለኛ መረጃዎችን በቻናላችን በኩል የምናደርስ በመሆኑ ሼር እና ሰብስክራይብ በማድረግ ለሌሎች ተማሪዎች ያሳውቁ።
@MarakiNews
@MarakiNews


ዛሬ ልደታ አዲስ አበባ

እንኳን አደረሳቹ
☑️ @MarakiNews ☑️


የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ከሰኔ 14 እስከ ሰኔ 21 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ፈተናውን 250 ሺህ ለሚደርሱ ተማሪዎች ለመስጠት ዝግጅት መደረጉንም ገልጿል፡፡

በሚኒስቴሩ የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ኤባ ሚጀና እንዳሉት፥ የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ተማሪዎች ትምህርታቸውን አጠናቀው ሲወጡ ሊኖራቸው የሚገባውን እውቀት፣ ክህሎትና አመለካከት ለመለካት የሚሰጥ ነው፡፡

የሚወጡ ጥያቄዎችም የየትምህርት ክፍሎች ምሩቃን እንዲኖራቸው የሚጠበቀውን እውቀት፣ ክህሎትና አመለካከት መሠረት አድርገው የሚዘጋጁ ናቸው ብለዋል።

ሚኒስቴሩ ፈተናውን ለመስጠት አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቁን ጠቅሰው፤ፈተናው ተዘጋጅቶ እንዲገመገም ተደርጓል ነው ያሉት።ከግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፈተናውን የሚወስዱ ተማሪዎች ዝርዝር በትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ተረጋግጦ ነው ወደ ሚኒስቴሩ የሚላከው ብለዋል፡፡

በፈተናው ሞባይል ይዞ የሚመጣና መታወቂያ ሳይዝ የሚመጣ ተማሪ ፈተናውን መውሰድ እንደማይችል ጠቅሰው፥ ተማሪዎች ይህን አውቀው ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ ይገባቸዋል ማለታቸውን ኢፕድ ዘግቧል።
☑️ @MarakiNews ☑️


በራሳችሁ ስም እና ኢሜይል የሚከፈት ቪዛ ካርድ በቅናሽ እኛ ጋር አለ
✅ከውጪ እቃዎችን ለማዘዝ
✅ለፌስቡክ ቡስት
✅የዩንቨርስቲ ክፍያዎች
✅የቪዛ አፕልኬሽን ክፍያዎችን
✅የኦንላይን ኮርሶችን ክፍያዎች
ሁሉንም መክፈል ያስችላል

በተጨማሪም Telegram Premium መግዛት ለምትፈልጉ
    ⭐ 1 Month
    ⭐ 3 Month
    ⭐ 6 Month
    ⭐12 Month

📩 •➤ Contact @Adis_pro
0954190018


✝ለክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ።

መልካም በአል
☑️ @MarakiNews ☑️


የአሜሪካ ዲቪ ሎተሪ (Diversity Visa) 2025 አሸናፊዎች ይፋ ተደርጓል።

ዲቪ (Diversity Visa) 2025 ማመልከቻ የሞሉ በ dvprogram.state.gov/ESC/ ብቻ Confirmation Number በማስገባት ውጤቱን መመልከት ይችላሉ።

መልካም እድል
☑️ @MarakiNews ☑️


የ2025 የአሜሪካ ዲቪ ሎተሪ ዛሬ ምሽት 1 ሰአት ላይ ይፋ የሚደረግ ሲሆን እንዴት ማየት እንደምንችል ሙሉ ቅደም ተከተሉን እንደሚከተለው አስቀምጠናል።

1⃣ ይህንን ሊንክ ተጭነው ወደ ድረገፁ ይግቡ 👉https://dvprogram.state.gov/ESC/Default.aspx

2⃣ Continue የሚለውን ይጫኑ።

3⃣ ማመልከቻ ሲያስገቡ የተሰጠውን የማረጋገጫ ቁጥር ያስገቡ። ለምሳሌ. 20251O0DZWY3DOV9

4⃣ በኤሌክትሮኒክ ዲቨርሲቲ ቪዛ መግቢያ ላይ ጥቅም ላይ የዋለውን የመጨረሻ ወይም የአያት ስም ያስገቡ።

5⃣ የተወለዱበትን ዓመተ ምህረት ያሰገቡ።

6⃣ የሚመጣሎትን ፊደል እያዩ ሁሉንም ያስገቡ።

7⃣ በመጨረሻም ሁሉን የተሟላ መረጃ አስገብተው ሲጨርሱ Submit የሚለውን በመጫን ውጤቶን መመልከት ይችላሉ።

ማሳሰቢያ ከአሜሪካ ኢምባሲ ነው እምንደውለው / ኢሜይል / ቴክስት የምንልከው"  በሚል የሚያጭበረብሩ አካላት ስለሚኖሩ አመልካቾች እንትጠነቀቁ አደራ እንላለን።

መልካም እድል
☑️ @MarakiNews ☑️


የአሜሪካ ዲቪ ሎተሪ (Diversity Visa) 2025 አሸናፊዎች ነገ ይፋ ይደረጋሉ።

ለዲቪ (Diversity Visa) 2025 ማመልከቻ የሞሉ በ dvprogram.state.gov/ESC/ ብቻ የማረጋገጫ ቁጥራቸውን በማስገባት ውጤቱን ወይም ማሸነፍ አለማሸነፋቸውን መመልከት ይችላሉ።

NB. የማረጋገጫ ቁጥር ማመልከቻው ሲሞላ የተሰጠ ነው። ይህ ቁጥር የጠፋበት Forgot Confirmation Number በማለት አስፈለጊ መረጃ በመሙላት በኢሜል አዲስ ቁጥር ማግኘት ይቻላል።

ውጤቱ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽት 1 ሰዓት ጀምሮ ይፋ ይሆናል።
☑️ @MarakiNews ☑️


የአዲስ አበባ ከተማ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ፥ ከትንሳዔ በዓል ጋር በተያያዘ " ህብረተሰቡ በየቤቱ የቁም እንስሳት እርድ በማካሄድ ወይም በየአካባቢው ቅርጫ በማድረግ የሚከፋፈልበት አሰራር ተከልክሏል " በሚል በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሐሰተኛ መሆኑ አሳወቀ።

ነገር ግን በየአካባቢው በሕገወጥ_መንገድ እርድ በመፈፀም ለሆቴሎች እና ለስጋ ቤቶች በማከፋፈል ተግባር ላይ የተሰማሩ አካላት የቁም እንስሳቱ ጤንነት ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ድርጊቱ በከተማው ነዋሪዎች ጤንነት ላይ ጉዳት የሚያደርስ በመሆኑ ጥብቅ ቁጥጥር ይደረጋል ብሏል።
☑️ @MarakiNews ☑️


የ2016 ዓ/ም የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና በሰኔ ወር መጀመሪያ የሚሰጥ ሲሆን ፈተናው ለ15 ቀናት በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ብቻ ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

70 በመቶ የሚዘጋጀው ፈተና በኦንላይንና በወረቀት ወይም በጥብቅ ቁጥጥር በወረቀት ይሰጣል ተብሏል።

ባለፈው ዓመት የተፈጠረውን ችግር ለመቅረፍ የሪሚዲያል ፈተናውን በሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ብቻ ለመስጠት ታቅዶ እየተሰራበት ነው።

ዘንድሮ 32,500 ተማሪዎች 50 በመቶ በላይ ውጤት በማምጣት በቀጥታ ዩኒቨርሲቲ ገብተው መደበኛ ትምህርት እየተከታተሉ ሲሆን ከ78 ሺህ በላይ ተማሪዎች ደግሞ በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ሪሚዲያል ትምህርት እየወሰዱ እንደሚገኙ ሚኒስቴሩ ለኢፕድ ከሰጠው መረጃ ተመልክተናል።
☑️ @MarakiNews ☑️


የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ 25 የክልል ከተሞች ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው።

በወረቀት ከሚሰጠው ፈተና በተጨማሪ የሚሰጠው የኦንላይን ፈተና ተማሪዎች ከቦታ ቦታ ሳይጓጓዙ በየአካባቢያቸው ቤተሰቦቻቸው ጋር እያደሩ ፈተናውን እንዲወስዱ እንደሚያስችላቸው የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አየለች እሸቴ ተናግረዋል።

የፈተና አሰጣጡን ስኬታማ ለማድረግ ባለድርሻ አካላት በቅንጅት በመስራት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ሚኒስትር ድኤታዋ ጠቁመዋል።

የኦንላይን ተፈታኞች ፈተናውን ከመውሰዳቸው በፊት ደጋግመው እንዲለማመዱ የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም ተገልጿል።
☑️ @MarakiNews ☑️


እንኳን ለዓለም አቀፍ የላብአደሮች ቀን አደረሳችሁ
Happy International Labour Day
☑️ @MarakiNews ☑️


ከካንሰር ህመም ጋር እየታገለ ያለው ስደተኛ በአሜሪካ የ1.3 ቢሊዮን ዶላር ሎተሪ አሸናፊ ሆነ

ከካንሰር ህመም ጋር እየታገለ ያለው የላኦስ ተወላጁ ስደተኛ በአሜሪካ 1.3 ቢሊዮን ዶላር የሎተሪ ጃክፖት አሸናፊ ሆነ።የ46 ዓመቱ ቼንግ ሳፋን ፓወርቦል በተሰኘው የሎተሪ ጃክፖት ጨዋታዎች እድለኛ መሆኑን የውድድሩ ባለስልጣናት ገልጸዋል።ቼንግ ዕድለኛ ያደረገውን የሎተሪ ቲኬት የገዛው በኦሪጎን ግዛት በፖርትላንድ ከተማ ከሶስት ሳምንት በፊት ነበር።

ግለሰቡ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ ግብር ተቀንሶ 422 ሚሊዮን ዶላር ያህል የሚደርሰው ሲሆን ይህንንም ከባለቤቱ እና ጓደኛው ጋር እኩል እንደሚካፈሉ አስታውቋል።“አሁን ቤተሰቤን አንበሻብሻለሁ። ለራሴም ጥሩ ዶክተር መቅጠር እችላለሁ” ሲል አስረድቷል።“ህይወቴ ተቀይሯል” ሲል ለሲቢኤስ አጋር የሆነው ኮይን የተናረው ቼንግ አምላኩ እንዲረዳው በጸሎት መማጸኑን አስረድቷል።

ቼንግ አክሎም ለቤተሰቡ ሲያልሙት የነበረውን ቤት መግዛት እንደሚፈልግ እና ፓወርቦል የሎተሪ ጃክፖት መጫወቱን እንደሚቀጥል ተናግሯል።“እንደገና እድለኛ ልሆን እችላለሁ” ሲል ተስፋውን አስረድቷል።ላለፉት ስምንት ዓመታት በኬሞቴራፒ ህክምና ውስጥ ያለው ቼንግ ከባለቤቱ እና ጓደኛው ጋር በመተባበር ከ20 በላይ የፓወርቦል የሎተሪ ቲኬቶችን መግዛታቸውን ተናግሯል።የሎተሪ ቲኬቶቹ አሸናፊ ቁጥሮች 22፣ 27፣ 44፣ 52፣ 69 እና ቀይ ፓወርቦል 9 ነበሩ ተብሏል።

በፓወርቦል ታሪክ ውስጥ አራተኛው ትልቁ የገንዘብ ሽልማት መሆኑ የተነገረ ሲሆን እስካሁን ድረስ በከፍተኛ ደረጃ የተቀመጠው በ2022 አሸናፊ የነበረው የ2.04 ቢሊዮን ዶላር ሽልማት ነው።የፓወርቦል የሎተሪ ቲኬቶች በ45 አሜሪካ ግዛቶች፣ በኮሎምቢያ እንዲሁም በፖርቶ ሪኮ እና በአሜሪካ የቨርጂን ደሴቶች እያንዳንዳቸው በ2 ዶላር ነው የሚሸጡት።የሎተሪ ቲኬቶች ዋጋ መጨመሩ ጋር ተያይዞ ከፍተኛ የቢሊዮን ዶላር ሽልማቶች በጣም የተለመዱ ሆነዋል።
☑️ @MarakiNews ☑️


የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 5 ለማህበራዊ ሳይንስ ፤ ከሐምሌ  9 እስከ ሐምሌ 11/2016 ዓ/ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች በበይነ መረብ (Online) እና በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በወረቀት ይሰጣል።

በወረቀት ላይ የሚፈተኑ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ከሰኔ 30 እስከ ሐምሌ 01/2016 ዓ/ም እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ከሐምሌ 6 እስከ 7/2016 ዓ/ም ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡ ይሆናል። 

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
☑️ @MarakiNews ☑️


በአዲስ አበባ በዛሬዉ እለት ባጋጠመ የጎርፍ አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት አልፏል

በዛሬው ዕለት ሚያዚያ 21 ቀን 2016 ዓ.ም ንጋት ላይ በቦሌ ክ/ከተማ በወረዳ 11 ወረገኑ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የጣለዉን ዝናብ ተከትሎ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት ማለፉን የአዲስ አበባ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታዉቋል።

የከተማ አስተዳደሩ ማስተር ፕላናቸዉን ያልተከተሉ የወንዝ ዳርቻ ግንባታዎች ህብረተሰቡን ለጎርፍ አደጋ እንደሚያጋልጡ በጥናት በመለየት ይህንን የአደጋ ስጋትና ተጋላጭነት በመሠረታዊነት የሚፈታ ፕላኑን የጠበቀ ዘላቂ የመፍትሄ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ አስታዉቋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ በደረሰው በዚህ ድንገተኛ አደጋ ምክንያት ህይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጿል::በመሆኑም ተመሳሳይ አደጋዎች እንዳያጋጥሙ ህብረተሰቡ ከከተማ አስተዳደሩና ከእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የሚተላለፉ የጥንቃቄ መልእክቶችን ተግባራዊ እንዲያደርግ አሳስቧል::

ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎት በ939 ህብረተሰቡ ፈጥኖ እንዲያሳዉቅ ጥሪ ቀርቧል፡፡
☑️ @MarakiNews ☑️


የ2016 ዓ.ም 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፤ " ፈተናው ሙሉ በሙሉ በኦንላይን ለመስጠት ባይቻልም በክልሎች በተመረጡ ከተሞች ለመስጠት እየተሠራ ነው " ብለዋል።

" በሁሉም ክልሎች ያሉ የተመረጡ ተማሪዎች በኦንላይን ፈተናቸውን ይወስዳሉ " ሲሉ አሳውቀዋል።

ቀሪዎቹ ደግሞ በተለመደው አግባብ ፈተናቸውን እንደሚወስዱ ገልጸዋል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር እሸቱ ከበደ በበኩላቸው ፤ " ፈተናው በኦንላይን ለመሥጠት የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተሠራ ነው " ብለዋል።

ተፈታኝ ተማሪዎች በሙከራ ፈተና እንዲለማመዱ እንደሚደረግ ገልጸዋል።

የአሰልጣኞች ስልጠና በመስጠት ተማሪዎች ተደጋጋሚ ስልጠና እንደሚሰጣቸው አመልክተዋል።

ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት ይጀመራል ብለዋል።
☑️ @MarakiNews ☑️

20 last posts shown.