ምዕራፍ 3 የደዕዋ ግልፅ መውጣት
ክፍል 23 ቁረይሾች በሐበሻ ስደተኞች ላይ ያደረጉት ተንኮል
ሙስሊሞች አምልጠዋቸው በራሳቸውም ሆነ በኢማናቸው ላይ ሰላምን አግኝተው ወደሚኖሩባት ሐበሻ መድረሳቸው ቁረይሾችን እረፍት ነሳቸው ። ወደ መካ እንድያስመልሷቸው በአዋቂዎቻቸው ሁለት ሰዎችን ወደ ሐበሻ ላኩ። እነሱም ዐምር ቢን አል አስ እና ዐብደላህ ቢን ረቢዓ ነበሩ። በዚያን ጊዜ ሽርክ ላይ ነበሩ።ሁለቱ ሰዎች ሐበሻ ከደረሱ በኋላ በረቀቀ ዘዴና እርምጃ ስራቸውን ቀጠሉ።በመጀመሪያ ከቀሳውስቱ ጋር ተገናኝተው ስጦታዎችን ሰጡዋቸው።አላማቸውንም ነገሩዋቸው።ማስረጃዎቻቸውንም አብራሩላቸው።ቀሳውስቱ ሐሳባቸውን ተቀበሏቸው፣ተስማሙበትም። ከዚያም ወደ ነጃሺ በመሄድ ስጦታ አበረከቱለት።
እንድህም አሉት፦
ንጉስ ሆይ! ሃይማኖታቸውን የለቀቁ ወደ አንተ ሃይማኖትም ያልገቡ እኛም ሆን አንተ የማናውቀው የሆነን ሃይማኖት የፈጠሩ ጅሎች ሰዎች ወደ አንተ አገር ሸሽተው ይገኛሉ።እነዚህን ሰዎች እንድትመልስላቸው ከአባቶቻቸው፣ከአጎቶቻቸውና ከዘመዶቻቸው የሆኑ ታላላቅ ሰዎች ወደ አንተ ልከውናል።በጥበቃቸውም እነሱ ይሻሏቸዋል። ባዩባቸው መጥፎ ነገርና በወቀሷቸው ነገርም ከሁሉም የበለጠ የሚያውቁት እነሱ (ዘመዶቻቸው)ናቸው።
ቀሳውስቱ በተጠነሰሰው ሴራ መሠረት ደገፏቸው። ነጃሺ ግን ውሳኔ ከመስጠቱ በፊት ቅድመ ጥንቃቄ አደረገ። ነገሩ ግልፅ እስኪሆንለት ድረስ ከሁለቱም ወገን ለመስማማት ወሰነ። ሙስሊሞቹን ጠርቶ ጠየቃቸው ይህ ከሕዝባችሁ በሱ የተለያችሁበት፣ወደ ሃይማኖቴም ሆነ ወደ ሌላ ማንኛውም ሃይማኖት የማትገቡበት የሆነ ሃይማኖታችሁ ምንድነው? አላቸው።
ጀዕፈር ቢን አቢ ጣሊብ ሙስሊሞቹን በመወከል ተናገረ፦
ንጉስ ሆይ! እኛ የጃሂልያ ሕዝቦች ነበርን።ጣዖትን የምንገዛ፣በክትን የምንበላ፣ ዝሙት የምንሰራ፣ ዝምድናን የምንቆርጥ፣ ጉርብትናን የምናበላሽ፣ከኛ ጠንካሮቹ ደካሞችን የምንበድል ነበርን። ዘሩን፣ እውነተኛነቱን፣ ታማኝነቱንና እውነተኛነቱን የምናውቀው መልእክተኛ ከኛው ውስጥ አላህ እስከላከልን ጊዜ ድረስ በዚህ አይነት ሁኔታላይ ነበርን። ወደ አላህ ጥሪ አደረገልን። አንድነቱን እንድንቀበል፣እንድንገዛው፣ እኛም ሆን አባቶቻችን ከአላህ ሌላ ስንገዛ የነበረውን ጣዖታትና ጅንጋይ እንድንተው ጥሪ አደረገልን።እውነትን እንድንናገር፣አደራ እንድናደርስ፣ዝምድናን እንድንቀጥል፣ በጥሩ ጉርብትና፣ወንጀልን ከመስራት እንድንቆጠብ አዘዘን። አላህን ብቻ እንድንገዛና እንዳናጋራበት አዘዘን። በሶላት፣በዘካ፣በፆም ሌሎች ኢስላማዊ ጉዳዮችንም ዘረዘረለት አዘዘንና ተቀበልነው።አመንበትም። ከአላህ ባመጣው ሃይማኖት ተቀበልነው።አላህን በብቸኝነት ተገዛን፣ በሱ ምንንም አናጋራም፣ ህዝባችን ድንበር አለፉብን ።አሰቃዩን ።በሐይማኖታችን ምክንያት ፈተኑን አላህ (ሱ.ወ)ን ከመገዛት ጣዖታትን ወደመገዛት ሊመልሱን ሲፈልጉና ስናደርግ የነበረውን መጥፎ ነገር መልሰን እንድናደርግ ሲያስገድዱን፣ በኋይል ሲያሸንፉን ፣ሲበድሉን፣ሲያስጨንቁንና በኛ በሃይማኖታችን መሃል በመግባት ከሃይማኖታችን ሳከለክሉን ወደ አንተ አገር መጣን፣ ከሌሎች አንተን መረጥን፣ጉርብትናህን ወደድን፣አንተ ዘንድ እንደማንበደል ተስፋ አደረግን ንጉስ ሆይ! አለ።
ነጃሺ ይህንን ሲሰማ ከቁርኣን የተወሰነ ነገር እንድያነብለት ጀዕፈርን ጠየቀው። ከሱረቱል ሠርየም መሀል አነበበለት። ነጃሺ ፁሙ በእንባ እስኪረጥብ ድረስ አለቀሰ። ከዚያም ነጃሺ ይህ ኢሳ(ኢየሱስ) ይዞት የመጣው ነገር(ሃይማኖት) ከአንድ ቀዳዳ(ሚሸካት)ነው የወጡት አለ።
ከዚያም ለቁረይሽ ተወካዮች ሂዱ ወላሂ በፍፁም እነሱን ወደናንተ አላስረክባችሁም።በፍፁም አላደረገውም አላቸውና ወጡ።
በሁለተኛው ቀን ዓምር ቢን አል ዓስ ሌላ ዘደ ቀየሰ። ለነጃሺ እንድህ አለ፦ እነሱኮ ስለ ኢሳ በጣም መጥፎ ይናገራሉ አለው።
ነጃሺ እንደገና ጠራቸውና ስለዚህ ነገር ጠየቃቸው። ጃእፈር እንድህ አለው፦ እኛ ስለ ኢሣ የምንለው ነቢያችን(ﷺ )የነገሩንን ነው። ኢሳ የአላህ ባሪያና መልእክተኛ ነው። አላህ በድንግሊቱ መርየም ያሳደረው የአላህ ሩህ (መንፈስ)እና የአላህ ቃልነው።
ነጃሺ አንድ የእንጨት ስባሪ ከመሬት አነሳና ወላሂ ኢሣ የዚህችን እንጨት ስባሪ ያክል አንተ ካልከው ነገር አላለፈም። ሂዱ እናንተ በሃገሬ ውስጥ ሰላምናችሁና። እናንተን የሰደበ ሰው ከሰረ፣እናንተን የሰደ በሰው ከሰረ፣ እናንተን የሰደበ ሰው ከሰረ። ከእናንተ ውስጥ አንዳችሁን አስቸግሬ በአፀፋው ተራራ ያክል ወረቅ እንድሰጠኝ አልፈልግም።አለ።
ከዚያም የቁረይሽ ተወካዮች ያመጡት ስጦታዎች እንድመልሱላቸው አዘዘ። ተዋርደውም ተሠለሱ።ሙስሊሞቹ በመልካም አገር መልካም ጉርብትና ኖሩ።
ይቀጥላል............
https://t.me/Menhaj_Asselefiya