ዓለምን ተጋፈጡ!
መድሎን የሚጠብቁ፣ ፈጣሪ እነርሱን ብቻ እንዲያግዝ፣ ዓለም ከእነርሱ ጋር ብቻ እንድትተባበር፣ የሚያውቁትም የማያውቁትም ሰው እንዲያግዛቸው የሚጠብቁ ሰዎች ከራሳቸው በላይ ምንም አይነት ጠላት የላቸውም። ዓለም ለማንም አታዳላም፣ ፈጣሪምም ማንንም ከማንም አይለይም፣ የሰው ልጅም እንዲሁ ሰውን ከሰው ለይቶ አይደግፍም። ነገር ግን ሁሉም አንድ ቅድመ ሁኔታ ይኖራቸዋል። የማይሞክርን ሰው በፍፁም አይደግፉም፣ አያበረታቱም። እርሱን የሚያደርገው ብቸኛው ፍጡር ከክብሩ ወርዶ ወደ እቶን እሳት የተጣለውና የሰውን ለውጥና እድገት የማይፈልገው ሰይጣን ብቻ ነው። ከሞከራችሁ፣ ከሰራችሁ፣ ከጣራችሁ፣ ምቾታችሁን መሱዓት ካደረጋችሁ፣ ብዙ ሰው ከሚጓዝበት መንገድ በተለየ መንገድ ከተጓዛችሁ፣ በየቀኑ ባለድል፣ በየሰዓቱ አሸናፉ፣ በየጊዜው የምትሻሻሉ ከሆነ ከማንም በፊት ፈጣሪ አብሯችሁ ይሆናል፣ ዓለም እጃችሁን ስማ ትቀበላችኋለች፣ የሰው ልጅ መንገድ ይሰጣችኋል። ሰነፍ ሰውን ማስገደድ አይችልም፣ ብርቱና ጠንካራ ሰው ግን በስራውና በውጤቱ ሰውን ይገዛል፣ ዓለምን ይቆጣጠራል።
አዎ! ማንም ከሰው በተለየ እንዲያዳላላችሁ አትጠብቁ፣ ማንም ከሰው ለይቶ ከጎናችሁ እንዲቆም አትፈልጉ። እናንተ ከማንም የተለየ ነገር እስካላደረጋችሁ ድረስ፣ ብዙ ሰው በሚጓዝበት መንገድ እስከተጓዛችሁ ድረስ ማንም ሰው የተለየ ነገር ሊያደርግላችሁ አይመጣም። ማንነታቸውን ያሳዩ፣ አቅማቸውን በግልፅ ያስመለከቱ፣ በችሎታቸው የተመሰከረላቸው፣ ውጤታቸው የሚናገርላቸው ሰዎች ብቻ የሚከበሩበት ዓለም ላይ እንደሆናችሁ አስታውሱ። ስንፍናን እንደ ጥበብ፣ ግዴለሽነትን እንደ ጀብድ፣ ወሬና አሉባልታን እንደ ተልቅ ስራ የሚቆጥሩ ሰዎች አወቁትም አላወቁትም ዓለም ቀስ በቀስ ለይታ የምትመታቸው ሰዎች ናቸው። ደፋር አያወራም ያደርጋል፣ ብርቱ ሰው ዙሪያ ጥምጥም አይሄድም ፊትለፊት ይጋፈጣል፣ በፈጣሪው የሚያምን፣ በራሱ የሚተማመን ሰው በፍፁም ተስፋ አይቆርጥም፣ ምንን እስከመቼ መጠበቅ እንዳለበት የሚያውቅ ሰው ሊሸነፍ አይችልም። በጥንካሬያችሁ ዓለምን ተጋፈጡ፣ በፅናታችሁ ዓለምን አሸንፉ፣ በታታሪነታችሁ ከሰው ተሽላችሁ ተገኙ።
አዎ! ጀግናዬ..! አምሮትህ ብዙ ነው የእውነት የሚያስፈልግህ ግን እጅግ በጣም ጥቂት ነው፤ የምትጓጓለት ህይወት ትልቅ ነው የምር የልብህን የሚያደርሰው ግን ትንሽ ነገር ነው። ሰው የሚያሳይህ ነገር በሙሉ ላንተ ትርጉም የሚሰጥህ አይደለም፣ ስታየው ያማረ ሁሉ ሲነካ ውድ እንቁ አይደለም። ጦርነትህን ካልመረጥክ ሁሌም ተሸናፊ ትሆናለህ፣ አቅምህን ካልተረዳህ ዘላለም ባሪያ ሆነህ ትኖራለህ። የእውነት አዋቂዎች እውቀትን በማሳደድ የተጠመዱ ሳይሆኑ የያዙትን እውቀት በተሻለ መንገድ የሚኖሩት ናቸው፣ ትክክለኛውን ተፅዕኖ መፍጠር የሚችሉት ስለህልምና ፍላጎታቸው ደጋግመው የሚያወሩ ሳይሆኑ ሁሌም እርሱን በመኖር ውስጥ ያሉ ሰዎች ናቸው። ከሰው ሳይሆን ከራስህ የምትጠብቀውን ነገር ከፍ አድርገው፣ በየቀኑ ወደፊት የሚገፋህን ፅኑ ፍላጎት ወደ ውስጥህ አስገባ፣ በማያስተኛ ምኞት ተሞላ፣ ስንፍናን በማይታገስ አጣብቂኝ ውስጥ እራስህን አስገባ። ውሎህን የጠንካራ ሰራተኛ አድርገው፣ ህይወትህን የአሸናፊ ህይወት አድርገው። ተቀምጠው እጅ ከሚሰጡት ሳይሆን ተነስተው ከሚታገሉት ጎራ ተቀላቀል።
ውብ ደማቅ ቀን ይሁንልን!
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!
#SHARE እንዳይረሳ ቤተሰቦች!
በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪