ውብ ነሽ!
ከሰዎች ጠብቀሽ ላታገኚው ትችያለሽ፣ በወዳጆችሽ መባል ፈልገሽ አልተባልሽም ይሆናል፣ የተለየ ቦታ በሰጠሻቸው ሰዎች እንዲሁ የተለየ ስፍራ አልተሰጠሽም ይሆናል። ነገር ግን አንድ ነገር አስታውሺ የትም ሳትሔጂ፣ ማንንም ሳትመስዪ፣ ከማንም ሳትወዳጂ፣ ማንም ሳይኖርሽ፣ ምንም ሳትጨምሪ እንዲሁ ውብ ነሽ። ውበትሽም የግድ በሰዎች ሊነገርና ሊደነቅ አይገባም። ዛሬ ውብ እንደሆንሽ የነገረሽ ሰው ነገም ውብ ስለመሆንሽ እንደሚመሰክር እርግጠኛ መሆን አትችይም። አዳማቂ የማይፈልገው ውበትሽ ከትምህርት ደረጃሽ የመጣ አይደለም፣ ከስራሽ የመጣ አይደለም፣ ከቤተሰቦችሽ የመጣ አይደለም፣ ከጓደኞችሽ የመጣ አይደለም። የውበትሽ ምንጭ የአምላክሽ ልጅ መሆንሽ ነው፤ የውበትሽ መነሻ ሴትነትሽ፣ አንቺነትሽና ጥልቁ ማንነትሽ ነው።
አዎ! ጀግኒት..! ውብ ነሽ! እስካከበርሽው ድረስ ሴት በመሆንሽ ብቻ ቆንጆ ነሽ፤ አሁን ያለሽበት ስፍራ በመገኘትሽ ብቻ ብርቱ ነሽ፣ እንዳቅምሽ ስለተንቀሳቀስሽ ብቻ ጠንካራ ሴት ነሽ። አለም የሚያደንቅልሽን ሳይሆን በአምላክሽ መንፈስ የተቃኘውን ውስጣዊ ውበትን የሚያዩ፣ የስብዕናሽን ጥልቀት የሚመረምሩ፣ እንዲሁ አይተው የሚማረኩብሽ ሰዎች እስኪከቡሽ ድረስ ውበትሽን ለእራስ ተናገሪ፣ ጥንካሬሽን ደጋግመሽ ለእራስሽ መስክሪ። የሚረዱሽን መምረጥ፣ የማይረዱሽንም የመተው ምርጫ አለሽ። ማንም እንዲያምንብሽ ዝቅ ብሎ የመለመን ግዴታ የለብሽም። አንደኛው ውበትሽ ክብርሽ እንደሆነ አስታውሺ። ለእራስሽ ብርታትና ሃይል መሆን ትችያለሽ፤ ለእራስሽ የሰጠሽውን ቦታ በመቀየር ብቻ አካባቢሽንና የተሰጠሽን ቦታ መቀየር ትችያለሽ።
አዎ! ጀግናዬ..! ወንድነት በእራሱ ለፈተና የሚያዘጋጅህ ቢሆንም በጥንካሬህ ግን አትጠራጠር። በህይወት እስካለህ ቀላል ነገር አገኛለሁ ብለህ እንዳታስብ። ከምድር በላይ አንተ ዋጋህን ጨምረህ፣ ይበልጥ ጠንክረህና ተሻሽለህ እስካተገኘህ ድረስ ሁሉም ነገር ከባድ ነው። እራስህን ለመስራት አትስነፍ፣ አቅምህን ከማጎልበት ወደኋላ አትበል፣ ምንም ድጋፍ ባታገኝ ድጋፍህ ወንድነትህና ፈጣሪ እንደሆነ አስታውስ። ወንድነት በእራሱ የሃላፊነት መለኪያ ነው። አሁንም ሃላፊነት አለብህ፣ ወደፊትም እንዲሁ ሃላፊነትህ ይጨምራል። ምንም ባይኖርህ፣ ማንም ባይጠጋህ እግዚአብሔር አምላክህን ብቻ ስለያዝክና ወንድ ስለሆንክ ጠንካራ ነህ፣ ብርቱ ነህ። ለእራስህ አይደለም ለምትወዳቸውና ለሚወዱህ ሁሉ ዋጋ ከፍለህ ህይወታቸውን የመቀየር አቅሙ አለህ። እራስህን ጠበቅ፣ እራስህን ተንከባከብ፣ የወንድነትህን ልክ ለእራስህም አሳየው።