አዲሱን መንገድ ውደደው!
ከዚህ በፊት ያልተጓዝክበትን፣ ያልሄድክበትን፣ ያልመረጥከውን መንገድ ውደደው፤ ከአዲሱ ተሞክሮህ ጋር ትስስር ፍጠር። ያላደረካቸውን ነገር ግን ያመንክባቸውን የተለዩ ድርጊቶች ከልብህ ውደዳቸው፣ ፈልጋቸው፣ ተዳፈራቸው፣ ተላመዳቸው። አዲስ መንገድ የአዲስ ግኚት ቁልፍ ነው፤ የአዲስ ግኚት መጨረሻም የተሻለና ከፍ ያለ ውጤት ማስገኛ ነው። ከዚህ በፊት ያልተደረጉ፣ በህይወታችን ፈፅመናቸው የማናውቃቸው፣ ኬት አንስተው የት ሊያደርሱን እንደሚችሉ የማናውቃቸው አዳዲስ ተግባሮች የምርጫችን ውጤት፣ የፍላጎታችን መነሻ ከሆኑ የተሻለ ነገር የማስገኘት እድላቸው ከፍተኛ ነው። ፍቅር ውስጥ ጥርጣሬ የለም፤ መውደድና ፍረሃት አብረው አይሄዱም፤ ህልምና ስጋት አይጣጣሙም። አዲስ ነገር እስኪጀመር ሊያስፈራ ይችላል፣ ካልተጀመረ ግን ሁሉም ነገር በነበረበት መቀጠሉ አይቀርም። ፍረሃትህን የሚደመስስ፣ ስጋትህን የሚያስወግድ መውደድ ያስፈልግሃል።
አዎ! ጀግናዬ..! አዲሱን መንገድ ውደደው! ፍረሃትህን በፍቅሩ አሸንፈው፣ ስጋትህን በመውደድህ ርታው፤ በሩን በድፍረት ክፈተው። በነገሮች ላይ ያለህ አረዳድ ሲቀየር፣ እይታዎችህ ሲለወጡ፣ በአዳዲስ እርምጃዎችህ ማመን ስትጀምር፣ ውስጥህ በድፍረት ሲሞላ፣ የወደድከው ላይ ስታተኩር የተዘጉ መንገዶች ይከፈቱልሃል፤ የተለየው እይታህ ለተለየ ውጤት፣ የተለየው ተግባርም ለተሻለ ድል ያበቃሃል። ሁሌም አዲስ ተግባር ውስጥ አዲስ ልምድ፣ አዲስ ውጤት፣ አዲስ ተሞክሮ ይገኛል። ከባቢህን የምትቀይረው የተሻለ ነገር ፍለጋ ነው፤ አዲስ ሰዎች የምትተዋወቀው፣ አዲስ ወዳጅነት የምትመሰርተው፣ አዲሱን መንገድ የመረጥከው ማንነትህን ለማሻሻል፣ እራስህን ለማብቃትና ለመቀየር ነው። የዘመናት ጥረትህ ተጨባጭ ውጤት ካላመጣልህ በተለየ አቅጣጫ መንቀሳቀሱ ያንተ ድርሻ ነው።
አዎ! የወደድከው ነገር አሸናፊ ያደርግልሃል፤ ምርጫህ ለውጤታማነት ያበቃሃል፤ እምነትህ ወደፊት ያራምድሃል። ስንቶች ለማይወዱት ስራ ስንት መሱዓትነት እየከፈሉ ባሉበት ሰዓት አንተ ለወደድከው፣ ለመረጥከው፣ ላመንክበት አዲስ መንገድ መሱዓትነት መክፈል አያቅትህም። ፍቅርህ ብቻ ብርታት ይሆንሃል፤ ፍረላጎትህ ብቻ እምቅ አቅምህን ያወጣዋል፤ መውደድህ ብቻ ህይወትና ተግባርህን ያስተሳስራል። ለእራስህ ብርታት መሆን ከፈለክ፣ ድሎችህን ማክበር፣ በጥንካሬዎችህ መደነቅ፣ ለተሻለ ነገር መብቃት ከፈለክ በአዲስ ወኔ፣ በአዲስ ፍቅር፣ በተለየ መንገድ ማሸነፍ ጀምር። ትናንት በነበርክበት መንገድ ምንም አይነት ስሜት ሰጪ አዲስ ግኚት ካልተገኘ በድፍረት የወደድከውን መምረጥ ያንተ ሃላፊነት ነው። ከልበህ የወደድከውን፣ ከመንፈስህ ጋር የተዋሃደውን፣ ስሜት የሚሰጥህን፣ ትልቅ ትርጉም እንዳለው የተማመንከውን ተግባር ከጀመርክ የምታቆምበት ምክንያት አይኖርህም። መውደድህን ሃይልህ፣ ፍቅርህን ብርታትህ አድርገው፤ ለወደድከው እስከ ጥግ መጋፈጥንም ከማንነትህ ጋር አዋህደው።