ቀላሉን እርሱት!
፨፨፨//////፨፨፨
ስለ ቀላሉ ገንዘብ መስሪያ መንገድ ብዙ ሲባል ሰምታችኋል፣ ስለ ቀላሉ ስራ ብዙ ተብላችኋል፣ ስለ አቋራጩ ሃብት ማከማቻ መንገድ፣ ስለ ተለመደው የቁማር ጫወታ ከብዙም ብዙ ሰምታችኋል፣ ከመስማትም በላይ ደጋግማችሁ ሞክራችሁታል። ነገር ግን ምን አገኛችሁ? እድሜን ከማባከን፣ ስሜትን ከመረበሽና እንቅልፍን ከማጣት በቀር ምን አተረፋችሁ? ምንም። ሁሌም የሰነፎች መገለጫ አቋራጭ መንገድ ነው፤ ሌቦች አምታተው ማትረፍ የሚፈልጉ ናቸው። ለማንም ያልሰራውን መስጠት እንደማትፈልጉ ሁሉ ባልሰራችሁትም ለመሸለም አትሯሯጡ። ቀላሉን መምረጥ ቀላል እንደሚያደርጋችሁ አስታውሱ፣ አቋራጩን መምረጥ ብኩን እንደሚያደርጋችሁ ተረዱ። ለሰነፎች ቦታ የማትሰጥ፣ በቀላሉ የማታበለፅግ፣ በአጭሩም ትርፋማ የማታደርግ ዓለም ላይ እንደምትኖሩ እወቁ።
አዎ! ቀላሉን እርሱት፣ አቋራጩን አቁሙ፣ ማምታታቱ ይቅርባችሁ፣ እራሳችሁም አትወናበዱ። ሰው ያደረገውን ማድረግ ትችላላችሁና ለከባዱ ፈተና እራሳችሁን አዘጋጁ፣ ውስብስቡን ለማለፍ፣ ከባዱን ለመጋፈጥ፣ ፍረሃታችሁን ለማሸነፍ፣ የወደፊት ህይወታችሁን ለማስተካከል፣ ልባችሁን ለማሳረፍ፣ እራሳችሁን ከድህነት ወለል ነፃ ለማውጣት መንፈሳችሁን አጠንክሩ፣ ስሜታችሁን አድሱ፣ ወኔያችሁን አነሳሱ። ከማንም ሳታንሱ ከማንም ያነሰ ህይወት ለመኖር አትንደርደሩ። ማንም ብትሆኑ ያለማቋረጥ የምትሰሩት ስራ የማይከፍላችሁ መንገድ አይኖርም። ተፈጥሮ የምትመራው በአንድ ህግ ብቻ ነው። "ከባዱ ምርጫ ከባድ ባለድል ያደርጋል፣ ቀላሉምርጫ ልፍስፍስ ደካማ ያደርጋል።" ከህጉ ዝንፍ ማለት ለህይወት ዘመን ከባድ ፀፀት ይዳርጋል።
አዎ! ጀግናዬ..! ቀላሉን ማሳደድ አቁመ እራስህን ፈትነው፣ እያወክ ዋጋ አስከፍለው፣ አቀርቅሮ አሰንዲሰራ አድርገው፣ ሳያቋርጥ እንዲተጋ አድርገው። ሰው የሚጠቁምህን ቀላል ስራ ሁሉ አትመን፣ የተባልከውን ሁሉ በመጀመር ጊዜ አታጥፋ። ዋጋህ የሚጨምረው ልክ እንደብረቱ በእሳት ስትፈተን እንደሆነ አስታውስ። አጭሯን እድሜ በልፍስፍሶች መንገድ እየተጓዝክ ይበልጥ አታሳጥራት፣ ውዷን ህይወትህን ትርጉም በማይሰጡ ጥቃቅን ተግባራት እርባና ቢስ አታድርጋት። ጨከን በል፣ ፈተና ያለውን ምርጫ በልበሙሉነት ምረጥ፣ ላሰኘህ ሳይሆን ለሚጠቅምህ፣ ለቀለለህ ሳይሆን ከብዶ ለሚያከብድህ እራስህን አሳልፈህ ስጥ። ጠንክረህ ተፋለም፣ እስከመጨረሻው ታገል፣ መቼም ተስፋህን አትጣ፣ ለከባዱ የህይወት ምርጫም የሚመጥን ማንነትን ገንባ።