ከግብር ከፋዮች ጋር ሰፋ ያለ ውይይት በማድረግ መግባባት ላይ ተደረሷል። አቶ አህመድ ሽዴ
መስከረም 22/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚዲያ )
የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራው የተሻለ አፈጻጸም ማስመዝገቡን የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ገልጸዋል፡፡
የትግበራው አፈጻጸም በዛሬው ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ተገምግሟል፡፡
ማሻሻያው ኢኮኖሚው በተረጋጋ ሁኔታ እንዲቀጥል ከማድረጉም ባሻገር በዜጎች ላይ የሚፈጠርን ማኀበራዊ ጫና በቀነስ አግባብ መተግበሩን የገንዘብ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡
የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ዋነኛ ትኩረት የመንግሥትን ገቢ ማሻሻል መሆኑን በመጥቀስም የሚኒስትሮች ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ወደ ሥራ መግባቱን አመላክተዋል፡፡
በዚህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጻር የተሻለ ገቢ መገኘቱን አብራርተዋል፡፡
በቀጣይም የመንግሥትን ገቢን የማሳደጉ ሥራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አቅጣጫ መቀመጡን አቶ አህመድ ሽዴ አስታውቀዋል፡፡
የገቢ ማሻሻያውን በሚመለከትም ከግብር ከፋዮች ጋር ሰፋ ያለ ውይይት በማድረግ መግባባት ላይ መደረሱን ገልጸዋል::
በትሬዥሪ ቢል አመካኝነትም ለረዥም ጊዜ ያልተከፈሉ ብድሮች ወደ ረዥም ጊዜ ቦንድ እንዲቀየሩ መደረጉን ተናግረዋል፡፡
የውጭ ሀገር የብድር ሽግሽግን በሚመለከትም በቡድን 20 የተቋቋመው የአበዳሪ ኮሚቴ ለኢትዮጵያ የብድር ማሸጋሸግ ዋስትና መስጠቱን ጠቅሰው፤ በቀጣይ ጥቂት ወራት ኢትዮጵያ የውጭ እዳ እፎይታ እንደምታገኝ ጠቁመዋል፡፡