ስተን
ስተን ጥሩውን ከመጥፎ መለየት አቅቶን
ጥሩ እንዳይርቀን ፊቱን እንዳይነሳን
ሰግተን
ዳር ድንበሩን አይተን ጦርነት ፈርተን
ንጉሱ ባጠፋው እኛ ህይወት ሰተን
ጥረን
ጥረን ለህይወታችን ብለን መኖርን ፈልገን
አንገት አቀርቅረን ጉልበታችን ሰብረን በእንብርክክ ሄደን
ለምነን
ለምነን ከፊታቸው ወድቀን
እጃችን ዘርግተን ምረትን ጠይቀን
አሸርግደን
ሞቱ ለማይቀረው ለህይወታችን ሰግተን
ፈጣሪ እያለ ለንጉሱ ሰግደን
ተቸግረን
ተቸግረን የምንበላው አተን
ፈጣሪን ሳንጠይቅ እነሱን ለምነን
ጠይቀን
ትልቁ እያለ ትንሹን ተማፅነን
ሀያሉ እያለ ለአቅመ ቢስ ወድቀን
ደንዝዘን
ፈጣሪን በመያዝ መጠንከር ሲገባን
በህይወት እያለን በቁማችን ሞተን
ገሀነም ሳንገባ እዚው ተቃጠልን
ጥፋታችን
ዋ ጥፋታችን እንደው መከራችን
በህይወት እያለን በቁም መሞታችን
✍ ABD
ስተን ጥሩውን ከመጥፎ መለየት አቅቶን
ጥሩ እንዳይርቀን ፊቱን እንዳይነሳን
ሰግተን
ዳር ድንበሩን አይተን ጦርነት ፈርተን
ንጉሱ ባጠፋው እኛ ህይወት ሰተን
ጥረን
ጥረን ለህይወታችን ብለን መኖርን ፈልገን
አንገት አቀርቅረን ጉልበታችን ሰብረን በእንብርክክ ሄደን
ለምነን
ለምነን ከፊታቸው ወድቀን
እጃችን ዘርግተን ምረትን ጠይቀን
አሸርግደን
ሞቱ ለማይቀረው ለህይወታችን ሰግተን
ፈጣሪ እያለ ለንጉሱ ሰግደን
ተቸግረን
ተቸግረን የምንበላው አተን
ፈጣሪን ሳንጠይቅ እነሱን ለምነን
ጠይቀን
ትልቁ እያለ ትንሹን ተማፅነን
ሀያሉ እያለ ለአቅመ ቢስ ወድቀን
ደንዝዘን
ፈጣሪን በመያዝ መጠንከር ሲገባን
በህይወት እያለን በቁማችን ሞተን
ገሀነም ሳንገባ እዚው ተቃጠልን
ጥፋታችን
ዋ ጥፋታችን እንደው መከራችን
በህይወት እያለን በቁም መሞታችን
✍ ABD