(ዜና) ዋዜማ ራዲዮ በጠዋቱ ባሰራጨው መረጃ "'በኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን በጅማ ከተማ ቤታቸው ለኮሪደር ልማት የፈረሠባቸው ነዋሪዎች መንግሥት በተከራየላቸው የሆቴል አልጋዎች፣ በግለሰብ መኖሪያዎችና በቀበሌ ቤቶች ውስጥ እየተንገላቱ መኾኑን ነገሩኝ" ሲል ዘግቧል።
"በከተማዋ አውራ ጎዳናዎች ግራና ቀኝ ያሉ የንግድና የመኖሪያ ቤቶች ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ለኮሪደር ልማቱ መፍረሳቸውን ከምንጮቼ ሰምቻለው ያለው የራድዮው ዘገባ "ከፈረሱት ቤቶች መካከል፣ አብዛኞቹ ሕጋዊ ካርታ ያላቸውና ግብር ከፋይ እንደነበሩም" ጠቅሰዋል ብሏል።
"ለፈረሱት ቤቶች ባለቤቶች መንግሥት የገንዘብ ካሳም ይኹን ተለዋጭ ቦታ አልሠጣቸውም ብለዋል።" ሲል የዘገበው ዋዜማ "በኮሪደር ልማቱ የፈረሱት ቤቶች 15 ሺሕ ገደማ እንደኾኑ ተረድቻለሁ"ም ሲል ዘገባ አሰራጭቷል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከሰሞኑ በጅማ ከተማ የኮሪደር ልማት ሥራዎችን ሲመርቁ ባደረጉት ንግግር "የጅማ ከተማ ነዋሪዎች ቤቶቻቸውን ሲያፈርሱም ሆነ ቦታዎችን ለፕሮጀክቶቹ ሲያስረክቡ ካሳ አለመጠየቃቸውን” በአድናቆት መግለጻቸው ይታወሳል። "የጅማ ከተማ ህዝብ፤ ካሳ ከመጠየቅ ይልቅ እስቲ ሃሳባችሁን አፍሱት፤ ልየው ነው ያለው። የጅማ አካባቢ ማህበረሰብ ለእነዚህ ህልሞች፣ ለእነዚህ ሃሳቦች መወለድ የነበረው ሚና፤ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ትምህርት መሆን ያለበት ነው” ማለታቸው አይዘነጋም።