#BREAKING🚨
የበሽር አላሳድ አገዛዝ ተገረሰሰ።
የሶሪያው ፕሬዜዳንት በሽር አላሳድ አገዛዝ ወደቀ። እሳቸውም ሀገር ለቀው ጠፍተዋል።
የታጠቁ የሶሪያ ተዋጊዎች የፕሬዚዳንት በሽር አል አሳድን የ24 ዓመት አገዛዝ ለመደምሰስ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ የተጠናከረ ወታደራዊ ዘመቻ እያካሄዱ ነበር።
በተለይም በሰሜናዊ ክፍል የሚገኙ የታጣቁ ተቃዋሚዎች ከረዥም ዓመታት በኋላ የአገሪቱ ጦር ላይ ድንገታዊ ጥቃት ከከፈቱ በኃላ ብዙ ቦታዎችን በፍጥነት ይዘዋል።
ከሳምንት በፊት ነው አሌፖን ዘልቀው የገቡት።
ከዛ በኃላ በመላ ሀገሪቱ ውስጥ ያሉ የመንግስት መከላከያዎች በአስደናቂ ፍጥነት ፈራርሰዋል።
በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች የአማጽያኑን ምት መቋቋም ከብዷቸው ድንበር አቋርጠው ኢራቅ ለመግባትና ጥገኝነት ለመጠየቅ ተገደዋል።
ተቃዋሚዎቹ በቀናት ውስጥ እጅግ በርካታ ቁልፍ ከተሞችን እና ቦታዎችን ከአላሳድ አገዛዝ ነጻ ያደረጉ ሲሆን ለሊቱን የአሳድ መቀመጫ ወደ ሆናችው ደማስቆ መግባታቸው ታውቋል።
አላሳድ ከደማስኮ ወጥተው ሄደዋል ተብሏል።
የፕሬዜዳንቱን ከደማስቆ መልቀቅ ሁለት ከፍተኛ የጦር አመራሮች ለሮይተርስ አረጋግጠዋል።
አሁን ላይ አሳድ የት እንደገቡ የሚታወቅ ነገር የለም።
የታጠቁት ተቃዋሚዎች ባወጡት መግለጫ ፤ " ጨቋኙ በሽር አላሳድ ከደማስቆ ለቀው ሄደዋል " ብለዋል።
" ደማስቆን ከጨቋኙ በሽር አላሳድ ነጻ አውጥተናል " ሲሉም ገልጸዋል።
በሽር አላሳድ ሀገሪቱን ለቀው መጥፋታቸውንም አሳውቀዋል።
ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያውንም ተቆጣጥረውታል።
አንዳንድ ቪድዮዎች እንዲሁም ሮይተርስ የአይን እማኞችን ዋቢ በማድረግ እንደዘገበው በደማስቆ ጎዳናዎች ሶርያውያን ወጥተው ' ነጻነት ! ነጻነት ! ' እያሉ መፈክር ሲያሰሙ ደስታቸውን ሲገልጹ ታይተዋል።
እነ ሩስያ ፣ ኢራን ፣ አሜሪካ እና ቱርክ ?
የአገዛዙ ዋነኛ አጋር የሆኑት ሩሲያ እንዲሁም ኢራን ለአሳድ ቀጣይነት ያለውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ሲያሳውቁ ቢሰነብቱም አገዛዙን ከመፍረስ አልታደጉም።
ሩስያ በዩክሬን በሚያደርገው ጦርነት የተጠመደች ሲሆን፣ ኢራን ደግሞ እስራኤል በሊባኖስ ሔዝቦላህ ላይ በከፈተችው ዘመቻ ምክንያት ተዳክማለች።
ጦርነቱ ሲባባስ ሞስኮ የሩሲያ ዜጎች አገሪቱን ለቅቀው እንዲወጡ ጥሪ ስታቀርብ ነበር።
በሶሪያ የረጅም አመታት የእርስ በርስ ጦርነት ዋና ተዋናይቷ አሜሪካም ብትሆን ሁኔታውን አይታ ዜጎቿን " በደማስቆ በረራዎች እስካሉ ድረስ " ሶሪያን ለቅቀው እንዲወጡ ስትጮህ ነበር።
ቱርክ በሶሪያ ያሉ አንዳንድ የታጠቁ ተቃዋሚ ቡድኖችን ትደግፋለች።
የቱርክ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ለወራት አሳድን ከተቃዋሚዎች ጋር ፖለቲካዊ መፍትሄ ላይ አንዲደርሱ ግፊት ሲያደርጉ ነበር።
ፕሬዜዳንቱ የተቃዋሚዎችን የቅርብ ጊዜ ግስጋሴ እንደሚደግፉ ተናግረው " አሳድ ጥሪዬን ቢቀበል ኖሮ ይህ አይከሰትም ነበር " ብለዋል።
#ሶሪያ : እ.ኤ.አ. ከ2011 ጀምሮ በተቃውሞ ስትናጥ ከቆየች በኃላ በከፋ የእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ የምትገኝ ሲሆን በዚህም እጅግ በርካታ ሰዎች አልቀዋል። ሀገሪቱ እንዳልነበረ ሆናለች። ለሀገሪቱ እንዲህ መሆን የውጭ ኃይሎች አገዛዙን እና አማጽያንን በመደገፍ ረገድ ትልቅ ድርሻ አላቸው።
መረጃው ከአልጀዚራ፣ ሮይተርስ እንዲሁም ቢቢሲ የተሰባሰበ ነው።
@my_oromia