የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት እና የሀብት አስተዳደር ሥርዓቱን ለማዘመን ከደቡብ አፍሪካ ኩባንያ ጋር ስምምነት ፈጸመ
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን እና መቀመጫውን ደቡብ አፍሪካ ኬፕታውን ካደረገው ሎህባወር አሶሴት ጋር በዘመናዊ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት አስተዳደር እንዲሁም በሀብት አስተዳደር ዙሪያ ዓለምዓቀፋዊ ልምዶችን ተግባራዊ ለማድረግ ስምምነት ደርሰዋል፡፡
ስምምነቱን የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ረሻድ ከማል እና የአማካሪ ድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሚስተር ሬን ሆርድ ፈርመዋል፡፡
በከፍተኛ ሁኔታ እያደገና እየሰፋ ያለውን የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የቤት ግንባታ መርሀ ግብር ዓለምዓቀፋዊ የፕሮጀክትና የሀብት አስተዳደር ልምዶችን በመቀመር ረገድ ስምምነቱ አገራዊ ፋይዳ ይኖረዋልም ተብሏል፡፡
በተጨማሪም በቴክኖሎጂ ፣ እውቀት ሽግግር እና በኮንስትራክሽን እንዲሁም በቤት አስተዳደር ሥራዎች ዘመናዊ የአሰራር ስርዓቶች ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት ነው፡፡
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ረሻድ ከማል በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር ኮርፖሬሽኑ በፕሮጀክት አስተዳደር ረገድ በሞዴልት የሚጠቀስ ስርዓት መዘርጋት የቻለ ተቋም እንደሆነ አስታውሰው በአሁኑ ሰዓት የኮርፖሬሽኑ የግንባታ ፕሮጀክቶች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ በመሆኑ የተቋሙን የፕሮጀክትና የሀበት አስተዳደር አቅምን በማሳደግና የአሰራር ሥርዓት በማሻሻል የኮርፖሬሽኑን ትርፋማነትና ተወዳዳሪነት ለማረጋገጥ የሚያስችል ሥራ ከወዲሁ መሥራት አስፈላጊ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ከሎህባወር አሶሴት ኩባንያ ጋር በመሆን ዓለምዓቀፋዊ ልምዶችን ተግባራዊ ለማድረግ ኮርፖሬሽኑ እንደሚሰራ ክቡር አቶ ረሻድ ተናግረዋል፡፡
የሎህባወር አሶሴት ዋና ሥራ አስፈጻሚ በበኩላቸው ባስተላለፉት መልዕክት በከፍተኛ ለውጥ ላይ ካለው ከፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ጋር በጋራ ለመስራት እድል በማግኘታቸው ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው ገልጸው በዘርፉ ለ28 ዓመታት ያዳበሩትን የማማከር አገልግሎት ልምድ ለኮርፖሬሽኑ ለማከፈል እንደሚሰሩም ተናግረዋል፡፡
በስምምነቱ ወቅትም የዓለምቀፉ የሙያ ደህንነትና የጤና ፕሬዜደንት የኢንተርናሽል የሲቪል መሀንዲስ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር ካርል ሀይንስ ተገኝተዋል፡፡