ኢትዮጵያ ባለፋት አራት ወራት ከቡና የውጪ ንግድ ከ674 ሚሊዮን በላይ የአሜሪካን ዶላር ገቢ አገኘች
ኢትዮጵያ በበጀት ዓመቱ አራት ወራት ውስጥ 98 ሺህ 999.38 ቶን ቡና ለውጪ ገበያ በመላክ ከ674 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘቷን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታውቋል።
የባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነትና የኮሚኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ አቶ ሳህለ ማርያም ገብረ መድህን ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ኢትዮጵያ በዚህ ጊዜ ውስጥ ለሽያጭ ካቀረበችው የቡና ምርት 5 መቶ 31ነጥብ 4 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ለማግኘት አቅዳ ነበር።አያይዘውም ከእቅድ በላይ 150 ሺህ 3 መቶ 46ነጥብ 57 ቶን ቡናን ለገበያ ማቅረብ ችላለች ያሉት አቶ ሳህለ ማርያም በምላሹ 674 ነጥብ 55 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ አግኝታለች።
በዚህም ከታቀደዉ አንፃር 127 በመቶኛ ብልጫ ያለው ገቢ ተገኝቷል ሲሉ ተናግረዋል። አፈጻጸሙ ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በመጠን 62 ሺህ 5መቶ 87 ነጥብ 58 ቶን እና በገቢ ደግሞ 2መቶ 26 ነጥብ 89 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወይም 51 በመቶ ጭማሪ ተመዝግቧል።በ2017 በጀት ዓመት አራት ወራት የተላከዉ ቡና ከመዳረሻ ሀገራት አኳያ ሲታይ ጀርመን ቀዳሚዋ የኢትዮጵያ ቡና ገዢ ሀገር መሆኗ ተመላክቷል።
ወደዚህችዉ ሀገር 32 ሺህ 6 መቶ 66.48 ቶን ቡናን መላክ እንደተቻለ የተገለፀ ሲሆን 132ነጥብ 40 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ተገኝቷል። በሌላ በኩል ወደ ሳዑድ አረቢያ 26ሺህ 579ነጥብ49 ቶን ቡና ለሽያጭ ቀርቦ 113 ነጥብ 83 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ተገኝቷል።እንዲሁም ባለፋት አራት ወራት 15 ሺህ 325 ነጥብ 9 ቶን ቡናን ለቤልጅየም በመላክ 71ነጥብ 59 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ማግኘት እንደተቻለ ሲገለፅ ይህን አፈፃፀም በማስመዝገብ እነዚህ ሀገራት ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃን ይዘዋል፡፡
በገቢ ቅደም ተከተል የተቀሩት የገበያ መዳረሻ ሀገራት 4ኛ አሜሪካ፣ 5ኛ ደቡብ ኮሪያ ፣ 6ኛ ጃፓን፣ 7ኛ የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ፣ 8ኛ ዮርዳኖስ፣ 9ኛ ጣልያን እና 10ኛ አዉስትራሊያ በመሆን የኢትዮጵያ ዋንኛ የቡና ምርት መዳረሼ ናቸው። ከ1ኛ እስከ 10ኛ ደረጃን የያዙት ሀገራት በአጠቃላይ በመጠን 77 በመቶ እና በገቢ ደረጃ ደግሞ 78 በመቶ የዉጪ ምንዛሪ ግኝት ይሸፍናሉ፡፡ በጥቅሉ የእነዚህ ዋና 10 መዳረሻ ሀገራት ከ2016 አፈፃፀም ጋር ሲወዳደር በመጠን 84 በመቶ እና በገቢ ሲታይ የ60 በመቶ ጭማሪ አለው ሲል ባለስልጣኑ አስታውቋል፡፡