#Earthquake
ዛሬ በሬክተር ስኬል 5.1 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ እንደነበር የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ገልጿል።
የመሬት መንቀጥቀጡ ከአዋሽ በሰሜን 36 ኪ/ሜ በኩል ነው የተመዝገበው።
የመሬት መንቀጥቀጡ ንዝረት አዲስ አበባ እና ቦታዎችም የተሰማ ሲሆን በተለይ በአዲስ አበባ ንዝረቱ በደንብ ይሰማ ነበር።
የመሬት ንዝረት እየተሰማ ነው ፤ ያለሁት ቦሌ አካባቢ መኪና ውስጥ ነው ፤ በደቂቃዎች ልዩነት ሁለቴ አጋጥሟል " ሲሉ ቃላቸውን ሰጥተዋል።
ሌላ አንድ የቤተሰባችን አባል " መኪናዬ ውስጥ ሆኜ ትንሽ ንቅንቅ ስል ተሰምቶኛል ወደ አያት አካባቢ ቆሜ ባለሁበት " ሲል ገልጿል።
ከሰሞኑን የተለያየ መጠን ያላቸው ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶች እየተመዘገቡ ሲሆን የዛሬው 5.1 ከፍ ካሉት አንዱ ነው።
በሬክተር ስኬል 5.1 ከተመዘገበው የመሬት መንቀጥቀጥ በኃላ በሬክተር ስኬል 4.5 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥም ነበር።
አፋር ላይ በተለይ የመሬት መንቀጥቀጡ አይሎ በሚሰማባቸው ቦታዎች ንብረት ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን በርካቶችም ከቤታቸው ሸሽተው ሄደዋል።
Via Tikvah