❤️ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤️
የዐቢይ ጾም ስምንተኛው ሳምንት
ሆሳዕና
ይህ የስምንተኛው ሳምንት ሰንበት መጠሪያ ሲሆን ይህም ዕለት በነቢዩ በዘካርያስ ላይ የተጻፈው ትንቢት ይፈፀም ዘንድ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያይቷ እና በውርንጭላይቷ ላይ ተቀምጦ ሆሳዕና በአርያም ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ ተብሎ እየተመሰገነ ወደ ቤተ መቅደስ መግባቱ የሚታሰብበት ዕለት ነው፡፡ ሆሳዕና ማለት መድኃኒት ወይም አቤቱ አሁን አድን ማለት ነው፡፡ ይህ የዐቢይ ጾም ፋሲካ አንድ ሳምንት ሲቀረው የሚከበረው የጌታ በዓል ከዘጠኙ ዓበይት በዓላት አንዱ ነው። በሰሙነ ሕማማት ጸሎተ ፍትሃት ጸሎተ አስተስርዮ ስለማይፈጸም ጸሎተ ፍትሃትና አስተስርዮ የሚደረገው በዚሁ ዕለት ነው::
አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ አልዓዛርን ከሞት ባስነሳባት የቢታንያ መንደር በተገኘ ጊዜ የአይሁድን ፋሲካ ለማክበር ከየሀገሩ መጥተው የነበሩ ሰዎች ጌታችንንም ከሞት ያስነሳውን አልዓዛርንም ለማየት ተሰብስበው ነበር። ተአምራቱን እያደነቁ ብዙዎችም አምነውበት ነበር፡፡ ጌታችን ከቢታንያ ወደ ኢየሩሳሌም እስኪደርስ ብዙዎች በምሥጋና አጅበውታል፡፡(ዮሐ. 12÷12) የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘው “ሆሳዕና በጌታ ስም የሚመጣ የእሥራኤል ንጉስ የተባረከ ነው።” እያሉ እያመሰገኑት ወደ ቤተፋጌ መንደር ደረሱ፡፡
=> ጌታችን ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ ዘንባባ የመነጠፉ ሚስጢር የምን ምሳሌ ነው?
1. ዘንባባ፡- ይስሃቅ በተወለደ ጊዜ ደስ ብሎት አብርሃም ዘንባባ ይዞ እግዚአብሔርን አመስግነዋል፡፡
2. ዘንባባ፡- ደርቆ እንደገና ህይወት ይዘራል:: የደረቀ የምታለመልም አምላክ ነህ ሲሉ ነው፡፡
3. ዘንባባ፡- የሰላም ምልክት ነው፡- የሰላም አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
4. ዘንባባ፡- የደስታ መግለጫ ነው ፤ አንተ ደስ የምታሰኝ ሃዘናችንም የምታርቅልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው፡፡
5. ዘንባባ፡- እሾሃማ ነው፡- አንተ ህያው አሸናፊ አምላክ ነህ ሲሉ ነው፡፡
6. ዘንባባ፡- እሳት አይበላውም ለብልቦ ይተወዋል እንጂ ፤ ጌታም አንተ ባህሪህ የማይመረመር ነው ሲሉ ነው፡፡