Forward from: "ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒
❇#ፃድቁ_አባ_ዮሐንስ_ሐፂር_።
☞•••ወር በገባ በ20 የአቡነ ዮሐንስ ሐፂር ወርሐዊ መታሰቢያቸው ነው አቡነ ዮሐንስ ሐጺር ቁመታቸው አጭር ስለ ነበር ዮሐንስ ሐጺር አጭሩ ዮሐንስ ተብለዋል፡፡ ☞በ18 ዓመታቸው እስቄጠስ ገዳም ገቡ ☞አባታችን አቡነ ዮሐንስ በታዛዥነታቸው በእጅጉ ይታወቃሉ፡፡ ይህንንም ለመፈተን አንድ ቀን አባ ባይሞይ የደረቀ እንጨት አንስተው ለአቡነ ዩሐንስ ሰጧቸውና ይህን ደረቅ እንጨት ትከለውና ውሃ እያጠጣህ አብቅለው ፍሬ እስኪያፈራም ተንከባከበው አሏቸው፡፡
☞አቡነ ዮሐንስም በፍጹም መታዘዝ እሸ ብለው ደረቁን እንጨት ተክለው ሦስት
ዓመት ሙሉ ከሩቅ ቦታ በቀን ሁለት ጊዜ ውኃ እየቀዱ በማምጣት ማጠጣት
ጀመሩ፡፡
☞በ3ኛውም ዓመት ደረቁ እንጨት ጸድቆ ለመለመ ታላቅ ዛፍም ሆኖ አብቦ
አፍርቶ ጣፋጭ ፍሬ አፈራ፡፡ አባ ባይሞይም ፍሬውን ቆርጠው ወስደው የታዛዡን
የትሑቱን ፍሬ እንሆ ቅመሱ እያሉ ሀቅዱሳን ሰጧቸው፡፡ ቅዱሳኑም እግዚአብሔርን
እያመሰገኑ ተመገቡ፡፡
]አባታችን ትልቁ የቅድስና ደረጃ ላይ ሲደርሱ ቀና ቢሉ ሥልሱ ቅዱስን
ይመለከታሉ ዝቅ ቢሉ ደግሞ እንጦሮጦስን ያያሉ፡፡ አቡነ ዮሐንስ ሐጺር በታላቅ
ተጋድሎአቸው ሥሉስ ቅዱስን በገሃድ ለማየት የበቁ ታላቅ አባት ናቸው፡፡
☞ከአባታችን ከአባ ዮሐንስ ሐጺር የህይወት ትምህርቶች መካከል
☞1'1☞የጠላቱን ከተማ ለመቆጣጠር የዘመተ ንጉሥ አስቀድሞ የውኃውን
መንገድ ይዘጋል፤ የእህሉንም መግቢያ ይይዛል፡፡ ያንጊዜ ጠላቶቹ ይራባሉ
ይጠማሉ፡፡ በመጨረሻም እጃቸውን ይሰጣሉ፡፡ የነፍስን ፆር ለማሸነፍም
በተመሳሳይ መንገድ መጠቀም ይገባል፡፡ በጾም በረኃብ ከጸና የነፍሱ ጠላቶች
ይዳከማሉ፡፡
☞1'2☞እኔ በትልቅ ዋርካ ሥር የተቀመጠንና አራዊት ሊጣሉት የመጣን ሰው
እመስላለሁ፡፡ ሊቋቋማቸው እንደማይችል ከተረዳ ሸሽቶ ወደ ዛፋ በመውጣት
ነፍሱን ያድናል፡፡ በእኔም የተፈጸመው ይኸው ነው፡፡
☞በባኣቴ ተቀምጪ ክፋ ሐሳቦች ሊቃወሙኝ ሲመጡ ልቋቋማቸው እንደማልች
ባወቅኩ ጊዜ በጸሎት ወደ፡እግዚአብሔር ሸሽቼ እመሽጋለሁ፡፡ በዚያም ከጠላቶቼ
ፍላፃ እድናለሁ፡፡
☞1'3☞መለወጥ የምትፈለግን ነፍስ በተመለከተ አባ ዮሐንስ እንዲህ አለ
በአንዲት ከተማ ውስጥ ብዙ ወዳጆች የነበሯት አንዲት አመንዝራ ሴት ነበረች፡፡
ከገዥዎቹ አንዱ ቀረባትና መልካም ሴት ለመሆን ቃል ግቢልኝና አገባሻለሁ
አላት፡፡ እርሷም ቃል ገባችለትና ተጋቡ፡፡ ወደ ቤቱም ወሰዳት፡፡
☞የቀድሞ አፍቃሪዎቿ ያቺን ሴት ፈለጓት እርስ በርሳቸውም ያ ልዑል ወደ ቤቱ
ወሰዷታል ወደ ቤቱ ብንሔድ ይቀጣናል፡፡ ነገር ግን ፧ጓሮ በኩል እንሒድ፤
ለርሷም እና ፏጭላት የፋጨቱን ድምጽ ስትሰማ ከደርቡ ወርዳ ወደኛ
ትመጣለች በዚህም ያለ ችግር እናገኛታለን ተባባሉ፡፡ ወደ ቤቷም ጓሮ ተጉዘው
ያፏጩ ጀመር፡፡
☞እርሷ ግን የፋጨቱን ድምፅ ስትሰማ ጆሮዎቿን ደፈነች፡፡ ወደ ውሳጣዊው
እልፍኝም ገባች፡፡ በሩንም ጥርቅም አድርጋ ዘጋች፡፡
☞ይቺ ሴት የኛ ነፍስ ምሳሌ ናት፡፡ ወዳጆቿ የተባለም ፈተናዎቿ ናቸው፡፡ ገዥ
የተባለውም ክርስቶስ ነው፡፡ እልፍኝ የተባለው ዘለዓለማዊ ቤት ነው፡፡ እነዚያ
የሚያፏጩት ክፋዎች አጋንንት ናቸው፡፡ ነገር ግን ነፍስ ሁለጊዜም በክርስቶስ
አምባነት ትሸሸጋለች፡፡
☞(በዲያቆን ዳንኤል ክብረት"በበረሓው ጉያ ውስጥ ከሚለው መጻሐፍ
የተወሰደ፡፡)
☞የጻድቁ አባታችን የአቡነ ዮሐንስ ሐጺር የጸሎታቸው በረከት አይለየን፡፡