መቃብሩ በፈርጣማ ወታደሮች ተጠበቀ። በትላልቅ ደጎራ ተዘጋ።
አይሁዶች በደስታ ሰከሩ። ፖለቲከኞች በፍርዳቸው እረኩ።
እናቱ እንባዋ እንደ ጅረት ፈሰሰ። ሐዋርያት የሀዘን ደመና ከበባቸው። ከበረከቱ፣ ከፈውሱ የተጠቀሙት ሕዝቦች በአምላክነቱ ተጠራጠሩ። ጥቂቶቹ በሀሰት በመገደሉ አለቀሱ።
እውነት በዝምታ ተቀበረች።
ነገር ግን ሙታንን የሚያስነሳው አምላክ መቃብሩን ፈንቅሎ ወጣ -
እሁድ ሌሊት 6:00።
የአርብ ልቅሶ በእሁድ ደስታ ተሻረ። የወላጅ እናቱ የጠነከረ ሀዘኗ እንደ ጤዛ ተነነ። ሐዋርያት በደስታ ተሰባበቡ። የተጠራጠሩት ወደ ማመን ተመለሱ። የተቀበረችው እውነት ተገለጠች።
በሀገር ውስጥም ከሀገር ውጪም እምትኖሩ የክርስትና እምነት ተከታዮች የድንግል ማርያም ወዳጆች እንኳን ለዳግማ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ