"ግፍና መከራ ተንከባሎ በሁሉም ቤት ይደርሳል። "
የምናደርገው ነገር ትርጉም መስጠት ያቆመበት በሚመስልበት ጊዜ ላይ ነን። እዚህ ሀገር ልጅ እንወልዳለን። የምናወርሰው ሀገር ግን ሲዖል ነው። ምሽቶች ባሎቻቸው ድንገት በወጡበት ይቀራሉ። ይታፈናሉ፥ ይታገታሉ። ልጆች ያልጠገቡትን፥ በውል ያለዩትን አባቶቻቸውን ባልጠበቁት ቅጽበት ይሰናበታሉ። ለሀገራቸው ውለታ የዋሉ ዋርካ ሰዎች በልጅ እግሮች ይገደላሉ። ደም ይፈሳል —በየመንገዱ፥ በየጫካው። አድባራት አንድ ባንድ ይፈርሳሉ። ማንም ምንም ማምጣት የሚችል አይመስልም። ድንገት ኢምንትነት እንዲሰማህ ትሆናለህ።
ሞት እየጠራህ ትማራለህ? ሞት እያነፈነፈህ ታከማቻለህ? በደጅህ ሞት እያደባ ታገባለህ? ሀገር እየተቃጠለ ትሰርጋለህ? ቆንጆ ቆንጆ ልጆች የጥይት እራት እንዲሆኑ ትወልዳለህ? መሣሪያ የታጠቀ ወንበዴ ቤትህን እየሠረሠረ ታንቀላፋለህ? የዓለም ምጽዓት አንተ ጋር እስከሚደርስ ትተኛለህ?
ሀገሩ የባለጌ ነው። ማን ጌታ እንደሆነ አይታወቅም። በመንገድ ስታልፍ ረግጦህ የገላመጥከው ሰው ዘመደ ብዙ ነው። የጦር መሣሪያ አለው። ባታውቀውም የጎበዝ አለቃ ነው። ትንሽ መንግሥት ነው። ሕይወትህን ከአፈር ይደባልቀዋል። ያየህ እስከማይገኝ ድረስ ድራሽህ ይጠፋል። ወዝህ ያስቀናው ሰው ዳር ሊያስይዝህ ይችላል።
ሀገርህ ከየት እስከየት እንደሆነ አታውቅም። እግርህ ከቤት ወጣ እንዳለ የጠላት ሀገር ነህ። በካርታ ባይከለልም የተበጀ ድምበር አለ። ድንገት ትጨመደዳለህ፥ እጅ ትሰጣለህ። ብትማረክም ትገደላለህ። ከቀን ውሎህ ተርፈህ፥ በሰላም ወጥተህ ከገባህ እድለኛ ነህ። ከሄድክበት ስትመለስ ቤትህን በገነባህበት ስፍራ ላታገኘው ትችላለህ። ግፍና መከራ ተንከባሎ በሁሉም ቤት ይደርሳል። እስከዚያው ያንተ ተራ እስኪደርስ ታንቀላፋለህ? ወይ የተኛህ ትመስላለህ? ዝም ካልከው በራፍህን አንኳክቶ መምጣቱ አይቀርም አልነገሩኝም እንዳትል!!
@Sewsinor @Sewsinor