ሰው መሆን...


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


ሰው ከመሆን በላይ ምን አለ ?
መልካም እንሁን ፡፡
ሟች መሆናችንን እያሰብን እንኑር
0923983389
@sam2127

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


🌹29🌹🌹04🌹🌹2017🌹

🌿እንደተነገረው ልክ እንደተጻፈው በነቢያት በኩል ፣
🌿ተፀንሰክ ተወለድክ ከሰው ልጆች እኩል።
🌿ከተሰጠን ገነት ከነበረን ክብር ትዕቢት ሲያዋርደን፣
🌿በስጋ ተገልጠህ ከዘላለም ጥፋት ምህረትህ ጋረደን።
🌿🌿አንተዬ🌿🌿
🌿እኛ ሀጢያተኞች በደል ያደከመን፣
🌿እንዴት❤️ ብትወደን❤️ ነው ከዙፋን አውርዶህ 
ትህትናህ ያከመን።?

🌹🌿❤️🌿❤️🌿❤️🌿❤️🌿❤️
እንኳን ለጌታችን እና ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ🌿❤️🌿❤️🌿❤️🌿❤️🌿❤️🌿❤️

@TIBEBnegni
@TIBEBnegni

✍ከሳሚ


Forward from: Samuel Adane
💡ከምትፈልገው ይልቅ፣ የተሰጠህ ይበልጣል!

〽️የሰው ልጅ ከመመኘትና ከመፈለግ የቦዘነበት የአፍታ ንቃተ-ህሊና ህይወት ኖሮት አያውቅም! ሰው በፍላጎቱ ዛቢያ ብቻ የሚሽከረከር
ፍጡር ነው!

🔅የምትፈልገውን ነገር ለአምላክህ በዕምነት ሰጥተኸው እንደሚሰራለህ አምነህ ዞር አትልም!ያለማቋረጥ መጠየቅን እንጂ በተቀበልከው መደሰትና ማመስገንን ረስተሃል! ወዳጄ ሆይ የተሰጠህን አስተውል !

ወዳጄ... እውነቱን ልንገርህ...

🔺የጥያቄህ ብዛት ስጦታህን ጋርዶብህ እንጂ፣ ያለህን አመስጋኝ ሳይሆን የሌለህን ናፋቂ ሆነህ እንጂ፣የፍላጎትህ ባህር የበረከትህን ውቂያኖስ አስንቆህ እንጂ፣ከምኞትህ ግልቢያ ለአፍታ ቆም ብለህ ብታስብ...
👉ከምትፈልገው ይልቅ. የተሰጠህ እንደሚበልጥ ማስተዋል ከባድ አይሆንብህም !

🔶እራስህን እንደማትወደው እንደማታከብረውና እንደማትሆነው ስታስብ ከማይመረመረው ፈጣሪ ጋር እየተደራደርክ ነውና ቆም ብለህ አስብ።

🔷ሰዎች ከሚሉህ በላይ ፈጣሪ ሲፈጥርህም ምክንያት አለውና የሌለህን ትተህ ያለህን ዋጋ ስጥ። በሌለህ ነገር ስለምታገኘው ሳይሆን ባለህ ነገር ስለምትለውጠው ተመራመር።

♦️በሌለህና ባልተጨበጠው ነገር ትልቅ ነገር ለመስጠት ከማሰብ ይልቅ
ባለህ ነገር ትንሽ ነገር ለመስጠት ሞክር። ያኔ አንተ ውስጥ የተደበቀው ከሌሎች የተለየው ድንቅ ፍልቃቂ ማበብ ይጀምራል።ብርሀንህ በዓለም ሁሉ ይሰፋል።በምድር ላይ በኖርክበት ዘመን ሁሉ ዘመንህ የጣፈጠ ይሆንልሀል።

🙏ፈጣሪ ሆይ... የማግኘት ምስጢሩ ማመስገን ነውና፣የደስታ ምስጢሩም እርካታ ነውና፣🙏

@TIBEBnegni
@TIBEBnegni


Forward from: Samuel Adane
​​እኛነታችንን በደንብ አናውቀውም፡ ግን እኛ እኔ በሚል አጥር ውስጥ ተተብትበናል።

መኖር እንመኛለን ግን የሌላው አለመኖር አያሳስበንም፡ መራብ አንፈልግም የሌሎች እርሀብ ግን አያመንም፡ ሰላም እንፈልጋለን ግን የሌሎች ሰላም እናናጋለን፡ መደሰት እንወዳለን ግን ሌሎች እንዲያለቅሱ ምክኒያቶች ነን።

በእውነት ምኑም ነገር አልገባንም፡ ብኩኖች ብቻ ነን ፡ ሸክላነታችን ያልገባን ፡ ነገን ለመኖር ዋስትና የሌለን ከንቱዎች፡ አፈርን ካፈር ለመለየት የምንዳክር ቂሎች
ስጋችን የተለቀ ፣አስተሳሰባችን ያልታረቀ ፣ አካሄዳችን እና ምግባራችን የተናቀ ምስቅልቅሎች፡ ምኑም ነገር አልገባንም።

ለክብርና ለዝና ፡ ለሀብትና አድሮ አመድ ለሚሆን ስጋችን ባሪያዎች የሆንን፤ የምንፈልገው አይገባንም ፡ የሚያስፈልገን አይታየንም፡ የውስጣችንን ባዶነት በጩህትና ባለባበስ ለመሸፈን የምንዋትት አሳዛኞች፡ ከፈጣሪ ትዛዝ ይልቅ የፍላጎታችን ባሪያወች ፡ ከፍርቅር ይልቅ የጥላቻ ፈረሶች ፡ የሰውነት ክብራችንን ያጣን፣ ጥጋብ ምንሆነውን ያሳጣን ፣ ከቁጣው መቅሰፍት ያልወጣን
ጅሎች ሆነናል ፡፡ የምንናገረውን አናቅም፡ የምናምነውን እሱን አንሰማውም፡ የቃል ሰዎች ብቻ ነን።

ሀጢታችን በፊታችን የተገለጠ ነው፡ ግን ክብራችን ይመስለናል ፡፡ እምናደርገውን አናስተውልም ፣ እየሆነ ያለው ሁሉ አይገባንም፡፡ የፈጣሪ እዳ አለብን ፡ እጃችን ባዶ ነው ፡ ለዛውም የተጨማለቀ ። አልገባንም ሀጢያታችን በዝቷል ፡ ውጤቱንም እያየነው ነው ፡፡

ከሩጫችን ረጋ እንበል፣እናስተውል ፣እንመለስ፣ ሰው እንሁን ፣ አስተሳሰባችንን ከሰውነት ሚዛን አናስወጣው ፡፡ አልረፈደም እንፀልይ ፡ የፈጠረን አምላክ ለይቅርታ የታመነ ነው።

ሰላም፣ ፍቅር፣ ጤንነት ፡ለሰው ልጆች ሁሉ ይሁን !


Samuel Adane
@sam2127
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን

የምንም ግዜ ተወዳጅ የሆነው

➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
አዘጋጅ፦ @Daniel_bewketu
@Daniel_bewketu
➟➟➟➟➟➛➟➟➟➟➟


Forward from: Samuel Adane
  🔶የደስታ ሁሉ ምንጭ አእምሮ ነው ፣ የመከራ የሥቃይ ምንጭም ራሱ አእምሮ ነው ፡የአዕምሮአችንን ተፈጥሮ በትልቅ ተረድተን ከተጠቀምበት እውነተኛ ደስታ እና የነፃነት ውጤት ማግኘት እንችላለን ፡፡

💚 ወዳጄ ሆይ አንድን ነገር ለመረዳት ስትፈልግ ያንን ነገር መውደድ ይኖርብሀል ፣ስትወደው ሕይወት ቀላል ይሆናል። ከዚያ ስሜት በሚነካ ሁኔታ ነገሮችን ማስተዋል እና መረዳት ትጀምራለህ።ሁሉንም ለመረዳት ግን መጀመርያ በልብህ ውስጥ ፍቅር ሊኖርህ ይገባል ፡፡

♦️ወዳጄ ሆይ ማንነትህን ጠንቅቀህ ስትረዳ ዋጋህን ታውቀዋለህ ።የምትኖርበትን እና የምትኖርለትን ትለያለህ ።ወደ አዚች ምድር የመጣኧው ለምክንያት ነው ። አንተ የዚህች አለም ገፅ ውብ እና ሙሉ ይሆን ዘንድ እንደ አንዱ ጡብ ነህ ።ዋጋህን ባለመኖርህ አትተምን በመኖርህ እንጂ።የአንተ መኖር ለሌሎቹ ጡቦች ድጋፍ እንዲሁም ለግንባታው ውበት አስፈላጊ ነው።

💛 ይህን ባስተዋልክ ጊዜ ራስህን ነፃ ታወጣለህ ፣ፍቅር ሲኖርህ ደግሞ የማንም ትዕዛዝ ሳያስፈልግህ የሰዎችን ሥቃይ የሚያስታግስ መንገድ ትፈጥራለህ።

መልካም ምሽት❤️
🔶♦️🔶♦️🔶♦️🔶♦️🔶♦️
@TIBEBnegni
@sam2127


ምን አለበት?

samuel Adane
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni


"ሳውልም በእርሱ መገደል ተስማምቶ ነበር"
+=========================+
የመጀመሪያው ሰማዕት ዲያቆን እስጢፋኖስን በግፍ ከቤተ ሳይዳ መግቢያ ከአንበሳ በር አውጥተው በድንጋይ ወግረው በግፍ እንዴት እንደገደሉት ዝርዝር ታሪኩ በሐዋርያት ሥራ ላይ ተጽፎአል:: የታሪኩ ማብቂያ ላይ ያለው ዐረፍተ ነገር እስጢፋኖስን በጭካኔ በድንጋይ ከቀጠቀጡት ሰዎች ጋር አብሮ ባይቀጠቅጠውም የሌላ አንድ ተሳታፊ ስም ተጠቅሶአል:: "ሳውልም በእርሱ መገደል ተስማምቶ ነበር" (ሐዋ. 7:60)

በዚያች የምታሳዝን ዕለት ራሳቸው ከሳሽ ራሳቸው ፈራጅ የነበሩት ጸሐፍት በጭካኔ ታውረው ሆ ብለው በእስጢፋኖስ ላይ ተነሥተውበት ነበር:: በዚያ ባለ ብዙ ተስፋ ወጣት ላይ የድንጋይ ዶፍ ሲያወርዱ ትንሽ እንኳን አልዘገነናቸውም:: ይቅር በላቸው ከማለት ውጪ ክፉ ያልወጣውን ምስኪን ክርስቲያን ወጣት ያለ ርኅራኄ ቀጥቅጠው ገደሉት::

በዚያች ዕለት ሳውል ተሳትፎው ምን ነበር? እርግጥ ነው በእጁ ድንጋይ አልያዘም:: በእስጢፋኖስ ጭንቅላት ላይ ጉዳት ለማድረስ እጆቹን አላስወነጨፈም:: ነገር ግን አንድ እውነታ መካድ አይቻልም:: ሳውል በእስጢፋኖስ መገደል ተስማምቶ ስለነበር በቀጥታም ባይሆን በተዘዋዋሪ ከእስጢፋኖስ ሞት ጋር ስሙ አብሮ ተነሥቶአል::

የሰው ልጅ ሁኔታዎች ከተመቻቹለት ፍጹም አዛኝ መልአክ መሆን እንደሚችል ሁሉ ሁኔታው ከተመቻቸለት ፍጹም አውሬ የመሆን እምቅ ችሎታ ያለው ፍጡር ነው:: ጭካኔም ሆነ ርኅራኄ ከየትኛውም ዘር ብትወለድ ሊኖርህ የሚችል ነገር ሲሆን በሕግ በሃይማኖትና በሰብአዊነት መርሆች ካልተገታ በስተቀር የሰው ልጅ የማያደርገው ክፉ ነገር እንደሌለ የዓለም ታሪክ ያስረዳል::

በዘመናችን የምናየው የንጹሐን ግድያ ላይ በቀጥታ የሚሳተፉና ብዙ እስጢፋኖሶችን በግፍ የሚገድሉ ጨካኞች አሉ:: በሕግ የሚጠየቁትም የሚቀጡትም እንደዚህ ያሉት ቀጥተኛ ተሳታፊዎች ናቸው::

ሆኖም በእኛ ሀገር በቁጥር እጅግ የሚበዙት እስጢፋኖስ ላይ ድንጋይ ከወረወሩት አይሁድ ይልቅ በእስጢፋኖስ መገደል የተስማሙት ሰዎች ናቸው:: ከሩቅ ሆኖ "ተነሣ በለው" ማለት ያም ባይሆን "እዚህ ሰፈር ሰው ተገደለ" ሲባል "እዚያ ሰፈርስ ሞቶ የለ ወይ?" እያሉ ለማካካስ መሞከር : ይበለው ይበላት ብሎ መናገርም በእስጢፋኖስ መገደል መስማማት ነው::

ወዳጄ በክፋት ውስጥ በቀጥታ መሳተፍም : ከሩቅ ሆኖ ቃላት መወራወርም : ጥላቻን መዝራትም : ሌላውን እየናቁ ራስን መኮፈስም ዞሮ ዞሮ በፈጣሪ ፊት ስለ ንጹሐን ደም ማስጠየቁ አይቀርም::

እስጢፋኖስን የመሰሉ በግፍ የተገደሉ ሁሉም ሰማዕታት በፈጣሪ ዙፋን ፊት ቆመው "እስከመቼ አትፈርድም?" ማለታቸው ስለማይቀር ሳናውቀው ዕዳ በራሳችን ላይ እንዳናከማች ከየትኛውም የጥላቻ ንትርክ ራሳችንን እናውጣ::

እስጢፋኖስ ሲገደል ሳውል የተስማማ ቢሆንም በመጨረሻ ግን "ይቅር በላቸው" በሚለው የእስጢፋኖስ ጸሎት ምክንያት በክርስቲያኖች መገደል ከመስማማት ወጥቶ በክርስትናው መከራ የተቀበለ ሐዋርያ ሆነ::
በጣም የሚደንቀው የእስጢፋኖስን ቤተሰቦችም ያጠመቀው በልጃቸው መገደል ተስማምቶ የነበረው ሳውል (ጳውሎስ) ነበረ:: የልጃችን ደም አለበት ሳይሉ ይቅር ብለው የተጠመቁት ጥፋትን በጥፋት ማረም እንደማይቻል ተረድተው ነበር:: ክርስትና ዘር ቆጥሮ የእኔን ወገን እንዲህ አድርገሃል ብሎ የመበቀል ሕይወት ሳይሆን
ባለፈ የጥላቻ ቁስል ማነከስን ትቶ በይቅርታ ዛሬና ነገን መኖር ነው:: ለትውልድ ቂም ማውረስ ለልጅ መርዝ ከማጠጣት አይተናነስም : ይቅርታን ማስተማር ግን ለልጅ በሰማይም በምድርም ርስት እንዲያገኝ ማድረግ ነው::

ኢትዮጵያ እግር አውጥታ ከእኛ እንዳትሸሽ እነዚህ ሦስት ነገሮች ከእንግዲህ በሀገራችን አይኑሩ

- በግፍ የሚገደል እስጢፋኖስ
- በግፍ የሚገድሉ ፈሪሳውያን
- በእስጢፋኖስ መገደል የሚስማሙ ሳውሎች

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ሐምሌ 9 2012 ዓ ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ


@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni


ምን አይነት ፍቅር❤️ ነው?
ምን አይነት ትህትና ?
ከዙፍኖ ወርዶ
በከብቶቹ በረት ተኝቶ የጸና።
ምን አይነት መውደድ❤️ ነው ?
ምን አይነት ታአምር?
ክብሩን አሳንሶ ሰው ሆኖ የሚምር።
።።።።አምላክ ተወለደ   ተወስኖ እንደሰው፣
        የጥልን ግድግዳ በፍቅር ሊያፈርሰው ።
         ሰበኣሰገል መጡ፦
         እጅ መንሻ ይዘው ለክብሩ ሰገዱ፣
         መላክት ከሰማይ
እረኞች ከምድር ለጌታ መወለድ ምስጋና አወረዱ ።
።።።።
........ይመስገን ዛሬም ይመስገን፨
........መዳን ሆነልን ሰው ሲሆን፨
........እናቱ ድንግል ወላዲቱ ፨
.......ጸሀይን  ወልዳ ለፍጥረቱ፨
አለሙ ሁሉ ብርሀን ሆነ ።
ጨለው🌑 ዘመን ተከደነ።

--------------------
28.....04.....16
---------------------

melkam beal

@TIBEBnegni


አለመናገሬን እናገረው ብየ መርጨ ባወጣም ፣
ዝምታየን ጥሶ
ነገሬን የሚውጥ ሰሚ እንደሁ አይመጣም ፣
እናም እንዳንዴ ባለ መናገር ውስጥ
መናገር ባይቻል ፣
ትርጉም ካጣ ጩኸት
እውነትን ያዘለ ዝምታ ይመቻል::

samuel Adane

01/09/13
🌿❤️🌿❤️🌿❤️🌿❤️🌿❤️🌿❤️🌿

@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni


በልተን ፡ ተናግረን ፡ ሰርተን ፡ አልቅሰን ፡ስቀን የምንጨርሰው የኑሮ መስተጋብር ይኖር ይሆናል እንጂ
አለምንና በአለም ላይ ያለውን ሁሉ ኖረን አንጨርሰውም ፡በልኩ እና በአግባቡ መኖር አለብን፡፡ ቅጥ የሌለውና ገደብ የለሽ ፍላጎታችንን መስመር ልናበጅለት ይገባል፡፡ ሁሉም ነገር ስለኛ ተፈጠረ እንጂ እኛ ስለሁሉም አልተፈጠርንም እና ያየነው እና የሰማነው ሁሉ ሊገዛን አይገባም፡፡ ሁሉም ነገር ልክ ሲኖረው ያምራል፡፡ በልኩ ስትበላ ጤነኛ ትሆናለህ፡ በልክ ከጠጣህ አትስከርም ፡ በልክ ከተናገርክ ሰሚ ይኖርሀል፡ በልክ ከተጓዝክ አትሰናከልም፡፡ አብዝተህ ሰውን ከመውደድ ፡አብዝተህ ቅን እና መልካም ከመሆን ውጭ ፡፡ኑሮህን በሙሉ በልክ አድርገው። ያኔ ሰላምና የተረጋጋ ህይወት ይኖርሀል። አመስጋኝም ትሆናለህ፡፡ የተሰራው መንገድ ሁሉ መሄጃህ አደለም መድረሻህን የሚያሳምረውን መንገድ ብቻ ተጓዝ፡፡ መስመርህን አትሳት፡ አምሮህ ብዙ ጊዜ የሚጨነቀው ፡ከልክ በላይ ነገሮችን ለማሟላት ከመነጨ ፅኑ ፍላጎት የተነሳ ነው፡፡ በተሰጠህ እንጅ በሮጥከው ልክ አትኖርም፡፡ ደስታን ትፈልጋለህ?እንግዲያውስ ሁሉን ነገር በልክ አድርገው ፡ከተሰጠህ ላይ መስጠትን ልመድ፡፡ በዙ አትመኝ ፡ ያለህ እንዲባረክ ዘወትር አመስጋኝ ሁን!!!

ፈጣሪ ለሰው ልጆች ሁሉ ሰላም ፍቅር አንድነትን ያብዛ። አሜን


@sam2127

💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚
ሌሎች እንዲማሩና እንዲለወጡ እናድርግ
ያወቅነውን እናሳውቅ፡ በፍቅር እንኑር፡፡
💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙


@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni


🌿🌿🌿🌿🌿🌿
01/01/2016
🌿🌿🌿🌿🌿🌿
አለም ፍትህ የላት
    ስንቶች በጭካኔ በሞት ተወሰዱ
    በርሀብና በጥም በእስር ተጎዱ
በአይናችን እያየን ስንቱ ተቀሰፈ
ፍትህ ጠፍቶ በአለም ደም እየጎረፈ....
🌲

....እስኪ ልጠይቅህ ንገረኝ ጌታዬ
      ለምን ?ካለፉት ጋር
      ለምን ?ከሞቱት ጋር አልሆነም እጣዬ
🌲
እንዴት ብትወደኝ ነው 🌿🌿🌿
ከሞት ሰልፍ አውጥተህ..
    ቀን የጨመርክልኝ እድሜ ለንስሓ
     ስበህ ያወጣሀኝ ከሃጢአት በረሓ
🌲
እንዴት ብትወደኝ ነው 🌿🌿🌿🌿
    ሙሉ ያደረግከኝ በፊትህ ስጎድል
    ዳግም የሰጠከኝ የንስሀን እድል
እንዴት ብትወደኝ ነው... 🌿🌿🌿

  ዘመን ያሻገርከው አሮጌው ሂወቴን
  ንቀህ ያልገፋከው ብኩን ማንነቴን ።

እንዴት ብትወደኝ ነው....????
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿


💚💚💚
ብቻ ላመስግንህ...
 ከፊትህ ባልነፃም
ግብሬ ና ነገሬ ከእንስሳት ባይሻል
ይቅር በለኝ እያልኩ ይነጋል ይመሻል ።
💚💚💚
ብቻ ላመስግንህ

💙ተመስገን የኔ ባት💙
💙ተመስገን ጌታዬ💙
💙ተመስገን አምላኬ💙
💙ተመስገን ተመስገን ዘላለም💙
💙ሁሉን ትችላለህ ሁሉን ታደርጋለህ የሚቀድምህ የለም .. 💙
💚💚💚ተመስገን!!!!!!💚💚💚

🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
አምላካችን ቅዱስ እግዚአብሔር አዲሱን አመት 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

በረከቱን አብዝቶ
ምህረቱን አጉልቶ
ፍቅር💙 ሰላምን ሰጥቶ
ለስጋ ወደሙ አብቅቶ ያኑረን
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
🙏🙏🙏አሜን🙏🙏🙏

መልካምና በጎ አዲስ አመትን ተመኘሁ
በጸሎት አስቡኝ።


sami
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni


"አንተ ልትበላው ያልፈለግኸው እንጀራ የተራቡት ሰዎች እንጀራ ነው። በቁም ሳጥንህ ውስጥ ሰቅለህ የተውከው ልብስ ዕርቃኑን የሆነው ሰው ልብስ ነው። የማታደርጋቸው ጫማዎችህ ባዶ እግሩን የሚሔድ ሰው ጫማዎች ናቸው። የቆለፍክበት ገንዘብ የደሃው ገንዘብ ነው። የማትፈጽማቸው የቸርነት ሥራዎች ሁሉ ኢፍትሐዊ ድርጊቶችህ ናቸው"
ቅዱስ ባስልዮስ

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni


እ .. ረ .. ስ .. ቸ .. ዋ .. ለ .. ሁ ..!!

አንድ ምስኪን ሴት ወደ አንድ መንፈሳዊ አባት ዘንድ ቀርባ "እግዚአብሔር ሁሌም ያናግረኛል" ትላቸዋለች። በሴትየዋ ሁኔታ ግራ የተጋቡት እኚህ አባትም በሁኔታው ተበሳጭተው ጥለዋት ይሄዳሉ። ከዚያን ቀን በኋላ እቺ ሴት እየደጋገመች በመምጣት "እግዚአብሔር ማታ ማታ እየመጣ ያናግረኛል" ትላቸዋለች። በሴትየዋ ጭቅጭቅ የተሰላቹት እኚህ አባትም እንደለመደችው አንድ ቀን መጥታ ስታናግራቸው እንዲህ አሏት "እውነት አንቺን እለት እለት እየመጣ ፈጣሪ የሚያናግርሽ ከሆነ አምንሽ ዘንድ አንድ የቤት ስራ ልስጥሽ" አሏት ትኩር ብለው እየተመለከቷት! ሴትዬይቱም የሚሏትን ሁሉ ለማድረግ ቃል ገባች! እኚህ አባትም ከዚች ሴት ጭቅጭቅ ይገላግለኛል ያሉትን ጥያቄ አቀረቡላት እንዲህ በማለት "እውነት አንቺን እግዚአብሔር የሚያናግርሽ ከሆነ እስቲ ዛሬ ማታ አንድ ጥያቄ ጠይቂልኝ" አሏት። ሴትየዋም በእርጋታ "ምን ልጠይቅልዎ አባቴ?" አለቻቸው። "ለረጅም አመት ልተወው ያልቻልኩት የዛሬ ወር ገደማ ግን ንስሐ ገብቼ የተውኩት አንድ ኃጢአት እሰራ ነበር። ያ በፊት እሰራው የነበረ አሁን ግን ንሰሐ ገብቼ የተውኩት ኃጢአት ምን እንደነበረ ጠይቀሽ ንገሪኝ። እሱን ከነገረሽ እውነትም ላንቺ እግዚአብሔር እንደሚናገር አምናለሁ" አሏት። ሴትዬይቱም ወደቤቷ ሄደች።
ተመልሳ እንደማትመጣ ግን ገምተው ነበር አባ ነገር ግን በበነጋው ያቺ ሴት መጥታ አባን አስጠራቻቸው። አባም ሴትየዬቱን ሲያዩ በጣም ተገርመው ወደሷ በመሄድ በፌዝ መልክ "እህስ ልጄ እግዚአብሔርን ንስሀ ገብቼ ያቆምኩት ሀጢያት ምን እንደነበር ጠየቅሺው?" አሏት ሳቅ እያሉ "አዎን አባ" አለቻቸው ሴትየዋ አንገቷን እንዳቀረቀረች "እህሳ ምን አለሽ?" አሏት አባ በመጓጓት "እረስቸዋለሁ አለኝ" አለቻቸው፡፡ እኚህ መንፈሳዊ አባት ባልገመቱት የእግዚአብሔር ምላሽ ልባቸው ተነክቶ ስቅስቅ ብለው እያለቀሱ ወደደረታቸው አስጠግተው አቀፏት!

እ .. ረ .. ስ .. ቸ .. ዋ .. ለ .. ሁ ..!!
የሰው ልጅ ሙሉ ይቅርታ የለውም። ዛሬ ምን ፍሪዳ አርዶ ቢታረቅህ፣ ምን በልቅሶ ታጅበህ እየተንፈራፈርክ ይቅር በለኝ ብትለው "ይቅር ብየሀለሁ" ይልህና የሆነ ቀን ስታስቀይመው ይቅር ያለውን በደልህን እየቆጠረ ሲወቅስህ ይውላል እግዚአብሔር ግን ይቅር ካለህ በቃ ረሳው ፍቅር ነዋ፤ ስንቶቻችን እንሆን እግዚአብሔርን በኛ መጠን መትረን ንስሐ በገባንበት ኃጢአት ዘወትር የምናለቅስ? ስንቶቻችን እንሆን እግዚአብሔር እንደኛ ቂመኛ መስሎን በፍቅር ሂፆጱ ያጠበውን ኃጢአታችንን እያስታወስን ዘወትር በፀፀት እሾህ ራሳችንን የምንገርፍ? ይቅርታ ከመለመን እኮ ይቅር ማለት ይከብዳል! ምሬሀለሁ ከማለት ማረኝ እያሉ እግር ስር መደፋት ቤት በቀለለ! በህይወታችን የገፋንና ያቆሰለንን ሰው በደል ከመርሳትኮ ሺህ ጊዜ ፍሪዳ እያረዱ "እንታረቅ" ማለቱ እጅግ ቀላል ነውኮ ...! ለዚያም ነው መሰል ኢየሱስ ክርስቶስ ፀሎት አስተምረን ባሉት ጊዜ "እኛም የበደሉንን ይቅር እንደምንል አንተም ይቅር በለን" ብላችሁ ፀልዩ ያለን፡፡
እግዚአብሔር አምላክ የይቅርታ ዘመን ያድርግልን የይቅርታ ልብ ይስጠን
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni


የምጽዋት ብዛት የሚመዘነው በሚሰ’ጠው ገንዘብ ቁጥር ሳይኾን ስጦታውን በሚሰጥ የልብ ስፋት ነው፡፡ አንዲት ድኻ ሴት ያላትን ጥቂት እንጀራ ምንም ከሌላት ከሌላ ሴት ጋር ተካፍላ የምትበላ ከኾነ፥ ወርቅን በሙዳዬ ምጽዋት ከሚጨምር ባለጸጋ ሰው እጅግ ትበልጣለች፡፡ ነገር ግን ምንም እንኳን ይህ እውነት እንደ ኾነ ብዙ ክርስቲያኖች ቢያውቁም፥ ምስጋና የሚሰጡት ወርቅ ለሰጠው ነው፡፡
አንድ ባለጸጋ ጠቀም ያለ ገንዘብ ለቤተ ክርስቲያን ቢሰጥ እጅግ ያመሰግኑታል፤ ካለው የሀብት ብዛት የተነሣ ያንን በመስጠቱ ምንም ባይጎድልበትም እንኳ፥ በሰዎች ዘንድ እጅግ ቸር እንደ ኾነ ተደርጎ ይንቆለጳጰሳል፡፡ ድኻው ጥቂት ገንዘብ ቢሰጥ ግን ሰዎች ስለ እርሱ ምንም ትንፍሽ አይሉም፡፡ ምናልባት ያቺ የሰጣት ገንዘብ’ኮ በኋላ እርስዋን በማጣቱ ምክንያት ተርቦ እንዲያድር ልታደርገው የምትችል ትኾን ይኾናል፤ ነገር ግን ይህን በማድረጉ የሚያመሰግነው አንድ ሰውስ እንኳ አይገኝም፡፡ በእውነት ያለ ሐሰት ምንም ሳይጎድልበት የሰጠውን ባለጸጋውን አመስግኖ ያለውን ኹሉ የሰጠውን ድኻ ሳያመሰግኑ ከሚቀሩ ከእነ ጭራሹ ምስጋና ባይኖር ይሻል ነበር፡፡
ስለዚህ እውነተኛ ምጽዋት የሚባለው የባለጸጋውም ይኹን የድኻው በአግባቡና በሥርዓቱ ልናውቀው ይገባናል፡፡ ማመስገን የሚገባንም ከዚያ በኋላ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር የምስጋናችን ስጦታም ሰዎች ከልባቸው ከሚሰጡት ገንዘብ ብዛት አንጻር ሊኾን ይገባል፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ:
🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿

@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni


የእግዚአብሔር ጸጋ

የእግዚአብሔር ጸጋ ማንንም ሳያስቀር ሰዎችን ሁሉ ስለሚጎበኝ ኃጢአተኞች እንኳ ከዚህ የእግዚአብሔር ጸጋ ጉብኝት ተቋዳሾች ናቸው። ስለ ጌታችን እንዲህ ተብሎ ትጽፏል “እርሱም መልካም እያደረገ ለዲያብሎስ የተገዙትንም እየፈወሰ ዞረ” ሐዋ. 10፥38። እርሱ የጠፉት ነፍሳት ባለመታመናቸው በልበ ደንዳናነት ከእርሱ ርቀው ቢጠፉም እርሱ ግን መፈለጉን አላቋረጠም። የነበሩበት እጅግ ተስፋ የሚያስቆርጥ ቢሆንም እንኳ መልሶ እስከሚያመጣቸው ድረስ ፍለጋው አልተቋረጠም።

ሰዎች ስለ ድኅነታቸው ተስፋ የሚቆርጡ ቢሆኑም እንኳ እግዚአብሔር ግን በሰዎች ላይ ተስፋ ማሳደሩን አያቋርጥም። እግዚአብሔር በመንፈሳቸው የደከሙትን ቀርቶ ሞቶ ሥጋው በመሽተት ላይ ያለውን ሰው እንኳ ሳያስቀር ለሁሉም ሁሉ ጊዜ በጎ ነገርን ይሰራል። (ዮሐ. 11፥39) ከዚህ በተጨማሪ እርሱ በሕይወቱ የመጨረሻ ህቅታ ለነበረው ወንበዴ፣ ለቀረጥ ሰብሳቢው ዘኪዎስና አምስት ባሎች ለነበርዋት ሳምራዊት ሴት ይሰራ ነበር። (ሉቃስ. 23፥43፣ ሉቃስ. 19፥9፣ ዮሐ. 4፥18)። እርሱ ያቺ ጠፍታ የነበረችው ሳምራዊት ሴት ወደ ንስሐ ሊመራት ያለችበት ድረስ ሄዶ ፈልጓታል።

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የእግዚእብሔርን ፍቅር በማስመልከት “እግዚአብሔር ለድኅነታችን ምክንያት ይሆን ዘንድ አንዲት ዘለላ እንባ እንኳ ትበቃዋለች። ይህች ዘለላ እንባ የከንቱ ደስታ ባለቤት በሆነው በዲያብሎስ ከመነጠቅዋ በፊት ለእኛ ለድኅነታችን ምክንያት እንድትሆን እግዚአብሔር ይቀበላታል” ብሎ ነበር።

በእርግጥ ከእኛ ልቦናዎች ይበልጥ እጅግ ርኅሩኅ ከሆነው ከአምላካችን ልብ የሚበልጥ የለም። ይህንን በማስመልከትም አምላካችን እግዚአብሔር እንዲህ ብሏል “ቀኑን ሁሉ ወደማይታዘዝና ወደ ሚቃወም ሕዝብ እጆቼን ዘረጋሁ” (ሮሜ. 10፥21፣ ኢሳ. 65፥2)።

አምላካችን እግዚአብሔር ኃጢአት እንጂ ኃጥእ አይጸየፍምና ያለ አድልዎ ለሁሉም በእኩል ዓይን ይጎበኘዋል።
ብፁእ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ

🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿

@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni


ልበ ንጹሓን ብፁዓን ናቸው፤ እግዚእብሔርን ያዩታልና›› ማቴ. ፭፥፲

በዘመነ ሥጋዌ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከናዝሬት ወደ ቅፍርናሆም በሔደ ጊዜ የገሊላ፣ የኢየሩሳሌም፣ የይሁዳ እና የዮርዳኖስ ሕዝብ ዝናውን ሰምተው ወደ እርሱ መጡ፡፡ በዚያም የመንግሥቱንም ወንጌል ሲሰብክ ‹‹……ልበ ንጹሐን ብፁዓን ናቸው፤ እግዚአብሔርን ያዩታልና…….ደስ ይበላችሁ፤ ሐሤትንም አድርጉ፤ ዋጋችሁ በሰማያት ብዙ ነውና፤ ከእናንተ አስቀድሞ የነበሩ ነቢያትንም እንዲሁ አሳድደዋቸው ነበርና፡፡›› ብሎ አስተማራቸው፡፡ (ማቴ.፭፥፩-፲፪)

ጌታችን ነቢያት ያላቸው ጻድቃን እግዚአብሔር አምላካቸውን የሚያገለግሉ ነበሩና ጠላት ዲያብሎስ ሲያሳድዳቸውና ሲያሰቃያቸው ኖሯል፤ ሆኖም ፈጣሪያቸው ሁል ጊዜ ከእነርሱ ጋር ስለነበር ጠላታቸውን አሸንፈውታል፡፡ በችግር እና መከራ ጊዜም እግዚአብሔር አምላክ ያበረታቸው ነበር፤ በቃሉ አሰምቶ በፊታቸውም ተገልጦ አናግሯቸዋል፡፡ በኦሪት ዘጸአት ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፩ ላይ እንደተጻፈው እግዚአብሔር አምላክ የእስራኤልን ሕዝብ ነጻ እንዲያወጣ በወደደ ጊዜ ለነቢዩ ሙሴ ተገልጦ እንዲህ አለው፤ ‹‹አሁንም እነሆ÷ የእስራኤል ልጆች ጩኸት ወደ እኔ ደረሰ፤ ግብፃውያንም የሚያደርጉባቸውን ግፍ ደግሞ አየሁ፡፡ አሁንም ና፤ ወደ ግብፅ ንጉሥ ወደ ፈርዖን እልክሃለሁ፡፡ ሕዝቤን የአስራኤልን ልጆች ከግብፅ ምድር ታወጣቸዋለህ››፡፡

ዳግምም ምስክሩን ለሚጠብቁ እርሱ በፈቀደ ይድኑ ዘንድ ለነቢዩ ዳዊት እንዲህ አለው፤ ‹‹ከሆድህ ፍሬ በዙፋንህ ላይ አስቀምጣለሁና፤ ልጆችህ ኪዳኔን÷ ይህንም የማስተምራቸውን ምስክሬን ቢጠብቁ፥ ልጆቻቸው ደግሞ በዙፋንህ ላይ ለዘለዓለም ይቀመጣሉ››፡፡ (መዝ. ፻፴፩፥፲፩) ነቢያት ልበ ንጹሐን ናቸውና አምላካቸውን አይተውታል፤ ለቃሉ ተገዝተው፣ በሕጉ ተመርተው በጾም በጸሎት ተግተው ስለኖሩ መንግሥተ ሰማያትን ወርሰዋል፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ቅን ልቡናን ይወዳል፤ ‹‹አቤቱ ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ›› ሲል ነቢዩ ዳዊት እንደተማጸነው (መዝ. ፶፥፲) ክርስትናን የተቀበለ ፍጡር በሙሉ ይህን ሊመኝ እና ልብን ንጹሕ ሊያደርግ ይገባል፡፡

የልብ ንጽሕና

ሰው ኃጢአትን ጨርሶ ሲጠላ፣ ኃጢአትንም ሁሉ ሲተውና ከልቡናው ፈጽሞ ሲያጠፋው የልብ ንጽሕናን ያገኛል፡፡ ሰው ኃጢአትን ጨርሶ መጥላቱ ሊታወቅ የሚችለው የሚከተሉትን ሲያደርግ ነው፡፡

፩. ከኃጢአት በመንፃት

ሀ) ሰው በናቃቸው ኃጢአቶች ሁሉ ላይ ንስሐ መግባት አለበት፤ ኃጢአትንም ሁሉ መተውና ከልቡናው ፈጽሞ ማጥፋት አለበት፤

ለ) ከኃጢአት መንፃት የምንችለውና ከንጽሕና ደረጃ የምንደርሰው ከእግዚአብሔር ጋር ስንሆን ነው፤ ‹‹እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ባይሆን ሰዎች በእኛ ላይ በተነሡ ጊዜ ቁጣቸውም በላያችን በነደደ ጊዜ፥ በዚያን ጊዜ ሕያዋን ሳለን በዋጡን ነበር››(መዝ. ፻፳፫፥፪-፫)

ሐ) እግዚአብሔር በፀጋው ከልሎ በቸርነቱ ጠብቆ ከኃጢአቱ ሊያሳርፈን ይችላል፤ ይህም ንጽሓን ስለሆንን አይደለም፤

መ) ትላልቅ ሰዎች ከሕፃናት ይልቅ ስለሚፈተኑ በጦርነቱ ውስጥ ሆነው ተዋግተው ያልፋሉ፡፡ የኃጢአትንም ኃይል ተቃውመዋልና የድል አክሊል ያገኛሉ፡፡ የልብ ንጽሕና ፍጹም ንጽሕና ማግኘት ነው፤ ፍጹም ንጽሕና ከኃጢአት ሁሉ መንፃት ነውና፡፡

፪. ስለ ንጽሕና መፈተን

ሰው ንጹሕ ሊባል የሚችለው እጅግ ከባድ የሆነ የኃጢአት ፈታና ቢደርስበት እንኳ ሳይናወጥ የኃጢአትን ኃይል የተቋቋመ እንደሆነ ነው፡፡ ንጹሕ ልብ አለን የምንባለው በኃሳብ፣ በስሜት፣ በመናገር፣ በአካል እንዲሁም በማድረግ ከሚሠሩ ኃጢአቶች ሁሉ ልቡናችንን ያነፃን እንደሆነ ነው፤ እግዚአብሔር በሰጠው ፀጋ ታግዞ እነዚህን ሁሉ ኃጢአቶች ተዋግቶ ያሸነፈ ሰው ነው፡፡ እግዚአብሔርን የሚያየው ይህም የመጨረሻው የንጽሕና ምዕራፍ ነው፤ ‹‹ልበ ንጹሐን ብፁአን ናቸው፤ እግዚእብሔርን ያዩታል›› እንደተባለው፡፡ (ማቴ. ፭፥፲)

፫. ከክፉ ሀሳብ መንፃት

ከሀሳብና ከግምት፣ ከመላምትም መንፃት ይገባል፡፡‹‹መልካም ሰው ከልቡ መልካም መዝገብ መልካሙን ያወጣል፤ ክፉም ሰው ከልቡ ክፉ መዝገብ ክፉውን ያወጣል››(ሉቃ. ፯፥፵፭)፡፡ ሀሳባችን ክፉ ከሆነ ልባችን ገና አልነፃም፤ ልበ ንጹሑ የሆነ ሰው ምንጊዜም ቢሆን የሚያስበው መልካም ነገርን ነውና፡፡ አእምሮአችን ንጹሑንና ለንስሐ ሕይወት የሚሳማማውን ሀሳብ እንዲመዝገብ ይሆናል፤ ያኔ የሚያልመው ነገርም ንጹሕ ይሆናል፡፡

፬. ከማያስፈልጉ ነገሮች መንፃት

ከማያስፈልጉና ጥቅም ከሌላቸው ነገሮች መንፃት ማለት ነው፤ ለምሳሌ የሚሠሩ፣ የሚነበቡ፣ የሚታዩ፣ የሚደመጡ ሆነው ኃጢአትም ጽድቅም ያልሆኑ ነገሮች በመሆናቸው ጊዜያችንን ያባክንብናል፡፡ ‹‹አቤቱ ከንቱ ነገርን እንዳያዩ አይኖቼን መልስ››እንዲል፡፡ (መዝ. ፻፲፰፥፴፯)

፭. የንጽሕና ገጽታ

ንጹሕ ልብ የፍቅረ እግዚአብሔር ማደሪያ ነው፡፡ ንጹሕ ልብ ያላቸው ሰዎች የሚያደርጉትን ሁሉ እግዚአብሔርን በማፍቀር ያደርጋሉ እንጂ ስለታዘዙ አይደለም፡፡ የመንፈስ ቅዱስ ፍሬዎች ማለትም ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም፣ ትዕግሥት፣ ቸርነት፣ በጎነት፣ እምነት፣ የውኃት፣ ራስን መግዛት፣ በግልጽ ይታያሉ፡፡ እነዚህንም የሚከለክል ሕግ የለም፡፡ (ገላ. ፭፥፳፪) ስለዚህ የመንፈስ ቅዱስ ፍሬን ለማግኘት መትጋት አለብን፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ንጹሕ ልቡናን ይፈጥርልን እና በሕይወታችን ይኖር ዘንድ ፈቃዱ ይሁንልን፤ አሜን፡፡

ምንጭ፤ ‹የንስሓ ሕይወት› መጽሐፍ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ፭ኛ የግብፅኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ፤ ውርስ ትርጉም ቀሲስ እሸቱ ታደሰ ወንድምአገኘሁ

ብፁእ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ

🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿

@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni


ዘወትር በሕሊናችን የሚመላለሱትን ሀሳቦች በጥንቃቄ ልንመረምራቸው፣ ወደ ውሳኔ ከመድረሳችንም አስቀድመን ‹‹ለምን?፣ እንዴት?፣ ከዚያስ?›› ብለን መጠየቅ ይጠበቅብናል፡፡ ባለን ዕውቀትም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከምናገኘው ትምህርት ጋር በማጣቀስ መረዳት መቻል አለብን፡፡ ‹‹የቀደመ የሕይወት ተሞክሮዬ ምን አስተምሮኛል?›› ብለንም ልንመረምረው ያስፈልጋል፡፡ ‹‹አጥብቀህ ልብህን ጠብቅ፥ የሕይወት መውጫ እርሱ ነውና››፤ (ምሳ. ፬፥፳፫) ቅዱስ ጴጥሮስ በዲያብሎስ የማስመሰል ርኅራኄው ወጥመድ እንዳንያዝ በንቃት እንድንኖር ያስገነዝበናል፡፡ ‹‹በመጠን ኑሩ ንቁም፥ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና›› እንዲል፡፡ (፩ኛ ጴጥ. ፭፥፰)

ለ/ በትሕትና

ሰይጣን በማስመሰል ርኅራኄው በመቅረብ የበቃውንም ሰው በትዕቢት በከንቱ ውዳሴ ለመጣል የተንኮል ወጥመዱን ይዘረጋል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹እንደቆመ የሚመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ›› (፩ቆሮ. ፲፥፲፪) እንዳለ ጠላት ቀርቦ በትዕቢት እንዳይጥለን ትሕትናን ገንዘብ ማድረግ ይኖርብናል፡፡ ‹‹ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል›› ተብሎም ተጽፏልና፡፡ (፩ኛ ጴጥ. ፭፥፭)

ሐ/ በጸሎት በመትጋት

ጸሎት ከዲያብሎስ የሚላኩብንን የጥፋት ፍላጻዎች ጋሻ ሆኖ የሚመክት መሣሪያችን ነው፡፡ ስለዚህ ዘወትር ሳናቋርጥ በጸሎታችን እግዚአብሔርን በማመስገን፣ ልዕልናውን፣ ቸርነቱንና አዳኝነቱን በማሰብ፣ በፍጹም ልባችን ሆነን ወደ እግዚአብሔር እንጸልይ፤ ‹‹ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ፤›› (ማቴ. ፳፮፥፵፩) ተብሎ ተጽፏልና፡፡ ስለሆነም የዲያብሎስን ፈተና ልንቋቋም ከምንችልባቸው መንፈሳውያት ኃይሎቻችን መካከል ጸሎት ዋነኛው መሆኑን ልንገነዘብ ይገባል፡፡

መ/ ሕዋሶቻችን ከክፉ ሥራ በመጠበቅ

ዲያብሎስ እኛን ለማሳት የሚጠቀመው የገዛ ሕዋሶቻችን ነው፡፡ እነርሱን መቆጣጠር ከቻልን በዲያብሎስ የማስመሰል ርኅራኄ አንታለልም፡፡ ዓይናችን የሚያየውን ክፉና በጎ ነገር፣ ጆሮዋችን የሚሰማውን ሐሰትና እውነቱን ነገር መምረጥ ስንችል፣ አንደበታችን እውነትን ሲናገር፣ እግሮቻችን ወደተቀደሱ ሥፍራዎች ሲያዘወትር ዲያብሎስ በቀላሉ ቀርቦ አያስተንም፡፡ በአጠቃላይ ሕዋሶቻችን ከኃጢአት ሥራ ተለይተው በጎ ነገርን መሥራት ሲጀምሩ በጎን ከክፉ ስለምንለይ በዲያብሎስ የማስመሰል ርኅራኄው ወጥመድ በቀላሉ አንወድቀወም፡፡

ሠ/ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ በመልበስ

ክርስቲያን ዘወትር በንቃት በመዘጋጀት ሕይወቱን ይመራል እንጂ በዘፈቀደ አይመራም፡፡ ‹‹ወገባችሁ የታጠቀ መብራታችሁም የበራ ይሁን›› (ሉቃ.፲፪፥፴፭) ተብሎ በወንጌል እንደተጻፈው፤ ቅዱስ ጳውሎስ የዲያብሎስን ውጊያዎች በድል አድራጊነት ለመወጣት ምን ማድረግ እንዳለብን ሲያጠይቅ ‹‹የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ። መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ሥፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ›› ብሎናል፡፡ (ኤፌ ፮፥፲፩) የጦር ዕቃ የተባሉትን ጾም ጸሎትና መንፈሳዊ ተጋድሎን ጋሻና ጦር አድርገን ከዲያብሎስ የማስመሰል ርኅራኄው ወጥመድ ማምለጥ ይቻላል፡፡

ረ/ በረድኤተ እግዚአብሔር በማመን

ዲያብሎስ በማስመሰል ርኅራኄው ለፈተና ወደ በሕይወታቸን ሲመጣ ‹‹ለምን ወይም እንዴት›› አንበል፤ ይልቅስ በእግዚአብሔር ረድኤት ማመን ይገባናል፤ እግዚአብሔር ማንንም በክፉ አይፈትንምና፡፡ ‹‹ማንም ሲፈተን በእግዚአብሔር እፈተናለሁ አይበል፤ እግዚአብሔር በክፉ አይፈትንምና››፡፡ (ያዕ. ፩፥፲፫) ይልቅስ እንኳን እኛ ጌታችንም ተፈትኗል፤ ‹‹እርሱ ራሱ ተፈትኖ መከራን ስለ ተቀበለ የሚፈተኑትን ሊረዳቸው ይችላልና›› (ዕብ. ፪፥፲፰) ተብሎ የተጻፈልን በፈተናችን ሁሉ መጽናኛ ይሆነን ዘንድ ነው፡፡ ስንፈተን ልንጨነቅ አይገባም፤ ጌታችንም ተፈትኗልና፤ ድል አድርጎም ድል የምናደርግበትን ኃይል ሰጥቶናል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ›› (ፊል. ፬፥፲፫) ብሎ እንዳስተማረን ኃይልን የሚሰጠን አምላክ እንዳለ አምነን ዲያብሎስ በማስመሰል ርኅራኄው የሚያመጣብንን ሥውር ፈተናን በማለፍ ድል ማድረግ እንችላለን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ምንጭ፤ ከ‹‹መንፈሳዊ ውጊያዎች›› ፪ኛ መጽሐፍ፤ በብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ፤ የግብፅኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ፤ ውርስ ትርጉም አያሌው ዘኢየሱስ፤ ፲፱፻፺፱ ዓ.ም.

ብፁእ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ

🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿

@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni


ስለማስመሰል ርኅራኄው ሰይጣንን ተጠንቀቀው

አምላካችን እግዚአብሔር አዳምን ሲፈጥረው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም እንዳልሆነ በማየቱ ከጎኑ አንዲት አጥንትን ወስዶ ሔዋንን ፈጠረለት፡፡ በገነት እንዲኖሩም አደረጋቸው፤ ከአንዲት ዕፅ (የሞት ዛፍ) በቀር ሁሉን እንዲበሉም አዘዛችው፤ ‹‹ከገነት ዛፍ ሁሉ ትበላለህ፤ ነገር ግን መልካምና ክፉን ከሚያሳውቀው ዛፍ አትብላ፤ ከርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና››፡፡ (ዘፍ. ፪፥፲፮) ነገር ግን ዲያብሎስ ወደ እነርሱ ቀርቦ ለእነርሱ ያዘነ በማስመሰል ክፉ ምክርን መከራቸው፡፡ ‹‹ሞትን አትሞቱም፤ ከእርስዋ በበላችሁ ቀን፥ ዐይኖቻችሁ እንዲከፈቱ፥ እንደ እግዚአብሔር እንደምትሆኑ፥ መልካምንና ክፉን እንደምታውቁ እግዚአብሔር ስለሚያውቅ ነው›› (ዘፍ ፫፥፬) አላቸው፡፡ እነርሱም ዲያብሎስ ለእነርሱ አስቦና ራርቶ የመከራቸው ስለመሰላቸው ክፉ ምክሩን ተቀብለው የእግዚአብሔርን ትእዛዝ አፈረሱ፡፡ አስቀድሞ ፈጣሪያቸው ለእነርሱ ያደረገላቸውን ነገር ረስተው በዲያብሎስ የሐሰትና የማስመሰል ምክር ተታለሉ፡፡ ከዚያም ከፍሬው ቆርጠው በሉ፤ ሞትንም ሞቱ፤ ገነትን ያህል ቅዱስ ሥፍራ፤ እግዚአብሔርን ያህል ኃያል ፈጣሪ አስከፉ፡፡

ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ሰይጣን በማስመሰል ርኅራኄው ሰዎችን እያባበለ ኃጢአት ሲያሠራ እና ከአምልኮተ እግዚአብሔር ሲለይ ኖረ፡፡ ሰይጣን ሰዎችን የሚያስትበት መንገድ ረቂቅ፣ እንደየዘመኑ ሁኔታም ተለዋዋጭ ነው፡፡ ሰይጣን ሰውን ሊያስት ሲመጣ እኔ ሰይጣን ነኝ፣ እነሆ ላስታችሁ መጥቻለሁ ተዘጋጅታችኋልን? ብሎ አይመጣም፡፡ ሰዎችን፣ ጊዜን፣ ሁኔታንና ቦታን ምክንያት እያደረገ በማታለያ ንግግሩ ቀርቦ በማስመሰል ሰዎችን ሸንግሎ ያስታል፡፡ የሰይጣን የማስመሰል ርኅራኄው የቱን ያህል አሳሳች እንደሆነ እንኳን አንረዳውም፡፡ ካሳተን በኋላም ያሳተን እርሱ መሆኑን መረዳት እየተሳነን ለውድቀታችን ሰዎችን፣ ዕድልን፣ ሁኔታዎችን እና ጊዜን ሰበብ እንድናደርግ ያደርገናል፡፡ ለዚህ ማሳያ የሚሆነው በተለይ በየጠበሉ ‹‹እከሊት ናት መድኃኒት ያደረገችብሽ፤ እከሌ ነው መድኃኒት ያደረገብህ›› እያለ ራሱን ሲያጋልጥ የምንሰማው የሰዎች ታሪክ እማኝ ነው፡፡ ‹‹ሐሰተኛ ነውና፤ የሐሰት አባትም ነው›› እንደተባለው፡፡ (ዮሐ. ፰፥፵፬) በዚህ ሐሰተኛነቱም አንዳንዶችን የአጋንንቱን ምስክርነት አምነው እንዲካሰሱ ባስ ሲል ወደከፋ ነገር እንዲደርሱ ያደርጋቸዋል፡፡

የሰይጣንን የማስመሰል ርኅራኄው አለማወቃችን ለጊዜ ከሚደርስብን ውድቀት በተጨማሪ በተደጋጋሚና በተመሳሳይ በኀጢአት እንድንወድቅ ያደርገናል፡፡ እርሱ ዘወትር እኛን በድካማችን ለማሳት አይሰለችምና እኛም እርሱ በእንዴት ያለ የማስመሰል ርኅራኄ ቀርቦ እንደሚያስተን ልናውቅበት እና ልንጠነቀቅ ይገባል፡፡

ዛሬ ላይ ሰይጣን እንዴት ባለ የማስመሰል ርኅራኄው ሰውን እየጣለ ነው?

ሀ/ ለራሳችን በምንሰጠው የተሳሳተ ግምት የተነሣ

ዲያብሎስ ትሕትናን ስለሚፈራ ሰዎች ለራሳቸው ከፍ ያለ የተሳሳተ ግምት እንዲኖራቸው ለማድረግ የሰዎችን አንደበት እየተጠቀመ ‹‹አንተ እንዲህ ነህ፤ አንች እንዲህ ነሽ›› እያለ በተሳሳተ መንገድ ይመራል፡፡ ዲያብሎስ ወጣቶችን ለማሳት ‹‹አንተ ወጣት አይደለህ?፤ በዕድሜህ ተዝናና›› በማለት በመዝናናት ውስጥ ያለውን ድቀት በመሸሸግ ለእነርሱ የራራ መስሎ ይመክራል፡፡ እኅቶቻችንን ‹‹አንቺ ወጣት አይደለሽ በዕድሜሽ አጊጪ››፤ ‹‹እግዚአብሔር ልብን ነው የሚያየው›› በማለት የምንዝር ጌጥ እንዲያጌጡ እና ከሥርዓተ ቤተክርስቲያን ውጪ እንዲሆኑ በማድረግ ባላሰቡትና ባልገመቱት መንገድ በፈተና እንዲወድቁ ያዳርጋቸዋል፡፡

የአንዳንድ ሰዎችን አንደበት እየተጠቀመ ዲያብሎስ መንፈሳውያንን ‹‹አንተ የእግዚአብሔር ሰው፣ አንቺ የእግዚአብሔር ሰው፣ ቅን ሰው፣ የዋህ ሰው፣ ጸሎተኛ ነህ፤ ጸሎተኛ ነሽ፤ ጾመኛ ነው፤ ጾመኛ ናት›› በማለት ልባችን ውስጥ ትዕቢት እንዲፈጠር ያደርጋል፤ እያታለለም የሌለንን ቅድስና ያለን እንዲመስለን ያደርገናል፤ በፍጻሜያችንም መንፈሳዊ ተጋድሎዋችን ላይ ድል ይነሣናል፤ ከዚያም በኋላ በቀላሉ በኃጢአት ይጥለናል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ጌታችንን መድኃኒታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ጠቅሶ ሊፈትነው እንደሞከረው መንፈሳውያንንም ‹‹እነሆ፥ ጊንጦችንና እባቦችን፥ የጠላትንም ኃይል ሁሉ ትረግጡ ዘንድ ሥልጣንን ሰጠኋችሁ፤ የሚጎዳችሁም ምንም የለም›› (ሉቃ. ፲፥፲፱) በማለት ራሳቸውን ከአደጋና ከወረርስኝ እንዳይጠብቁ፣ በሕይወታቸው ላይ ያላቸውን ድርሻ አስረስቶ ሳያውቁት እግዚአብሔርን እንዲፈታተኑ ያደርጋቸዋል፡፡ ጌታችን በዲያብሎስ በተፈተነ ጊዜ ዲያብሎስ ወደ ቅድስቲቱ ከተማ ወሰደውና በመቅደስ ጫፍ ላይ አቁሞ ‹‹ስለ አንተ መላእክቱን ያዝልሃል፤ እግርህንም በድንጋይ እንዳትሰነካከል በእጃቸው ያነሡሃል፤ ተብሎ ተጽፎአልና የእግዚአብሔር ልጅስ ከሆንህ ወደታች ራስህን ወርውር አለው፡፡ ኢየሱስም ጌታ አምላክህን አትፈታተነው ተብሎ ደግሞ ተጽፎአል አለው፡፡›› (ማቴ ፬፥፮-፰) ዲያብሎስ በእምነታችን የጸናን እንዲመስለን በማድረግ የእግዚአብሔርን ጠብቆት እንድንፈታተን ያደርገናል፡፡

ባለጸጎችን ሀብትን የሰጠ እግዚአብሔር መሆኑን፤ በተገቢውም ሥርዓት ሊያስተዳድሩ እንደሚገባና በሀብት በንብረታቸው ላይ በእግዚአብሔር የተሾሙ መሆናቸውን ያስረሳቸዋል፡፡ ለድሆች ጥቂት ነገር ሲመጸውቱ፣ ለቤተክርስቲያን ሲረዱ፣ መመስገንን አጥብቀው እንዲሹ የማይገባቸውን ክብር እንዲመኑ ያደርጋቸዋል፡፡ የሰዎችን አንደበት እየተጠቀመ ‹‹የአንተ ቤት የአብርሃም ቤት ነው፤ እስኪ ሌሎችን ባለጸጎች ተመልከት! ንፉጎች ናቸው›› እያለ ራሱን ከአብርሃም ጋር እያነጻጸረ ለራሱ ያልተገባ ክብር እንዲሰጥ እያደረገ በከንቱ ውዳሴ ይጥላቸዋል፡፡

አገልጋዮችን ‹‹አንተ ስትቀድስ፣ አንተ ስትሰብክ፣ አንተ ስትዘምር ይደምቃልና ጠጠር መጣያ ይጠፋል›› እያስባለ አገልጋዮች እያገለገሉ የሚገለገሉ መሆናቸውን ያዘናጋቸዋል፡፡ አንዳንዴ ከንቱ ውዳሴን ሳያውቁት እንዲሹ ያደርጋቸዋል፡፡

ለ/ ወቅታዊ የሀገር ሁኔታዎችን በመጠቀም

ዲያብሎስ አጥብቆ ከሚጠላው አንዱና ዋነኛው ነገር የሰውን በአንድ ልብ በአንድ ሀሳብ ሆኖ እግዚአብሔርን ማምለክ ነው፡፡ ስለዚህም ሰዎችን የሚለያዩ ልዩ ልዩ መንገዶችን ይጠቀማል፡፡ መገኛችን አባታችን አዳም መሆኑን አስዘንግቶ ሰዎች በብሔር በመከፋፈል በሰዎች መካከል ልዩነትን እንዲፈጠር አድርጎ የባላጋራነት ስሜትን ይፈጥራል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ሰዎች በሚሰሙትና በሚናገሩት ቋንቋ መገልገልና ማገልገል የተከለከለ አስመስሎ ‹‹ለምን በቋንቋዬ አይሰበክም እና አይቀደስም›› በሚሉ ሀሳቦች ነገር ግን በውስጣቸው ምእመናን ከመንጋውና ከእረኛ አባቶች የመለየት ሥውር ተልዕኮውን ይፈጽማል፡፡

ሐ/ ዓለማዊ አስተሳሰቦችን መንፈሳዊ በማስመሰል

በተለይ ዛሬ ላይ የዲያብሎስ ዋናው ማታለያው በመንፈሳዊነትና በዓለማዊነት መካከል ያለውን ድንበር በማጥፋት ለዓለማዊ አስተሳሰቦች መንፈሳዊ ሽፋን መስጠት ነው፡፡ በተደጋጋሚ የምንሰማቸው የድኅረ ዘመናዊነት፣ የባህል እና የሃይማኖት ብዝኃነት፣ የሉላዊነት እና የዓለማዊነት እይታዎች በግለሰቦች ነፃነት ስም ሃይማኖት የሰዎችን ነፃነት እንደሚገድብ አድርጎ በማቅረብና ሃይማኖተኛ መሆንን እንደጽንፈኛ አድርጎና አስመስሎ ያቀርባል፡፡ ሰዎችንም ሳያውቁት በእነዚህ አስተሳሰቦች ተጽዕኖ ከሃይማኖታቸው ወጥተው ሃይማኖት የለሽ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል፡፡

ከዲያብሎስ የማስመሰል ርህራሔው እንዴት እንጠንቀቅ?

ሀ/ ሕሊናችንን በመርመር


ጾም የሥጋ ረሀብ አይደለም የነፍስ ምግብ እንጅ

አንዳንድ ሰዎች እንደሚያስቡት ጾም የሥጋ ሥቃይ ሰማዕትነት ወይም መስቀል አይደለም፤ ሥጋ ከነፍስ ጋር የሚተባበርበት ደረጃ ላይ ለመድረስ ከፍ ከፍ የሚልበት እንጂ። ስንጾም የመጾማችን ዕቅድ ሥጋችንን ለማንገላታት አይደለም ጠባዩን_ለመግራት እንጂ። ይህ በመሆኑም አንድ የሚጾም ሰው መንፈሳዊ እንጂ ሥጋዊ ሰው አይሆንም ማለት ነው።

ጾም መናኝ ነፍስ ስለሆነ በምናኔ ውስጥ ያለ ባልጀራ ሥጋውን ይዞ ይጓዛል እንጂ ብቻውን አይጓዝም። ጾም ማለት የተራበ ሥጋ ማለት አይደለም የመነነ ሥጋ እንጂ።

ጾም የሥጋ ረሀብ አይደለም የሥጋ ልዕልና እና ንጽህና እንጂ ለመብላት የሚናፍቅ የሚራብ ሰውነት ያለበት ሁኔታ ማለትም አይደለም፤ መብላት ዋጋውን የሚያጣበትና ሰውነት ለመብላት ካለው ፍላጎት ራሱን የሚያላቅቅበት ሁኔታ እንጂ።

ጾም ነፍስ ከፍ ብላ ሥጋን ከእርስዋ ጋር ከፍ የምታደርግበት ጊዜ ነው። ይህ ጊዜ ሥጋ ጓዙንና ሸክሙን የሚያራግፍበት ጊዜ ስለሆነ እግዚአብሔር ያለ ምንም እገዳ ለመንፈሳዊ ዘላለማዊነት ደስታ የሚሠራበት ጊዜ ይሆናል።

ጾም ማለት ነፍስና ሥጋ በኀብረት መንፈሳዊ ተግባር ለማከናውን የሚጠቀሙበት ጊዜ ነው።

በጾም ወቅት ነፍስና ሥጋ የነፍስን ሥራ ለመሥራት ይተባበራሉ። ይህም ማለት ለጸሎት ለተመስጦ ለክብርና ከእግዚአብሔር ጋር የሚሆን ሕይወትን ለመጋራት ይተባበራሉ ማለት ነው።

ብፁእ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ

🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿

@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni


ኃጢአት ምን እንደሆነና ፍፃሜውንም ብታውቅ ትሸሸዋለህ!

ኃጢአት የኀሊናና የመንፈስ ሞት ነው፤ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው ‹‹የኃጢአት ደሞዝ ሞት ነው›› (ሮሜ.፮፥፲፫) ሰው በዚህች በዓለም ውስጥ ሲኖር በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ኃጢአት ይሠራል፤ በመታገስ ኃጢአትን ማሸንፍ አቅቶት ክፉት ሲሠራ ለኃጢአት ይሸነፋል፡፡ ይህም ከልጅነቱ ያርቀዋል፡፡ አዳም ከልጅነቱ ተዋርዶ ከገነት የወጣው ለኃጢአት በመሸነፉ ነበር፡፡ ‹‹ክፉን በመልካም አሸንፉ እንጂ በክፉ አታሸንፉ›› (ሮሜ.፲፪፥፳፩) ከአባቱ ቤት የወጣ ልጅ፣ ከእረኛው የተለየ በግ፣ ባለቤት የሌለው ገንዘብ ነውና ኃጢአተኖች የጠፉ ናቸው፤ ዓለማዊ ሕይወት የሚያሸንፋቸው ይጠፋሉና፤ ‹‹ማንም ዓለምን ቢወድ የአባት ፍቅር በእርሱ ውስጥ የለም››፡፡ (፩ ዮሐ. ፪፥፲፮)

ኃጢአት የሚሠራ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር መተባበር የለውምና ከፈጣሪው ይርቃል፤ ለዚህም ነው ኃጢአትም ከእግዚብሔር መለየት ነው የተባለው፤ ‹‹ብርሃን ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው?፤ ክርስቶስ ከቤልሆር ጋር ምን መስማማት አለው? ወይስ የሚያምን ከማያምን ጋር ምን ክፍል አለው?›› ( ፪ ቆሮ. ፮፥፲፬-፲፭)

ኃጢአት እግዚብሔርን ማጣትም ነው፤ በኃጢአት የሚኖር ሰው ራሱንና ልቡናውን ከእግዚአብሔር በመለየቱ እግዚአብሔርን ያጣል፤ ‹‹የሚወደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል››፤ (ዮሐ.፲፬፥፳፫) ፈጣሪን የማያምን ግን ኃጢአትን አብዝቶ ይሠራል፤ መጥፎ ሥራዎችን የሚሠራ ሰው መንፈስ ቅዱስ ይርቀዋል፤ የመንፈስ ቅዱስንም ሥራ ይቃወማል፡፡ ‹‹ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ›› (ኤፌ.፬፥፴) መንፈስ ቅዱስ በሰው ልቡና ውስጥ ሥራውን ካልሠራ ሰው ንስሓ ሊገባ አይችልም፤ ሰው በኃጢአቱ እንደተጸጸተና ንስሓ እንዲገባ የሚያበረታው መንፈስ ቅዱስ ነውና፡፡ ኃጢአተኛ ሰው የሕይወትን ትርጉም አያውቅም፤ ስለንስሓ ቢነገረው ‹በሕይወቴ እንድደሰት ተውኝ› ይላል፤ ምድራዊና ዓለማዊ ደስታ ሕይወት እንደሆነ ያስባልና፡፡

በኃጢአት ውስጥ የኖረ ሰው ውስጣዊ ሰላም የለውም፤ ‹‹ለክፎዎች ሰላም የላቸውም ይላል እግዚአብሔር›› (ኢሳ. ፵፰፥፳፪) ልቡናውም በጭንቀት ስለሚሞላ ፈሪ ይሆናል፡፡ መጥፎ ባሕርይን ይወርሳል፡፡ አዳም ኃጢአትን በሠራ ጊዜ ከዚያ በፊት ያልነበሩ ሦስት ነገሮችን ገንዘብ አደረገ፤ ፍርሀት፣ ድንጋጤና ሰላም ማጣት፤ ፍርሀት የሥነ ልቡና ሕመምተኛ ያደርጋል፤ ኃጢአት ሕሊናን ያደክማል፡፡ ጻድቃን ግን በሰላም፣ በፍቅርና በድስታ ይኖራሉ፡፡ የመንፈስ ፍሬ ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም፣ ትዕግሥት፣ ቸርነት፣ በጎነት፣ እምነት፣ የውሃት፣ ራስን መግዛት ነውና፤(ገላ. ፭፥፳፪-፳፫)

በዚህ ምድር ስንኖር ሕገ እግዚአብሔርን በመተላለፍ የተነሳ መርገሞች የሚያስከትሉአቸው ቅጣቶች ብዙ ናቸው፡፡ ‹‹የዚህን ሕግ ቃሎች ያደርግ ዘንድ የማያጸና ርጉም ይሁን…››(ዘዳ. ፳፰፥፳፮) ሰው ንስሓ ሳይገባ ለድንገተኛ ሞት ሊዳረግ ይችላል፤ በበሽታ ይቀጣል፤ ረኃብ፣ ቸነፈርና ድኅነት ይበዛበታል፤ በደልም ይደርስበታል፡፡

ሰው ንስሓ ከገባ ከዘለዓለማዊ ቅጣት ይድናል፡፡ ነገር ግን በእግዚአብሔር የተወሰነበትን ምድራዊ ቅጣት መቀበል ይኖርበታል፡፡ ያም የሚወሰነው ከሚሠራው የኃጢአት ዓይነት ነው፡፡ በእርግጥ የኃጢአት ትንሽና ትልቅ የለውም፤ ሆኖም ሰው ዐሥርቱ ትእዛዛትን በተላለፈበት መጠን ይቀጣል፡፡ ከእግዚአብሔር ቁጣ የተነሳ የሚመጣ ቅጣትና በፍትሐ ብሔር ወይም በቤተ ክርስቲያን የሚመጣ ቅጣት ሊቀበል ይቻላል፡፡ ይህም ለተወሰነ ጊዜ ከቅዱስ ቁርባን መከልከና ቤተክርስቲያን እንዳይገባ መከልከል ሊሆን ይችላል፡፡

ኃጢአትን አብዝቶ መሥራት በእግዚአብሔር አርአያና ምሳሌ መሆንን ያስቀራል፤ የኅሊና ነጻነትንና የልቡና ንጽሕናንም ያሳጣል፡፡ ‹‹እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ›› (ዘሌ.፲፩፥፵፬) ኃጢአትን የማይተው፣ እስከዕለተ ሞቱም ንስሓ የማይገባ ሰው ግን የዘላለም ቅጣት ይፈረድበታል፡፡ እግዚአብሔር መሓሪና ምሕረቱም የበዛ እንደሆነ ሁሉ ፍርዱም እውነትና ፍጹም መሆኑን፣ በደልን ይቅር የሚል፣ ኃጢአትንም የማይወድ መሆኑን ማወቅ ይገባል፡፡ ከእግዚአብሔር ቸርነትና ምሕረት አንጻር ፍርዱንና ቅጣቱንም አስቦና ተረድቶ ወደ ንስሓ መመለስ ያስፈልጋል፡፡ ቸርነቱን በመተማመን ጭከናውን መርሳት፣ ምሕረቱንም ተስፋ በማድረግ ፍርዱንም ደግሞ መዘንጋት አይገባም፡፡ ‹‹እንግዲህ የእግዚአብሔርን ቸርነትና ጭከና ተመልከት፤ጭከናውም በውድቀቱ ላይ ነው፤ በቸርነቱ ግን ጸንተህ ብትኖር የእግዚአብሔር ቸርነት በአንተ ላይ ነው፤ ያለዚያ አንተ ደግሞ ትቆረጣለህ›› (ሮሜ. ፲፩፥፳፪)

እግዚአብሔር እውነተኛ ፈራጅ ነው፤ ፍርዱም በትክክል ነው፤ ንስሓ ገብተን ከፊቱ ብንቆም የእግዚአብሔርን ቸርነት እናያለን፡፡ በግድ የለሽነት የምንኖር ንስሓ የማንገባ ሆነን በፊቱ ብንቆም ደግሞ በጭካኔውና በፈራጅነቱ እግዚአብሔርን እናየዋለን፡፡

የዓለም ፍጻሜ የፍርድ ቀን አስደንጋጭና አስፈሪ ነው፤ ‹‹እነሆ ምድሪቱን ባድማ ሊያደርግ፣ ኃጢአተኞቿንም ከእርሷ ዘንድ ሊያጠፋ ጨካኝ ሆኖ በመዓትና በጽኑ ቁጣ ተሞልቶ የእግዚአብሔር ቀን ይመጣል›› (ኢሳ. ፲፫፥፱) በዚያም ቀን እግዚአብሔር ብቻ ከፍ ከፍ ይላል፡፡ ጣኦቶቻቸውም ሁሉ ፈጽመው ይጠፋሉ፡፡ እግዚአብሔርም ምድርን ያናውጥ ዘንድ በተነሣ ጊዜ ሰዎችን ከማስደንገጡና ከግርማው ክብር የተነሣ ወደ ድንጋይ ዋሻና ወደ ምድር ንቃት ውስጥ ይገባሉ፡፡ (ኢሳ.፪፥፲፯-፳) ፭ኛው የግብፅ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሽኖዳም እንዳሉትም ‹‹ኃጢአት ምን እንደሆነና ፍፃውንም ብታውቅ ትሸሸዋለህ››፡፡ ጻድቃን መንግሥተ ሰማያትን ሲወርሱ ኃጥኣን ግን ዘለዓለማዊ ቅጣት ወዳለበት ገሀነመ እሳት ውስጥ ይጣላሉ፡፡ ‹‹እነዚያም ወደ ዘለዓለም ቅጣት፣ ጻድቃን ግን ወደ ዘለዓለም ሕይወት ይሄዳሉ›› (ማቴ.፳፭፥፵፮)

በዚያች በፍርድ ቀን ለቅሶ፤ ዋይታና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል፤ ሆኖም ሁሉም የማይጠቅም ጩኸት ነው፡፡ ጨለማውና የማይጠፋው እሳት እጅግ ከባድና አስፈሪ ነው፡፡ ከባድነቱንም ለመረዳት የሚቻለው ግን የጻድቃንን ሕይወት በማየት፣ በመረዳትና በማወቅ ነው፡፡

ምንጭ፤ የንስሓ ሕይወት መጽሐፍ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ የግብፅ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ፤ ውርስ ትርጉም ቀሲስ እሸቱ ታደሰ ወንድምአገኘሁ በ፳፻፱ ዓ.ም.

ብፁእ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ

🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿

@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni


ኃጢአት የሚሠራ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር መተባበር የለውምና ከፈጣሪው ይርቃል፤ ለዚህም ነው ኃጢአትም ከእግዚብሔር መለየት ነው የተባለው፤ ‹‹ብርሃን ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው?፤ ክርስቶስ ከቤልሆር ጋር ምን መስማማት አለው? ወይስ የሚያምን ከማያምን ጋር ምን ክፍል አለው?›› ( ፪ ቆሮ. ፮፥፲፬-፲፭)

ኃጢአት እግዚብሔርን ማጣትም ነው፤ በኃጢአት የሚኖር ሰው ራሱንና ልቡናውን ከእግዚአብሔር በመለየቱ እግዚአብሔርን ያጣል፤ ‹‹የሚወደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል››፤ (ዮሐ.፲፬፥፳፫) ፈጣሪን የማያምን ግን ኃጢአትን አብዝቶ ይሠራል፤ መጥፎ ሥራዎችን የሚሠራ ሰው መንፈስ ቅዱስ ይርቀዋል፤ የመንፈስ ቅዱስንም ሥራ ይቃወማል፡፡ ‹‹ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ›› (ኤፌ.፬፥፴) መንፈስ ቅዱስ በሰው ልቡና ውስጥ ሥራውን ካልሠራ ሰው ንስሓ ሊገባ አይችልም፤ ሰው በኃጢአቱ እንደተጸጸተና ንስሓ እንዲገባ የሚያበረታው መንፈስ ቅዱስ ነውና፡፡ ኃጢአተኛ ሰው የሕይወትን ትርጉም አያውቅም፤ ስለንስሓ ቢነገረው ‹በሕይወቴ እንድደሰት ተውኝ› ይላል፤ ምድራዊና ዓለማዊ ደስታ ሕይወት እንደሆነ ያስባልና፡፡

በኃጢአት ውስጥ የኖረ ሰው ውስጣዊ ሰላም የለውም፤ ‹‹ለክፎዎች ሰላም የላቸውም ይላል እግዚአብሔር›› (ኢሳ. ፵፰፥፳፪) ልቡናውም በጭንቀት ስለሚሞላ ፈሪ ይሆናል፡፡ መጥፎ ባሕርይን ይወርሳል፡፡ አዳም ኃጢአትን በሠራ ጊዜ ከዚያ በፊት ያልነበሩ ሦስት ነገሮችን ገንዘብ አደረገ፤ ፍርሀት፣ ድንጋጤና ሰላም ማጣት፤ ፍርሀት የሥነ ልቡና ሕመምተኛ ያደርጋል፤ ኃጢአት ሕሊናን ያደክማል፡፡ ጻድቃን ግን በሰላም፣ በፍቅርና በድስታ ይኖራሉ፡፡ የመንፈስ ፍሬ ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም፣ ትዕግሥት፣ ቸርነት፣ በጎነት፣ እምነት፣ የውሃት፣ ራስን መግዛት ነውና፤(ገላ. ፭፥፳፪-፳፫)

በዚህ ምድር ስንኖር ሕገ እግዚአብሔርን በመተላለፍ የተነሳ መርገሞች የሚያስከትሉአቸው ቅጣቶች ብዙ ናቸው፡፡ ‹‹የዚህን ሕግ ቃሎች ያደርግ ዘንድ የማያጸና ርጉም ይሁን…››(ዘዳ. ፳፰፥፳፮) ሰው ንስሓ ሳይገባ ለድንገተኛ ሞት ሊዳረግ ይችላል፤ በበሽታ ይቀጣል፤ ረኃብ፣ ቸነፈርና ድኅነት ይበዛበታል፤ በደልም ይደርስበታል፡፡

ሰው ንስሓ ከገባ ከዘለዓለማዊ ቅጣት ይድናል፡፡ ነገር ግን በእግዚአብሔር የተወሰነበትን ምድራዊ ቅጣት መቀበል ይኖርበታል፡፡ ያም የሚወሰነው ከሚሠራው የኃጢአት ዓይነት ነው፡፡ በእርግጥ የኃጢአት ትንሽና ትልቅ የለውም፤ ሆኖም ሰው ዐሥርቱ ትእዛዛትን በተላለፈበት መጠን ይቀጣል፡፡ ከእግዚአብሔር ቁጣ የተነሳ የሚመጣ ቅጣትና በፍትሐ ብሔር ወይም በቤተ ክርስቲያን የሚመጣ ቅጣት ሊቀበል ይቻላል፡፡ ይህም ለተወሰነ ጊዜ ከቅዱስ ቁርባን መከልከና ቤተክርስቲያን እንዳይገባ መከልከል ሊሆን ይችላል፡፡

ኃጢአትን አብዝቶ መሥራት በእግዚአብሔር አርአያና ምሳሌ መሆንን ያስቀራል፤ የኅሊና ነጻነትንና የልቡና ንጽሕናንም ያሳጣል፡፡ ‹‹እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ›› (ዘሌ.፲፩፥፵፬) ኃጢአትን የማይተው፣ እስከዕለተ ሞቱም ንስሓ የማይገባ ሰው ግን የዘላለም ቅጣት ይፈረድበታል፡፡ እግዚአብሔር መሓሪና ምሕረቱም የበዛ እንደሆነ ሁሉ ፍርዱም እውነትና ፍጹም መሆኑን፣ በደልን ይቅር የሚል፣ ኃጢአትንም የማይወድ መሆኑን ማወቅ ይገባል፡፡ ከእግዚአብሔር ቸርነትና ምሕረት አንጻር ፍርዱንና ቅጣቱንም አስቦና ተረድቶ ወደ ንስሓ መመለስ ያስፈልጋል፡፡ ቸርነቱን በመተማመን ጭከናውን መርሳት፣ ምሕረቱንም ተስፋ በማድረግ ፍርዱንም ደግሞ መዘንጋት አይገባም፡፡ ‹‹እንግዲህ የእግዚአብሔርን ቸርነትና ጭከና ተመልከት፤ጭከናውም በውድቀቱ ላይ ነው፤ በቸርነቱ ግን ጸንተህ ብትኖር የእግዚአብሔር ቸርነት በአንተ ላይ ነው፤ ያለዚያ አንተ ደግሞ ትቆረጣለህ›› (ሮሜ. ፲፩፥፳፪)

እግዚአብሔር እውነተኛ ፈራጅ ነው፤ ፍርዱም በትክክል ነው፤ ንስሓ ገብተን ከፊቱ ብንቆም የእግዚአብሔርን ቸርነት እናያለን፡፡ በግድ የለሽነት የምንኖር ንስሓ የማንገባ ሆነን በፊቱ ብንቆም ደግሞ በጭካኔውና በፈራጅነቱ እግዚአብሔርን እናየዋለን፡፡

የዓለም ፍጻሜ የፍርድ ቀን አስደንጋጭና አስፈሪ ነው፤ ‹‹እነሆ ምድሪቱን ባድማ ሊያደርግ፣ ኃጢአተኞቿንም ከእርሷ ዘንድ ሊያጠፋ ጨካኝ ሆኖ በመዓትና በጽኑ ቁጣ ተሞልቶ የእግዚአብሔር ቀን ይመጣል›› (ኢሳ. ፲፫፥፱) በዚያም ቀን እግዚአብሔር ብቻ ከፍ ከፍ ይላል፡፡ ጣኦቶቻቸውም ሁሉ ፈጽመው ይጠፋሉ፡፡ እግዚአብሔርም ምድርን ያናውጥ ዘንድ በተነሣ ጊዜ ሰዎችን ከማስደንገጡና ከግርማው ክብር የተነሣ ወደ ድንጋይ ዋሻና ወደ ምድር ንቃት ውስጥ ይገባሉ፡፡ (ኢሳ.፪፥፲፯-፳) ፭ኛው የግብፅ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሽኖዳም እንዳሉትም ‹‹ኃጢአት ምን እንደሆነና ፍፃውንም ብታውቅ ትሸሸዋለህ››፡፡ ጻድቃን መንግሥተ ሰማያትን ሲወርሱ ኃጥኣን ግን ዘለዓለማዊ ቅጣት ወዳለበት ገሀነመ እሳት ውስጥ ይጣላሉ፡፡ ‹‹እነዚያም ወደ ዘለዓለም ቅጣት፣ ጻድቃን ግን ወደ ዘለዓለም ሕይወት ይሄዳሉ›› (ማቴ.፳፭፥፵፮)

በዚያች በፍርድ ቀን ለቅሶ፤ ዋይታና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል፤ ሆኖም ሁሉም የማይጠቅም ጩኸት ነው፡፡ ጨለማውና የማይጠፋው እሳት እጅግ ከባድና አስፈሪ ነው፡፡ ከባድነቱንም ለመረዳት የሚቻለው ግን የጻድቃንን ሕይወት በማየት፣ በመረዳትና በማወቅ ነው፡፡

ምንጭ፤ የንስሓ ሕይወት መጽሐፍ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ የግብፅ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ፤ ውርስ ትርጉም ቀሲስ እሸቱ ታደሰ ወንድምአገኘሁ በ፳፻፱ ዓ.ም.

20 last posts shown.