Forward from: Samuel Adane
እኛነታችንን በደንብ አናውቀውም፡ ግን እኛ እኔ በሚል አጥር ውስጥ ተተብትበናል።
መኖር እንመኛለን ግን የሌላው አለመኖር አያሳስበንም፡ መራብ አንፈልግም የሌሎች እርሀብ ግን አያመንም፡ ሰላም እንፈልጋለን ግን የሌሎች ሰላም እናናጋለን፡ መደሰት እንወዳለን ግን ሌሎች እንዲያለቅሱ ምክኒያቶች ነን።
በእውነት ምኑም ነገር አልገባንም፡ ብኩኖች ብቻ ነን ፡ ሸክላነታችን ያልገባን ፡ ነገን ለመኖር ዋስትና የሌለን ከንቱዎች፡ አፈርን ካፈር ለመለየት የምንዳክር ቂሎች ፡
ስጋችን የተለቀ ፣አስተሳሰባችን ያልታረቀ ፣ አካሄዳችን እና ምግባራችን የተናቀ ምስቅልቅሎች፡ ምኑም ነገር አልገባንም።
ለክብርና ለዝና ፡ ለሀብትና አድሮ አመድ ለሚሆን ስጋችን ባሪያዎች የሆንን፤ የምንፈልገው አይገባንም ፡ የሚያስፈልገን አይታየንም፡ የውስጣችንን ባዶነት በጩህትና ባለባበስ ለመሸፈን የምንዋትት አሳዛኞች፡ ከፈጣሪ ትዛዝ ይልቅ የፍላጎታችን ባሪያወች ፡ ከፍርቅር ይልቅ የጥላቻ ፈረሶች ፡ የሰውነት ክብራችንን ያጣን፣ ጥጋብ ምንሆነውን ያሳጣን ፣ ከቁጣው መቅሰፍት ያልወጣን
ጅሎች ሆነናል ፡፡ የምንናገረውን አናቅም፡ የምናምነውን እሱን አንሰማውም፡ የቃል ሰዎች ብቻ ነን።
ሀጢታችን በፊታችን የተገለጠ ነው፡ ግን ክብራችን ይመስለናል ፡፡ እምናደርገውን አናስተውልም ፣ እየሆነ ያለው ሁሉ አይገባንም፡፡ የፈጣሪ እዳ አለብን ፡ እጃችን ባዶ ነው ፡ ለዛውም የተጨማለቀ ። አልገባንም ሀጢያታችን በዝቷል ፡ ውጤቱንም እያየነው ነው ፡፡
ከሩጫችን ረጋ እንበል፣እናስተውል ፣እንመለስ፣ ሰው እንሁን ፣ አስተሳሰባችንን ከሰውነት ሚዛን አናስወጣው ፡፡ አልረፈደም እንፀልይ ፡ የፈጠረን አምላክ ለይቅርታ የታመነ ነው።
ሰላም፣ ፍቅር፣ ጤንነት ፡ለሰው ልጆች ሁሉ ይሁን !
Samuel Adane
@sam2127
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን
የምንም ግዜ ተወዳጅ የሆነው
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
አዘጋጅ፦ @Daniel_bewketu
@Daniel_bewketu
➟➟➟➟➟➛➟➟➟➟➟