በሰሜን ወሎ ሲኖትራክ ላይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት በርካቶች መገደላቸውን የዓይን እማኞች እና የተጎጂ ቤተሰቦች ተናገሩ
በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ባለፈው ሳምንት 'ሲኖ ትራክ' በተባለ የጭነት ተሽከርካሪ ላይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት 50 የሚሆኑ ሰዎች እንደተገደሉ የዓይን እማኞች እና የተጎጂ ቤተሰቦች ለቢቢሲ ተናገሩ።
ጥቃቱ የደረሰው ዞኑ ዳውንት ወረዳ ውስጥ ባለፈው ሐሙስ ኅዳር 19/2017 ዓ.ም. ቀትር 8፡00 አካባቢ መሆኑን የተናገሩት የአካባቢው ነዋሪዎች የጥቃቱ ሰለባዎች ከተለያዩ ጉዳዮች ወደ ኩርባ ከተማ ሲመለሱ የነበሩ ሰዎች ናቸው ብለዋል።
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ስለ ጥቃቱ ጥቆማ እንደደረሰው እና መረጃ እያሰባሰበ እንደሆነ ለቢቢሲ ተናግሯል።
ሐሙሲት የተባለ ገበያ ከሚውልበት ሾጋ አካባቢ ወጣ ብሎ ልዩ ስሙ ሰጎራ በተባለ አካባቢ ጥቃቱ መድረሱንም የዓይን እማኞች ተናግረዋል።
በአካባቢው ባለው የትራንስፖርት ችግር ምክንያት በጭነት ተሽከርካሪዎች መጓዝ የተለመደ መሆኑን የተናገሩት ነዋሪዎች፤ ያለፈው ሳምንት ጥቃት አሸዋ እና ሰዎችን በጫነ 'ሲኖ ትራክ' በተባለው ተሽከርካሪ ላይ መድረሱን ተናግረዋል።
ገበያ ውለው ሲመለሱ የነበሩ ገበያተኞች፣ አርሶ አደሮች፣ ለሥራ ፍላጋ ከአጎራባች ዋድላ ወረዳ ሲመለሱ የነበሩ ወጣቶች እንዲሁም ከደላንታ ወረዳ ክርስትና ደርሰው ሲመለሱ የነበሩ ሰዎች የጥቃቱ ሰለባዎች እንደሆኑ ተናግረዋል።
በጥቃቱ ቀን ሁለት ድሮኖች ለሰዓታት "ቅኝት ሲያደርጉ ነበር" ያሉ በንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩ አንድ የዓይን እማኝ፤ "መብረቅ" የሚመስል ድምጽ ሰምተው ወደ አካባቢው ማቅናታቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ተሽከርካሪው ዳገት ሲወጣ መመታቱን የተናገሩ ሌላ የዓይን እማኝም "ከባድ እና አስፈሪ ድምጽ" መስማታቸውን እና ከተወሰነ ጊዜ በኋላ አካባቢው ላይ መድረሳቸውን ተናግረዋል።
የሰለባዎቹ አካላት በጥቃቱ "ተቆራርጦ" እና ከባድ ጉዳት ደርሶ በመመልከታቸው አዕምሯቸው መረበሹን የጠቀሱ ሌላ እማኝ፤ "እንዲህ ነው ተብሎ በቃላት የሚገለጽ አይደለም" ብለዋል።
የድሮን ቅኝት በመቀጠሉ ተጨማሪ ጥቃት በመፍራት ዛፍ አካባቢ ተጠልለው አመሻሽ አካባቢ አስከሬን ለማንሳት መገደደዳቸውን የተናገሩ እማኙ፤ "ሰው ሆኖ መፈጠርን የጠላሁበት" ሲሉ ያዩትን ሁነት ገልጸዋል።
ሌላ እማኝ ደግሞ አስከሬን መኪናው ውስጥ እና ውጭ ወዳድቆ ማየታቸውን ጠቁመው "በጣም ያሳዝናል። . . . የሰው ልጅ ሆኖ አለመፈጠር ነው" በማለት ስለተለመከቱት ክስተት ያደረባቸውን ስሜት ተናግረዋል።
"ጨለማን ተገን አድርጎ ነው አስከሬን የተነሳው" ያሉ የመንግሥት ሠራተኛ የሆኑት የዓይን እማኝ፤ አስከሬን ለማንሳት እና ለመለየት ከባድ እንደነበር ተናግረዋል።
እስከ ሌሊት 9፡00 ድረስ አስከሬን መነሳቱን እና "ኤፍኤስአር" በተባለ ተሽከርካሪ ተጭኖ ወደ ጤና ጣቢያ መወሰዱን የተናገሩት ሌላ የዓይን እማኝ፤ አስከሬን በልብስ፣ በጫማ እና በልዩ ምልክቶች መለየቱን ገልጸዋል።
"ከ50 በላይ አስከሬን ቆጥሪያለሁ" ያሉት እማኙ ሹፌሩን ጨምሮ 10 የሚሆኑ ጋቢና እና 'ፖርቶመጋላ' አካባቢ የነበሩ ሰዎች መቁሰላቸውን ተናግረዋል።
በጥቃቱ የተገደሉት ሰዎች ቁጥር 50 እንደሚሆን የተናገሩ ሌላ የዓይን እማኝም፤ ስምንት የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ ቆስለው ለህክምና ጤና ጣቢያ ተወስደዋል ብለዋል።
"ማኅበረሰቡ ሙሉ መጥቶ፤ እናት ልጇን እየፈለገች፤ አባት ልጁን እየፈለገ፤ እነደዚህ ዓይነት ልብስ ነው ለብሶ የወጣው፤ እንዲህ ዓይነት ናቸው፤ አካላቸው ላይ እንዲህ ዓይነት ምልክት አላቸው እየተባለ በሽርፍራፊ ነገር ነው አስከሬን ከቤተሰብ ጋር መገናኘት የቻለው" ብለዋል።
የ21 ዓመት ያሳደጉት የወንድማቸው ልጅ ከተገደሉት ውስጥ እንደሚገኝ የተናገሩ አንድ የአካባቢው ነዋሪ፤ ምንም እንኳ 12፡00 አካባቢ ጥቃቱ የደረሰበት ስፍራ ቢገኙም ጤና ጣቢያ ውስጥ አስከሬን ሲለይ በጥቃቱ መገደሉን እንደተረዱ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ከዩኒቨርስቲ ተመርቆ ሥራ ለመፈለግ ሐሙሲት ደርሶ ሲመለስ እንደተገደለ የተናገሩት የሟች ቤተሰብ መታወቂያው ተቃጥሎ በትምህርት ማስረጃዎች እንደተለየም ተናግረዋል።
"ልጅ፣ ወንድም ያልሞተበት ሰው የለም። . . . ሙሉ ወረዳዋ ሐዘን ላይ ነበረች" ሲሉ ሐዘኑ ሁሉም ቤት ስለመግባቱ ደግሞ ሌላ ነዋሪ ገልጸዋል።
ከሟቾቹ ውስጥ አራቱ ቤተሰቦቻቸው እንደሆኑ የተናገሩ አንድ የዓይን እማኝ፤ በምህንድስና ትምህርት ተመርቆ ሥራ ለመፈለግ የወጣ የአጎታቸውን ልጅ ጨምሮ በአነስተኛ የንግድ ሥራ ተሰማሩ እና የቤተሰብ አስተዳዳሪ ዘመዶቻቸው መገደላቸውን ተናግረዋል።
እስከ አራት ቀናት ድረስ የቀብር ሥነ ሥርዓት ሲፈጸም እንደነበር የገለጹት እማኙ "ከ14፤ 15 ቀበሌዎች የቀረ የለም" ሲሉም በሁሉም የወረዳዋ ቀበሌዎች ቀብር እንደነበር ጠቁመዋል።
አስከሬን ያነሱ በ20ዎቹ የእድሜ ክልል የሚገኙ ወጣቶችም በተመለከቱት ነገር ተረብሸው "ወደ ራሳቸው" መመለስ አልቻሉም ሲሉ የሥነ ልቦና እክል እንደገጠማቸው የተናገሩ አንድ ነዋሪ፤ ፀበልን ጨምሮ ወደ ተለያዩ ቦታዎች መወሰዳቸውን ገልጸዋል።
ጥቃቱ በደረሰበት አካባቢ በፋኖ እና በመንግሥት ኃይሎች መካከል ውጊያ እንዳልነበር የተገሩት ነዋሪዎች፤ የጥቃቱ ሰለባዎችም ንጹሃን እንጂ የፋኖ ታጣቂዎች አልነበሩም ብለዋል።
ሆኖም ወረዳው ከመስከረም ወር ወዲህ በፋኖ ኃይሎች ቁጥጥር ስር እንደሚገኝ ነዋሪው አስረድተዋል።
ከጥቃቱ በኋላ በአካባቢው ነዋሪዎች ዘንድ በተፈጠረው ስጋት ምክንያት በገበያ ቦታ ጭምር አለመረጋጋት እንደነበረ ነዋሪዎች አመልክተዋል።
"ማኅበረሰቡ ከፍተኛ ስጋት ላይ ነው ያለው። ባለፈው ቅዳሜ ገበያ ላይ ይጥላል ተብሎ ከፍተኛ ግርግር ነበር። ሻይ ቤት መቀመጥ፤ በቡድን ሆኖ መቀመጥ በራሱ በጣም ከፍተኛ ፍርሃት ነው ያለው" ሲሉ ሌላ ነዋሪ ያለውን ሁኔታ ገልጸዋል።
ለቅሶ ለመድረስም ሆነ ለመጠያየቅ ማኅበረሰቡ ስጋት ውስጥ መሆኑንም እና ዘመዶቻቸው እንኳ ለቅሶ ለመድረስ መቸገራቸውን የሟች ቤተሰብ ተናግረዋል።
"በጣም አስቸጋሪ ሁኔታ ነው። እስካሁን ያለው ሁኔታ ሰው ገበያውን የሚገበይበት አይደለም። ወደ ቤተ ክርስቲያንም ማለዳ ተነስቶ ስሞ ዘወር ማለት ካልሆነ በስተቀር የሚያወጋበት፤ የሚመክርበት ነገር የለም" ብለዋል።
ከዳውንቱ ጥቃት በኋላ በዞኑ ላስታ ወረዳ ብልብላ በተባለ አካባቢ ኅዳር 24/2017 ዓ.ም. በተፈጸመ የድሮን ጥቃት የ83 ዓመት እናት መገደላቸውን እና ሰዎች መቁሰላቸውን መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
ቢቢሲ ስለ ጥቃቶቹ ከሰሜን ወሎ ዞን አስተዳደር መረጃ ለማግኘት ያደረገው ጥረት አልተሳከም።
አንድ ዓመት ያለፈውን በአማራ ክልል በመንግሥት ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ከሚካሄደው ውጊያ ጋር ተያይዞ በሚፈጸም የድሮን ጥቃት በተለያዩ ቦታዎች በሰዎች እና በተቋማት ላይ ጉዳት መድረሱን ቢቢሲ ከዚህ በፊት መዘገቡ ይታወሳል።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ስለድሮን ጥቃቶቹ እስካሁን በይፋ የሰጠው መልስ የለም። መረጃው የቢቢሲ አማርኛ ነው!!
https://t.me/Tamrinmedia