በጉጂ ዞን በመሬት መደርመስ የ8 ሰዎች ሕይወት አለፈ
በጎጂ ዞን ሳባ ቦሩ ወረዳ በባሕዊ መንገድ ማዕድን እያወጡ በነበረው ሰዎች ላይ በደረሰው የመሬት መደርመስ የስምንት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የዞኑ ኮሚኒኬሽን ገልጸዋል፡፡ የዞኑ ኮሙኒኬሽን ኃላፊ አቶ አሸናፊ ዳንቆ ለዲዳቢሊው እንደገለጹት በትናትናው ዕለት 9፡00 ገደማ አደጋው መድረሱን ገልጸው በቦታው በባሕላዊ መንገድ ሲያወጡ የነበሩ ሕይወታቸው ያለፈው 8ቱ ሰዎች አስከረን ዛሬ መውጣቱን አመልክተዋል፡፡
‹«ቦታው ጉጂ ዞን ሳባ ቦሩ ወረዳ ቃቲቻ የሚባል ቀበሌ ውስጥ ነው፡፡ በትናንትናው ዕለት ከ9፡00 በኋላ ነው ድርጊቱ የተፈጠረው፡፡ በባሕላዊ መንገድ ማዕድን በማውጣት እየሠሩ የነበሩ ሰዎች ላይ አፈር ተንሸራርቶ የስምንት ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡ ሕይወታቸውን ለማሻሻል በባሕላዊ መንገድ የሚሠሩ ሰዎች ናቸው መሬት ተንሸራርቶ ነው ሕይወታቸው ያለፈው አስከረናቸው ወጥቷል›› ብለዋል ።
ሳባ ቦሩ ወረዳ ከጉጂ ዞን አስተዳደር መቀመጫ ከሆነችሁ አዶላ ከተማ 70 ኪ.ሜ ገደማ ላይ የሚትገኝ ወረዳ ናት፡፡