የትም: መቼም በማንም ለሚፈጸም ኢሰብዓዊና ጭካኔ የተመላበት ተግባር: ምንም ዓይነት ትዕግስት ሊኖረን አይገባም!
==================
ሰሞኑን በማህበራዊ ድረ-ገጽ እየተዘዋወረ ያለው አሰቃቂ የግድያ ተግባር ሊወገዝ ይገባዋል::
ማንም ይፈጽመው: በየትኛውም ሰው ላይ ይፈጸም: የትም ይፈጸም: አረመኔያዊና ኢሰብዓዊ በመሆኑ በፅኑ ሊኮነን ይገባዋል::
መንግሥት ተብዬው #የአብይአህመድ ቡድንም እንደ ተለመደው ለእራሱ የፖለቲካ ፍጆታ ለማዋል መሽቀዳደሙን ትቶ: አስፈላጊውን ክትትልና ምርመራ በማድረግ ፈፃሚዎቹን ለፍርድ ማቅረብ አለበት:: ግዴታው ነውና::
ይሄንን አሰቃቂ የግድያ ተግባር (ሰውን የማረድ ተግባር) በመቃወም ሰበብ ግን ሕዝብን በሕዝብ ላይ ሚያነሳሳ ፕሮፓጋንዳ መታቀብ ያስፈልጋል:: ብልጥግናም በደጋፊዎቹና በካድሬዎቹ በኩል የሚያደርገውን የ"እንበቀል" (ወይም "የጉማ እናውጣ") ጥሪ በአስቸኳይ ማስቆም አለበት::
እንዲህ ዓይነት ኃላፊነት የጎደለው ጥሪ ማድረግ: ከተፈጸመው አሰቃቂ ድርጊት የማይሻል: ምናልባትም የባሰ: ሕገ-ወጥነት: ተመሳሳይ ኣረመኔነት: ተመሳሳይ ኢሰብዓዊነት ነውና በእኩል ደረጃ ሊኮነን የሚገባው ነገር ነው::
ከዚህ በፊት: በተደጋጋሚ እንዲህ ዓይነት ኣረመኔያዊ ተግባር ሲፈጸም: በአብዛኛው የማሕበረሰብ ክፍል በዝምታ እየታለፈ: ክፋትን የመለማመድና የመታገስ ሁኔታ እየተስፋፋ ቢሆንም: አሁን ግን: ማንኛውም ግለሰብ ወይም ቡድን: ይሄን ዓይነት ተግባር ሊቃወም: ሊፀየፍ: ሊያወግዝ: ሊኮንን ይገባል:: አልፎም: ሥርዓትና ሕግ: ፍትሕና ሰብዓዊነት በተመላበት አግባብ ሊታገለው ይገባል:: (በተለያዩ ቦታዎች ይሄን ዓይነት ተቃውሞ በሰላማዊ ሰልፍ የገለፁ ተማሪዎችን በወታደራዊ ኃይል ማጥቃትም ሊቅምና ሊኮነን ይገባዋል::)
መቼም #አብይኣህመድ እና ቡድኑ: ጉዳዩን እንደ መንግሥት: በገለልተኛነት መርምሮ: ጥፋተኞችን ለፍርድ በማቅረብ: ለተበዳዮች ፍትሕን: ለኣጥፊዎች ቅጣትን ይበይናል: ያስፈፅማል የሚል ተስፋ ኢምንት ነው:: ይልቁንም የድርጊቱን ዓይነት ፍጅት አስፋፍቶ በመፈፀም: እነ "እከሌ ይሄን ፈፀሙ" እያለ ፕሮፓጋንዳ በመንዛት ሕዝብን የማጋጨት የዘወትር ተግባሩን እንደሚቀጥል ይጠበቃል:: ነገር ግን አጥፊዎችን በአግባቡ ለይቶ በፍርድ ሂደት ተጠያቂ እስካላስደረገ ድረስ: የወንጀሉ ሃላፊነት: መንግሥት ነኝ ከሚለው የብልጥግና ስብስብ እራስ አይወርድም::
በመሆኑም: ማንም ሰው የሚያስተላልፈው የበቀል እርምጃ ጥሪም ሆነ የካድሬዎች "የጉማ እናውጣ" ጥሪ : በፍጥነት መቆም አለበት:: ሁሉም ዜጋ ይሄን ዓይነት ጥሪ የሚያስተላልፉ የደም ነጋዴዎችን ለማስቆም ጥረት ማድረግ አለበት::
ይሄን ዓይነት: ከጉዳዩ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸውን ምስኪን ሰላማዊ ግለሰቦች ለሕገ-ወጥና ላልተገባ ጥቃት የሚያጋልጥ ተግባር: በሁሉም መወገዝ: መኮነን: አለበት:: ወንጀል ስለሆነም በሕግ ቁጥጥር ሥር መዋል እለበት::
#The_enemy_is_the_system!