በፕሪሚየር ሊጉ ሊቨርፑል ድል ሲቀዳጅ ማንቺስተር ሲቲ ተሸንፏል
ጥቅምት 23/2017 (አዲስ ዋልታ) በ10ኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ መርሃ ግብር ሊቨርፑል በብራይተን ላይ ድል ሲቀዳጅ በርንማውዝ የሊጉን መሪ ማንቸስተር ሲቲን 2 ለ 1 አሸንፎታል።
ለበርንማውዝ ሰሜንዮ እና ኢቫኒልሰን አንድ አንድ ግቦችን ሲያስቆጥሩ ለሲቲ ብቸኛዋን ግብ ጊቫርዲዮል አስቆጥሯል።
ሊቨርፑል ብራይተንን 2 ለ 1 ባሸነፈበት ጨዋታ ጋክፖ እና ሳላህ አንዳንድ ግብ ሲያስቆጥሩ ለብራይተን ብቸኛዋን ግብ ካዲዮግሉ ማስቆጠር ችሏል።
ኖቲንግሃም ፎረስት ዌስትሃምን 3 ለ 0፣ ሳውዝሃምፕተን ኤቨርተንን 1 ለ 0 ሲያሸንፉ ኤፕስዊች ከሌስተር ሲቲ አንድ አቻ ተለያይተዋል።
ውጤቱን ተከትሎ ሊቨርፑል በ25 ነጥብ የደረጃ ሰንጠረዡን በአንደኝነት ሲመራ ማንችስተር ሲቲ በ23 ነጥብ ሁለተኛ እንዲሁም ኖቲንግሃም ፎረስት በ19 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።