#መልካም_ዜና: አሊባባ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ #በኢትዮጵያ_ብር ክፍያ መቀበል እንደሚጀምር አስታወቀ!
አለም አቀፍ የኤሌክትሮኒክስ ግብይት ተቋም የሆነው አሊ ባባ እንደገለፀው ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ #በአሊ_ኤክስፕረስ የበርካታ አገራትን ገንዘብ ጥቅም ላይ ያውላል፡፡
ከእነዚህ አገራት መካከል ኢትዮጵያ፣ ናይጄሪያ፤ ግብፅ፣ ኬንያ እና ደቡብ አፍሪካ ይገኙበታል፡፡ የክፍያ መፈፀሚያ ገንዘቦችን ማስፋፋት ያስፈለገው ለአፍሪካ ተጠቃሚዎች በስፋት ተደራሽ ለመሆን በማሰብ እንደሆነ የጠቀሰው አሊ ባባ በተጨማሪም በአለም አቀፍ የክሬዲት ካርዶችና #የውጭ_ምንዛሬ ላይ ያለውን ጥገኝነት ለማስቀረት እንደሆነ አስረድቷል፡፡
የአፍሪካ አገራትን ገንዘብ በግብይቱ ውስጥ ጥቅም ላይ ማዋሉ በአለም አቀፍ የክፍያ ስርአት የተነሳ ለአፍሪካዊያን ትልቅ ማነቆ የሆነውን ችግር ለመቅረፍ ማቀዱንም አስታውቋል፡፡ በዚህም አዳዲስ የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎችን እንደሚያገኝ ተስፋ ሰንቋል፡፡
ለዚህ እንዲረዳው በተጠቀሱት አገራት ከሚገኙ የዲጂታል ክፍያ አገልግሎት ሰጪዎች ጋር ጥምረት መፍጠሩን የገለፀው አሊ ባባ ከሚቀጥለው ሳምንት ማለትም #የካቲት_17 ጀምሮ ብርን ጨምሮ የተለያዩ ገንዘቦችን በግብይት ስርአቱ ውስጥ እንደሚያካትት አስታውቋል፡፡
#ለምሳሌ፦ አሊባባ ከቴሌ ብር ጋር ለመስራት ቢስማማ ከአሊ ኤክስፕረስ ላይ ኦንላይን/Online እቃ ለመግዛት ቴሌ ብር ተጠቅሞ መክፈል ይቻላል ማለት ነው!